“በሙት ሕግ” መሪዎቿ አሳልፈው የሰጡት አሰብ “በፍትህ ከሄደች በቅሎየ ያለፍትህ የሄደች ጭብጦየ”

Date:

የኢትዮጵያ የውስጥ ሕጋዊ እርምጃ አባቶቻችን ይህንን እውነታ በመረዳት በአዋጅ ቁጥር 124/1945 አማካኝነት የቀድሞዎቹን የቅኝ ግዛት ስምምነቶች በይፋ በመሻር ለዛሬው ሕጋዊ ክርክር የማይናወጥ መሠረት ጥለውልናል። በዚህ አዋጅ ላይ በአንቀጽ 5፣ “ስለ ኤርትራ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረጉ ውሎችና ሰምምነቶች በዚህ ትዕዛዝ ፈርሰዋል፣ ዋጋ የሌላቸው ሆነዋል” በማለት በግለጽ ይሽራቸዋል። ይህ ድንጋጌ፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ የወሰደችው እጅግ ስልታዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ የሀገር ውስጥ ሕግ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የውሳኔ ሐሳብ 390 V ጋር ያለውን ጥብቅ ግንኙነት ስንመለከት፣ የመጀመሪያው ትልቁ ፋይዳ የ”ሕጋዊ ቀጣይነት” (Legal Continuity) መርህን ማረጋገጡ ነው። ተመድ በውሳኔ 390 V ላይ ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት “ሕጋዊ ፍላጎት” (Legitimate need) እንዳላት እውቅና ሲሰጥ፣ አዋጅ 124/1945 ደግሞ ይህንን ዓለም አቀፍ እውቅና ወደ ሀገር ውስጥ ሕግ ቀይሮታል። አዋጁ የቀድሞዎቹን የቅኝ ግዛት ስምምነቶች “ፈርሰዋል፣ ዋጋ የሌላቸው ሆነዋል” (Null and Void) ብሎ ሲያውጅ፣ በተመድ ውሳኔ እና በሀገሪቱ ሉዓላዊ ውሳኔ መካከል ያለውን የሕግ ክፍተት ደፍኗል። ይህም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መብቷን በራሷ ሉዓላዊ የሕግ ሥርዓት ውስጥ በማካተት የሕግ ቀጣይነት እንዲኖረው አድርጓል።


በአለባቸው ጉብሳ / የአዲስ ሪፖርተር አምደኛ

አዲስ ሪፖርተር – የአልጀርስ ስምምነት የተፈረመው “ሙት ሕጎችን” መሰረት ተደርጎ ነው። ታሪካዊ ጥላቶቻችን የትህነግንና የሻዕቢያን አመራሮች በወጣትነታቸው ወራት በቅኝ ግዛት ትርክት ኮትኩተው በማሳደግ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም እንዲሸረሽሩ አድርገዋቸዋል። የደህንነት እና የስነ-ልቦና ባለሙያዎች እንደሚስማሙበት፣ የአንድ ሰው የዓለም እይታ እና የርዕዮተ-ዓለም መሰረት የሚጣለው በአፍላ የጉልምስና ወቅት ነው። እነዚህ መሪዎች ኢትዮጵያን እንደ እናት አገር ሳይሆን እንደ “ጨቋኝ እና ቅኝ ገዥ” አድርገው እንዲመለከቱ ተደርገው በመታነጻቸው፣ የሃገራችንን ብሄራዊ ጥቅም ከማስከበር ይልቅ ለታሪካዊ ጥላቶቻችን የቅኝ ግዛት ትርክት ቅድሚያ ሰጥተዋል። በወጣትነታቸው የተጋቱት የጥላቻ ትርክት በስልጣን ዘመናቸው የሃገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም የሚሸረሽር ውሳኔ እንዲያሳልፉ አድርጓቸዋል።

የአልጀርስ ስምምነት በዋናነት የተመሰረተው ህጋዊ ተፈፃሚነት በሌላቸው “ሙት” የቅኝ ግዛት ውሎች ላይ ነው። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን የባህር በር ሉዓላዊ መብትመከራከሪያዎች ወደ ጎን በመተው፣ ተፈጻሚነት የሌላቸውን የጣሊያን ቅኝ ግዛት ስምምነቶች እንደ ብቸኛ የድንበር ማካለያ መስፈርት እንድትቀበል አድርገዋታል።  ይህም ኢትዮጵያ በታሪክም ሆነ በህግ ያላትን የባህር በር የማግኘት መብት አሳልፎ የሰጠ ስምምነት ሆኗል። ሉአላዊ የባህር በር የነበራትን የተከበረችና የታፈረችዋን ሃገራችንን ወደ ባህር በር አልባ ዝግ(Landlocked) ሃገር እንድትሆን አድርጓታል።

ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ፣ ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ ለዘመናት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወጪ አድርጋ የገነባቻቸውን ግዙፍ የወደብ መሰረተ ልማቶች እና የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ያለምንም ካሳ እና ዋስትና አሳልፎ መስጠቱ ነው። አንዲት ሃገር በገዛ ሃብቷ የገነባችውን ንብረት ያለምንም የኢኮኖሚ ጥበቃ አሳልፋ መስጠቷ፣ የአመራሮቹ የፖለቲካ ታማኝነት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ይልቅ ለተሳሳተው የቅኝ ግዛት ትርክት ማደሩን ግልጽ ማሳያ ነው። በዚህም ምክንያት ሃገሪቱ ዛሬ ለወደብ ኪራይ የምታወጣው ከፍተኛ ወጪ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ የዚሁ “የሙት ህጎች” ተከታይ ውጤት ነው።
በዚህ ፅሁፍ የኢትዮ ኤርትራን ጦርነት ለማስቆምና ድንበር ለማካለል በአልጀርስ ስምምነት የተጠቀሙት ኢትዮጵያ ከጣልያን ጋር የፈረመችውን የቅኝ ግዛት ስምምነቶች በተለያየ ወቅት ግዙፍ በሆነ መልኩ በጣልያን ወረራ የተሻሩ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ኤርትራን ከእናት ሃገሯ ጋር በፌደሬሽን ለማዋሃድ ያወጣው የህግ ውሳኔ እና ይህንኑ ተከትሎ ኢትዮጵያ በህግ የሻራችው በመሆኑ ተፈፃሚነት እንደሌለው እና ኢትዮጵያ ሉዓላዊ የባህር በር መብቷን ለማስከበር  ልትሞግትባቸው የሚገቡትን አለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ ሕጎች በተጨባጭ ማስረጃ በማስደገፍ እንደሚከተለው እናያለን።

የጣልያን ወራራና የሰላም ስምምነት  

ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የመንግስታት ሸንጎ (League of Nations) አባል ነበሩ። የሸንጎው ማቋቋሚያ ህግ አንቀጽ 10 መሰረት እያንዳንዱ አባል ሀገር የሌላውን የፖለቲካ ነፃነት እና የግዛት አንድነት የማክበር ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል። ሆኖም ጣሊያን በ1935 (እ.ኤ.አ) ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ይህንን ታላቅ የዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን በግልጽ ጥሳለች። በዓለም አቀፍ የልምድ ሕግ ትርጓሜ መሰረት አንድ ወገን በሁለትዮሽ ስምምነቶች ውስጥ የተቀመጡትን መሰረታዊ ግዴታዎች ሲጥስና የወረራ ተግባር ሲፈጽም ቀደም ብለው የተፈረሙ የድንበርም ሆኑ የጓደኝነት ስምምነቶች በሙሉ መሰረታዊ የውል ጥሰት “Material Breach” በሚባለው መርህ መሰረት ዋጋ አልባ ይሆናሉ።

ጣሊያን ኢትዮጵያን በሃይል ለመጠቅለል መሞከሯ ቀደም ሲል በ1900፣ 1902 እና 1908 የተፈረሙትን የድንበር ስምምነቶች በራሷ ፍላጎት እንደጣሰች ይቆጠራል። ጣሊያን ኢትዮጵያን “የእኔ ቅኝ ግዛት ነች” ብላ ካወጀችበት ቅጽበት ጀምሮ፣ እነዚያ ስምምነቶች በሁለት ሉአላዊ ሀገራት መካከል ዋጋ አልባ ይሆናሉ።

እንዲሁም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በ1947 የተፈረመው የፓሪስ የሰላም ውል፣ ጣሊያን በአፍሪካ የነበሯትን የቅኝ ግዛት መብቶችና ጥቅሞቿን በሙሉ በፈቃዷ እንድትተው አስገድዷታል። ይህ ማለት ጣሊያን በኢትዮጵያ ላይ የነበራትን ማንኛውንም የህግም ሆነ የድንበር ጥቅም በይፋ አጥታለች። ስለሆነም፣ ከአስርተ አመታት በኋላ የተካሄደው የአልጀርስ ስምምነት እነዚህን በጣሊያን ወረራና በዓለም አቀፍ ውሎች የፈረሱ ሰነዶችን እንደገና ህያው ለማድረግ መሞከሩ፣ የኢትዮጵያን የታሪክና የህግ የበላይነት ችላ ያለ አካሄድ ነበር።

የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ

ለኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ዋነኛው እና የበላዩ የሕግማዕቀፍ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤኤርትራን በፈደሬሽን ከእናት ሃገሯ ጋር ለማዋሃድ ያሳለፈውውሳኔ 390 V ነው። ይህ ውሳኔ ዋጋ ያጡትን የቅኝ ግዛትስምምነቶች በመተካት፣ ለኢትዮጵያ የባህር በር መብት እናለቀጣናው ደህንነት ዋስትና እንዲሆን ተብሎ የተዘጋጀ “የበላይየሕግ ሥርዓት” (Legal Regime) ነው። የተባበሩት መንግሥታትድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ 390 A (V) በታህሳስ 2 ቀን 1950 እ.ኤ.አ. ሲጸድቅ፣ በመግቢያው (Preamble) ላይ ኢትዮጵያ የባህርበር እንዲኖራት የሚፈቅደውን የታሪክና የፍትሕ ምክንያትበግልጽ እንደሚከተለው አስቀምጦታል።

“…Taking into consideration:

(a) The wishes and welfare of the inhabitants of Eritrea, including the views of the various racial, religious and political groups of the provinces of the territory and the capacity of the people for self-government;
(b) The interests of peace and security in East Africa;
(c) The strategic interests of Ethiopia, including her legitimate need for adequate access to the sea;”

የአማርኛ ቅጂውም እንደሚከተለው ይነበባል። …የሚከተሉትን ነጥቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት፦

(ሀ) የኤርትራ ነዋሪዎችን ምኞትና ደህንነት፣ በግዛቱ ውስጥየሚገኙትን የተለያዩ የዘር፣ የሃይማኖትና የፖለቲካ ቡድኖችአመለካከት እንዲሁም ሕዝቡ ራሱን የማስተዳደር አቅምን፤
(ለ) በምስራቅ አፍሪካ ያለውን የሰላምና የደህንነት ጥቅም፤
(ሐ) የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች፣ ይህም ተገቢናበቂ የሆነ የባህር በር የማግኘት ሕጋዊ ፍላጎቷን ጨምሮ፤”

ይህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የውሳኔ ሐሳብ፣ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት እንድትሆን የፈቀደው ዝም ብሎ ሳይሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባላቸውና በማይሻሩ ሦስት መሠረታዊ መርሆዎች ላይ ተመርኩዞ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ የኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት “ሕጋዊ ፍላጎት” (Legitimate Need) በማለት መግለጹ፣ ጥያቄው የታሪክና የፍትሕ መሠረት ያለው እንጂ በወረራ ወይም በኃይል የመጣ እንዳልሆነ ያረጋግጣል። በሁለተኛ ደረጃ፣ የባህር በር ባለቤትነቱን ከኢትዮጵያ “ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች” (Strategic Interests) ጋር በቀጥታ በማያያዝ፣ ሀገሪቱ ያላትን የጂኦፖለቲካዊ ሚና እና የኢኮኖሚ ህልውና ለማስቀጠል የባህር በር መኖሩ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን በሕግ አጽንቷል። በመጨረሻም፣ ይህ ውሳኔ የኢትዮጵያን የባህር በር መብት መከበር ከሃገራዊ ጥቅም አልፎ ለጠቅላላው “የምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደህንነት” (Peace and Security) ወሳኝ መሆኑን እውቅና ሰጥቷል። ይህም ማለት፣ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን ለቀጠናው መረጋጋትና ለዓለም አቀፍ ደህንነት ዋስትና መሆኑን የሚያሳይ የበላይ የሕግ ማዕቀፍ ነው። ይህ ሰነድ ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍመድረክ ለምታቀርበው የፍትሐዊ የባህር በር ጥያቄ ትልቁየሕግ መከራከሪያ (Legal Pillar) ሆኖ ያገለግላል። ይህ ሕጋዊመሠረት የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ጥቅም የሚያረጋግጥና የቅኝግዛት ውሎችን በተግባር የሻረ ብቸኛ ተፈጻሚነት ያለው ሰነድነው።

የኢትዮጵያ የውስጥ ሕጋዊ እርምጃ አባቶቻችን ይህንን እውነታ በመረዳት በአዋጅ ቁጥር 124/1945 አማካኝነት የቀድሞዎቹን የቅኝ ግዛት ስምምነቶች በይፋ በመሻር ለዛሬው ሕጋዊ ክርክር የማይናወጥ መሠረት ጥለውልናል። በዚህ አዋጅ ላይ በአንቀጽ 5፣ “ስለ ኤርትራ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረጉ ውሎችና ሰምምነቶች በዚህ ትዕዛዝ ፈርሰዋል፣ ዋጋ የሌላቸው ሆነዋል” በማለት በግለጽ ይሽራቸዋል። ይህ ድንጋጌ፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ የወሰደችው እጅግ ስልታዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ የሀገር ውስጥ ሕግ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የውሳኔ ሐሳብ 390 V ጋር ያለውን ጥብቅ ግንኙነት ስንመለከት፣ የመጀመሪያው ትልቁ ፋይዳ የ”ሕጋዊ ቀጣይነት” (Legal Continuity) መርህን ማረጋገጡ ነው። ተመድ በውሳኔ 390 V ላይ ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት “ሕጋዊ ፍላጎት” (Legitimate need) እንዳላት እውቅና ሲሰጥ፣ አዋጅ 124/1945 ደግሞ ይህንን ዓለም አቀፍ እውቅና ወደ ሀገር ውስጥ ሕግ ቀይሮታል። አዋጁ የቀድሞዎቹን የቅኝ ግዛት ስምምነቶች “ፈርሰዋል፣ ዋጋ የሌላቸው ሆነዋል” (Null and Void) ብሎ ሲያውጅ፣ በተመድ ውሳኔ እና በሀገሪቱ ሉዓላዊ ውሳኔ መካከል ያለውን የሕግ ክፍተት ደፍኗል። ይህም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መብቷን በራሷ ሉዓላዊ የሕግ ሥርዓት ውስጥ በማካተት የሕግ ቀጣይነት እንዲኖረው አድርጓል።

በሌላ በኩል፣ ይህ አዋጅ የቅኝ ግዛት ውሎችን በይፋ የቀበረ (Abrogation of Colonial Treaties) ታሪካዊ ሰነድ ነው። የ1900፣ 1902 እና 1908 ስምምነቶች በኢትዮጵያ ላይ ተጭነው የነበሩ ኢ-ፍትሐዊ ውሎች ቢሆኑም፣ አዋጅ 124/1945 አንቀጽ 5 እነዚህን ውሎች በመሻር ኢትዮጵያ ከጣሊያን ጋር የነበራትን ማንኛውንም የቅኝ ግዛት ውል በሕግ ፊት መቃብር አውርዶታል። ይህ እርምጃ ከተመድ ውሳኔ ጋር ያለው አንድምታ፣ ተመድ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን እንድትቀላቀል ሲወስን፣ መሠረት ያደረገው የቀድሞዎቹን የድንበር ውሎች ሳይሆን “ታሪካዊና ስልታዊ ፍላጎትን” መሆኑን አዋጁ በተግባር አጽንቶታል።

ይህ አዋጅ ለዛሬውም ሆነ ለወደፊቱ ዓለም አቀፍ ክርክር “የማይናወጥ መሠረት” ጥሏል። አዋጁ ዛሬ ላይ ለሚደረግ ማንኛውም ሕጋዊ ክርክር እንደ “መከላከያ ጋሻ” የሚያገለግል ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ውሎችን አስቀድማ በሕግ በመሻሯ ማንም አካል ዛሬ ላይ ተነሥቶ በነዚያ “በሞቱ ውሎች” ሊሞግታት አይችልም። ከተመድ ውሳኔ ጋር ተዳምሮ፣ አዋጁ ኢትዮጵያ የባህር በር መብቷን በሕግ አግባብ የወሰደች እንጂ በኃይል ያልያዘች መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚያረጋግጥ ሕያው ሰነድ ሆኖ ያገለግላል።

ከስልታዊ ትዕግሥት ወደ ፍትህ

የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪዎች እነዚህን ለኢትዮጵያ ምቹ የሆኑ የዓለም አቀፍ ህግ መከራከሪያዎችን ከመጠቀም ይልቅ፣ የጣሊያንን የቅኝ ግዛት ካርታዎች እንደ ብቸኛ ዋቢ መውሰዳቸው ትልቅ የታሪክ ስህተት ነው። በ1935 የተፈጸመው ወረራ የቀድሞ ውሎችን ውድቅ ማድረጉንና ኢትዮጵያ እንደ አሸናፊ ሀገር የራሷን የተፈጥሮ የባህር በር እና የታሪካዊ ግዛት መብት ማስከበር ሲገባት፣ በቅኝ ገዥዎች የተሰመሩ መስመሮችን “ተፈጻሚነት አላቸው” ብሎ መቀበል ሀገሪቱን ያለ ባሕር በር እንድትቀር አድርጓታል። ይህ ውሳኔ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እና ደህንነታዊ ብሄራዊ ጥቅም ያዳከመ “ጂኦፖለቲካዊ ክህደት” ነው።
የአልጀርስ ስምምነት ተፈፃሚነት በሌለው ዋጋ አልባ የቅኝ ግዛት ውልል ስምምነት መሰረት በመደረጉ ተቀባይነት የለውም። ፈራሽ ነው። በመሆኑም ያገር ሰው “በፍትህ ከሄደች በቅሎየ ያለፍትህ የሄደች ጭብጦየ” እንዲል የኢትዮጵያየባህር በር ጥያቄ ከስሜት ባለፈ በጠንካራ የሕግ እና የታሪክመሠረት ላይ የቆመ ነው። ከዚህ በፊት ስትከተለው የነበረውን ስትራቴጂክ ትዕግስት ወደ “ስትራቴጂካዊ ፍትህ” በመቀየር የዲፕሎማሲ ፓሊሲና ስትራቴጅዋን እንደገና ማጠናከርይኖርባታል። የባህር በር ማግኘት የፍላጎት ጉዳይ ብቻ ሳይሆንየሕልውና፣ የሕግ እና የታሪካዊ ፍትህ ጥያቄ በመሆኑ፣ኢትዮጵያ የሕግ መሠረቶቿን ከዘመናዊው የጂኦፓለቲካ ስትራቴጂ ጋር በማዋሃድ የባህር በር ባለቤትነቷንየምታረጋግጥበት ጊዜ አሁን ነው።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

የፕሮፌሰሩ እይታ “ጠንቋይ የሰዉን እንጂ የራሱን አያዉቅም” አብይ አሕመድ ነጥብ አስጥለዋል

ሀገር የምትገነባው መንግስት ያድርግ በሚሉ ጥያቄዎች ሳይሆን እኔ ይሄን...