በምዕራብ ግንባር ተሰልፎ የነበረው አርሚ 17 ኮር-2 ታጣቂዎች ሙሉ በሙሉ እጅ ሰጡ፤ ከጀርባቸው ጥቃት እንዲሰነዘር ያዘዙ አመራሮች ላይ ርምጃ ወስደዋል

Date:

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — የአርሚ 17 ኮር-2 በመባል የሚታወቀው የህወሃት ታጣቂ እየፈረሰና እጅ እየሰጠ መሆኑ ዛሬ ረፋድ ላይ ተመልክቶ ነበር። አሁን ላይ ከስፍራው በደረሰ ዜና እጅ የሰጡት ታጣቂዎች 280 ሆነዋል።

በምዕራብ ግንባር የተሰማራው የአርሚ 17 ኮር-2 ሜይዴይ ክፍለ ጦር በምርጫ ሺሻይ ኪዳነ የሚመራ ነው። ይህ ኃይል  በፀሊሞይ አካባቢ ስምሪት ተሰጥቶት ሲንቀሳቀስ እንደቆየ ያስታውቁት የዜናው በለቤቶች፣ ጦሩ የተሰጠውን ተግባር እየመረመረና እየመከረ ቆይቶ በዛሬው እለት ፈልሶ እጁን ለመከላከያ መስጠቱን አስታውቀዋል። 

መንግስት “ጽንፈኛ” የሚለው ህወሓት በትግራይና አጎራባች ክልልሎች እየፈጸመ ያለውን ትርምስ፣ የኃይል አፈሳና አምባገነናዊ አገዛዝ የተቃወሙት የአርሚ 17 ታጣቂዎች ዛሬ ማለዳ ላይ ህወሃት የሞከረውን ትንኮሳ ተገን አድርገው ነው እጅ የሰጡት። 

“ዓላማ ለሌለው ጦርነት ህይወታችንን አንገብርም” ራሳቸውን ከሌላው ኃይል በመለየት ሙሉ የአርሚው ሃይል ማለትም 280 ታጣቂዎች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ለአገር መከላከያ በማስረከብ በሰላም እጃቸውን ሰጥተዋል። ዛሬ መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም በግንባሩ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን የሰጡት አርሚ 17 ኮር-2 ሜይዴይ ክፍለ ጦር አባላት እጃቸውን ሲሰጡ ታማኝ የሚባለው የህወሃት ሌላ ኃይል ከጀርባ የጎዳቸው እንዳሉ መረጃውን ያደረሱት አመልክተዋል። 

ክፍለጦር ወደ ወገን ጦር እጅ ለመስጠት ሲነሳ እንቅስቃሴውን ለመግታት ተኩስ በከፈቱት የህወሃት ታጣቂ አመራሮች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደተወሰደ የዜናው ባለቤቶች አስታውቀዋል። ርምጃ ከተርወሰደ በኋላ ታጣቂዎቹ በሰላም ለአገር መከላከያ ሰራዊት እጅ ሰጥተዋል። ይህ ሲሆን የሚያሳይ ምስል ቀደም ሲል ማሰራጨታችን ይታወሳል። ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና እያገኙ እንደሆነም ታውቋል። 

ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ግንባሮች በተደራጀ መልኩ እና በተናጠል እጅ ለመስጠት የሚያደርገውን እንቅሰቃሴ እንዳለ ታውቋል። የህወሃት ከፍተኛ አመራሮችና የጦር አዛዦች “ጦርነት ከተጀመረ ጦሩ ይፈርሳል” የሚል ግምገማ እንዳላቸው ከሳምንት በፊት መዘገባችን አይዘነጋም። ዛሬ አርሚው ነቅሎ እጅ ስለመስጠቱ ከህወሃት በኩል የተባለ ነገር የለም። ዜናው ይፋ ከመሆኑ በፊት ግን “ሁለት የመከላከያ አባላት እጅ ሰጡ” በማለት የህወሃት ደጋፊ ከሆኑት ሚዲያዎች መካከል ዜና አሰራጭተው ነበር። አንዳንዶቹ ዜናው በቪዲዮ ተደግፎ ሲለቀቅ የለጠፉትን አንስተዋል። አንዳዶቹም ሃሰት እንደሆነ በመግለጽ ለማስተባበል ሞከረዋል። 

በሌላ ዜና “ጽምዶ” በሚለውና ሻዕቢያ በመመሪያ እንዳቋቋመው የተነገረለትን ህብረት የተቀላቀሉትን የፋኖ ሃይሎች በመቃወም በገሃድ አቁማቸውን ከሚገልጹት መካከል የጎንደር አፋብን ከተከዜ ዘብ ጋር ንግግር እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል። 

እነ አርበኛ መሳፍንትና አርበኛ ደረጀ በላይ መላው የጎንደር አፋብን ክንፍ አመራርና ታጣቂ ከተከዜ ዘብን ጋር የሚዋሃዱበት አገባብ ላይ እየመከሩ መሆኑ ተሰምቷል። እነ ኮሎኔል  ደመቀን በማነጋገር ላይ ናቸው የተባሉት ስማቸው የተገለጸውም ሆነ ከተከዜ ዘብ በኩል ይህ እስከተጻፈ ድረስ  ምንም የተባለ ነገር የለም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related