“ ግብፅ በጅቡቲ ለማከናወን ያሰበችው ፕሮጀክት የመገጭ ወንዝ  የመስኖ ግድብ የወለደው ብስጭት ነው”

Date:

አዲስ የወደብ እና የሎጂስቲክስ መገልገያዎችን ለመገንባት ፍላጎት ማሳየቷ በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጥረው የጂኦፓለቲካ አንድምታ

አዲስ ሪፓርተር ዜና – ግብጽ በጅቡቲ ለመጀመር አሰበች የተባለው የወደብ እና የሎጂስቲክስ መገልገያዎችን ለመገንባት ፍላጎት ማሳየቷ ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ገባር በሆነው በመገጭ ወንዝ ላይ በጀመረችው ግዙፍ ፕሮጀክት ንዴት የተነሳ መሆኑ ተገለጸ። የግብጽ እርምጃ መንግስት በጅቡቲ ብቻ መተማመን እንደማይገባ አምኖ ኢትዮጵያ የራሷ የባህር በር እንዲኖራት የጀመረው ጥረት ትክክለኛ መሆኑን አመልካች እንደሆነ የገለጹም አሉ።  ውሳኔው በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጥረው የጂኦፓለቲካ አንድምታ በማስላት ስጋት ተገባቸውም ጥቂት አይደሉም።

ኢትዮጵያ የሕዳሴው ግድብን ካስመረቀች በኋላ የአባይ ተፋሰስ በሆነው የመገጭ ወንዝ ላይ የመስኖ ግድብ በመገንባት የሃይድሮፖለቲካ አቅሟን ማሳየቷን ተከትሎ የግብፅ በቀጠናው ያሉ ሃገራት ጋር ግንኙነቷን በማጠናከር የኢትዮጵያን ተፅዕኖ ለመመከት ያለመ ስልታዊ ምላሽ እየሰጠች ለመስጠቷ  ከጅቡቲ የተሰማው ዜና ዋና ማሳያ መሆኑን በርካቶች ሲተቅሱ፣ የግብጽን አካሄድ “ ብስጭት የወለደው፣ ሊሳካ የማይችል” ሲሉ የገለጹም አሉ።

በቀይ ባህር ዙሪያ የግብፅ የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴዎች፣ በተለይም በዛሬው ዕለት የወጡ ዓለም አቀፍ ዜናዎች ግብጽ በጅቡቲ አዲስ የወደብ እና የሎጂስቲክስ መገልገያዎችን ለመገንባት የሚያስችላትን የትብብር ስምምነት ለማድረግ መቃረቧን ያስረዳል።

ይህ የግብፅ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ በአባይ ተፋሰስ ላይ ያላትን የልማት እና የቀጠና ፍላጎቶች አንፃር ትልቅ የጂኦፓለቲካ አንድምታ እንዳለው ጉዳዩን የሚከታተሉ እየገለጹ ነው።

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ንግዷ ከዘጠና በመቶ በላይ የምታከናውነው በጅቡቲ ወደብ በኩል ነው። የግብፅ በጅቡቲ ወደብ እና የሎጂስቲክስ ማዕከላትን ለመገንባት መቃረብ ለኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ንግድ መተላለፊያ በሆነችው ሀገር ላይ ያላትን  ተፅዕኖ መጨመር ያሳያል።  በዚህ ሁኔታ ግብፅ በጅቡቲ በሚኖራት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እና የሎጂስቲክስ ቁጥጥር በአባይ ተፋሰስ ልማት ዙሪያ ኢትዮጵያ ላይ ጫና በማሳደር የንግድ መስመሩን እንደ ስልታዊ መደራደሪያ ካርድ እንድትጠቀምበት እድል ለመፈጠር እንደሆነ የሚናገሩ፣  ይህም በኢትዮጵያ ንግድ ላይ የጂኦፓለቲካ ተፅዕኖ ተጋላጭነትን ሊጨምር እና የንግድ ፍሰቷን አስተማማኝነት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል ባይ ናቸው።

ግብፅ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በቀይ ባህር ዙሪያ ምክክር ሲያደርጉን ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር ድርሽ እንዳትል አቋም ከመያዛቸው ጋር ተዳምሮ ዛሬ ከጅቡቲ ጋር ያላትን ግንኙነት በኢንቨስትመንት ለማጠናከር እያደረገች ያለው ጥረት ኢትዮጵያን ከበባ ውስጥ የሚያስገባትና  ክልላዊ ጥምረት የመፍጠር ፍላጎቷን ማሳያ ተደርጓል።

ከሳምንት በፊት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ጎረቤት አይደለችም” በማለት በይፋ መቃወማቸው፣ ኢትዮጵያ የባህር በር መዳረሻ የማግኘት የቅርብ ጊዜ ምኞቷን ለመገደብ የታለመ ግልጽ ስትራቴጂያዊ እርምጃ እንደሆነ የቀጠናው ትንታኞች እያስረዱ ነው።

“ከዚህም በተጨማሪ ይህ የግብፅ እንቅስቃሴ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ እና ሌሎች የአባይ ገባር ወንዞች ላይ ኢትዮጵያ የምታካሂደው ልማት የሃይድሮፖለቲካዊ ውጥረት መቀጠልን ያመለክታል” የሚሉ ከጅቡቲ የወጣው ዜና፣ ግብፅ የኢትዮጵያን የልማት እርምጃዎች ለመግታት ዲፕሎማሲያዊ እና ስትራቴጂካዊ ጥረቶቿን በቀጠናው አጋሮች በኩል እያሳደገች እንደሆነ ማሳያ መሆኑን ይገልጻሉ።

“ በጅቡቲ የሚገነቡት አዲስ ወደብ እና የሎጂስቲክስ ማዕከል ግብፅ የባህር ኃይሏን በቀይ ባህር አካባቢ ይበልጥ እንድታሰፍር እና እንድታጠናክር እድል በመስጠት ለኢትዮጵያ የስትራቴጂያዊ ደህንነት ስጋት ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ወደብ የማግኘት ፍላጎቷን በይፋ በገለፀችበት በዚህ ወቅት፣ የግብፅ በቀጠናው ወታደራዊ አቅም እና ተፅዕኖ መጨመር በአካባቢው ያለውን የኃይል ሚዛን በመቀየር የኢትዮጵያን የጂኦፓለቲካ አቋም ይፈታተነዋል” በማለት ስጋታቸውን የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም።

እነዚህ ወገኖች ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጥረቶቿን በማጠናከር በግብፅ የሚካሄደው እንቅስቃሴ የክልላዊ ሰላምንና መረጋጋትን የሚጎዳ መሆኑን ለአፍሪካ ህብረት፣ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እና ለሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ማስረዳት እንዳለባት ያሳስባሉ።

እነዚህ ወገኖች አክለውም በቀይ ባህር ላይ ያለው የኢትዮጵያ ፍላጎት ፍትሃዊ እና በኢኮኖሚ የተደገፈ መሆኑን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በጠንካራ መከራከሪያ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳዎቅ፣  በተጨማሪም ምንም እንኳን ግብፅ በጅቡቲ የኢንቨስትመንት ፍላጎት ቢኖራትም ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ በእጅጉ እንደተሳሰረች ግልጽ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ከጂቡቲ ጋር ያላትን የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በማጉላት እና የጋራ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በማስፋት የባለቤትነት ስሜትን (ownership) ማጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ ይጠቁማሉ።

በሌላ በኩል ግብጽን ጅቡቲ ለመግባት እያደረገች ያለውን ሩጫ በማድነቅ “ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ ተሸነፈች” በሚል በስፋት ውግዘት የሚያቀርቡትን አስመልክቶ “ የግብጽ መንግስት የጅቡቲ ሩጫ ኢትዮጵያ ትልቁን የአባይ ግድብ የሆነውን የመገጭ ወንዝን ለልማት ማዋሏን ተከትሎ የተፈጠረ ንዴት ነው” ሲሉ ፕሮርጀክቱ እውን የሚሆን እንደማይመስላቸው በዘርፉ ጥናት የሚያደርጉ ሲያስታውቁ ያነሱት ማሳያ “ ጅቡቲ ላይ የሚሰራ ማናቸውም የወደብ ላይ አገልግሎት ኢትዮጵያን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ የማትጠቀምበት ከሆነ ዋጋ ስለማይኖረው ግብጽ በፕሮጀክቱ አትገፋበትም” የሚል ነው።

ግብፅ በሎጂስቲክ ግንባታ ወደ ጂቡቲ ለመዝለቅ ያቀረበችው ጥያቄ የተጀመረው ከአራት ዓመት በፊት አብዱልፋታህ አል ሲሲ ጂቡቲን ሲጎበኙ እንደነበር ይታወሳል። ወቅቱ ደግሞ የሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት የሚጀመርበት ነበር።

በወቅቱ ጂቡቲ ጥያቄውን በመርህ ደረጃ ብትቀበልም ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣ እንደነበር የግብጽ ሚዲያዎች አስታውቀው ነበር። በዚሁ መሰረት በጅቡቲ የኮንቴይነር ማራገፍያን ፣ የስፖርት ሜዳ፣ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ማቋቋም የመሳሰሉ ግንባታዎችን ግብጽ በራሷ ወጪ ለመገንባት ፈቃደኛ መሆኗ በግብጽ ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ዜና እንደነበር ይታወሳል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

Egypt’s Red Sea Signal: Opening the Door to a Historic Nile Agreement with Ethiopia

"sources like The National indicating Egypt's conditional openness to...

አብን በሁመራ፣ አዲረመጥ፣ ኮረም ኦፍላ፣ ጠለምት ራያና አላማጣ ሕዝቡ ለክልልም ምርጫም መሳተፍ አለበት አለ

አዲስ ሪፖርተር - "ህዝባችን ለክልሉ ምክርቤት ጭምር ምርጫ መካሄድ...

“ለዓመታት የፖለቲካ መብታቸው ተገፎ ለኖሩ ዜጎች የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ታሪካዊ እርምጃ” ወልቃይት

አዲስ ሪፖርተር - የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ...

“ለአራተኛ ጊዜ ተወረናል” ከወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ከሚቴ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ ሪፖርተር - "መንግሥትም የህዝቡን የማንነት እና የራስ አስተዳደር...