አዲስ ሪፓርተር ባሕር ዳር — ካፒቴን ማስረሻ ሰጤን ተከትሎ የአፋህድ ምክትል ሊቀመንበር ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ ከእነ ሠራዊታቸው የሰላም አማራጭን መቀበላቸው ተገለጸ። “የሻዕቢያ ተወካይ ናቸው” የሚባሉት አቶ ነዓምን ዘለቀ “ኮሌኔል ገባ ቀረ የሚያመጣው ነገር የለም” አሉ። ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ቀድመው ይህን ማለታቸው ማንነታቸውን የሚያሳይ እንደሆነ ተመልክ
ባለፉት ሁለት ወራት በየቀኑ የሰላም ጥሪ በመቀበል የሚገቡ የፋኖ ታጣቂዎች መበራከታቸውን ተከትሎ “ህገወጡ ፋኖ እየፈረሰ ነው” በሚል በባህር ዳር የሚኖሩ አክቲቪስቶች በማህበራዊ ገጾቻቸው በተደጋጋሚ ሲጽፉ እንደነበርና “ስም አንጠቅስም እንጂ በቅርቡ የሚገቡ አሉ” የሚል ፍንጭም ሲሰጡ ነበር።
በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የአፋህድ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ፣ ድርጅታቸው ከክልሉ መንግሥት ጋር የደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ከእነ ሠራዊታቸው የሰላም አማራጭን በመቀበል ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሳቸው ይፋ የሆነው ፍንጮች በብዛት ከተሰጠ በሁዋላ መሆኑ፣ ሌሎችም እንደሚከተሉ አመላካች ሆኖ ተወስዷል።
ይህ እርምጃ በክልሉ ለረጅም ጊዜ የቆዩ ግጭቶችን በውይይት ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ስኬት ተደርጎ የተወሰደ ሲሆን፣ ኮሎኔሉና ሠራዊታቸው ወደ ሰላም መድረክ መመለሳቸው በክልሉ መንግሥት በኩል የሚቀርበው የሰላም ጥሪ ውጤት እያመጣ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ተመልክቷል።

ይህ የኮሎኔል ፈንታው ውሳኔ በመንግሥት የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ስትራቴጂ ላይ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው የፖለቲካና የፀጥታ ተንታኞች ይናገራሉ። ከፍተኛ ወታደራዊ ልምድ ያላቸው አመራሮችና ሠራዊት በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠታቸው፣ በጫካ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ታጣቂ ኃይሎችን የሞራል አንድነት የሚሰብርና ለተመሳሳይ የሰላም እርምጃ መንገድ የሚከፍት ነው። ይህም መንግሥት በወታደራዊ ዘመቻ ብቻ ሳይሆን፣ በፖለቲካዊ ድርድርና በማሳመን ጥበብ የሽምቅ ተዋጊዎችን አቅም ማዳከም እንደሚችል ማሳያ ሆኗል።
በተጨማሪም፣ እንዲህ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ሰላም መመለሳቸው በክልሉ የሚከሰተውን የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ከመቀነሱም በላይ፣ የመንግሥትን የፀጥታ ኃይል ትኩረት በልማትና በዘላቂ መረጋጋት ላይ እንዲሆን ያስችላል። ይህ ክስተት “ለችግሮች ሁሉ መፍትሔው ጠመንጃ ሳይሆን ውይይት ነው” የሚለውን መልዕክት ለታጣቂ ኃይሎች በግልጽ የሚያስተላልፍ ሲሆን፣ መንግሥትም ለሰላም ያለውን ዝግጁነት በተግባር ያሳየበት አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል።
“ኮሎኔል ፋንታሁን ሄደ መጣ ምንም የሚጠቅመው ነገር የለም። በፈረሰ ተጭኖ ሲሄድ ነው ነገሩ ያለቀው። ጡረተኛ ዛሬም ነገም ፋኖ ያሸንፋል እኛ ለክብሩ ብለን ነው እንጂ ድሮም ዝም ያልነው ሴረኛ መሆኑ ጠፍቶን አይደለም። አሸናፊዎቹ እኛው አማራዎች ነን!!” ሲሉ አቶ ነዓምን በቲውተር ገጻቸው አስፍረዋል።
የአቶ ነዓምን መልዕክት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የፈጠነ መሆኑ የሚወክሉትን ሻዕቢያን ንዴት የሚያመልክት እንደሆነ ማሳያ መሆኑ ወዲያው ተመልክቷል።
“በዓለም ላይ እንደ ፋኖ ትግል እሚያስቅ የለም ሁሉም እማይጠቅም ከሆነ ታድያ ማነው ጠቃሚው ታጋይ? ዓላማችሁ ምንድነው?” ሲሉ ለአቶ ነዓምን የጥያቄ ምላሽ ተሰጥቷል።
አቶ ነዓምን ባለፈው ቅዳሜ በዙም በተካሄደ ስብሰባ ኢትዮጵያ ውስጥ ትርምስና ሕዝባዊ አመጽ እንዲቀጣጠል ህቡን የማሳመን ስራ በሚዲያዎች መሰራት እንደሚገባ፣ በአሁኑ ሰዐት ሰልፍ ቢጠራ የሚወጣ ሕዝብ እንደሌለ መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል። አቶ ነዓምን አቶ ልደቱ ላቋቋሙት ግብረኃይል እውቅና ለመስጠት ድርጅቶቻቸው እያጤኑ እንደሆነ ገልጸው ከውይይቱ ቀድመው የሰጡትን መመሪያ የድምጽ ማስረጃ መለጠፋችን አይዘነጋም።
ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ በተመሳሳይ ሲገቡ፣ የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር አፈ ቀላጤ ልክ እንደ አቶ ነዓምን በፍጥነት ተመሳሳይ ቲዊት አድርገው እንደነበር አይዘነጋም።
ቀደም ሲል ከወራት በፊት ኮሌኔሉ ወደ ሰላም መንገድ እንደሚያቀኑ የእሳቸውን የቅርብ ሰው ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። አሁንም እንደሚሰማው ከሆነ በቅርቡ ሌሎች ኃይሎችም ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






