የሁለት ፎቶዎች ወግ፤ የሰላምና የቅጥረኛ ባንዳ መንገዶች

Date:

“ኮሎኔል ፋንታሁን ሄደ መጣ ምንም የሚጠቅመው ነገር የለም  በፈረሰ ተጭኖ  ሲሄድ ነው  ነገሩ ያለቀው   ጡረተኛ   ዛሬም ነገም ፋኖ ያሸንፋል   እኛ ለክብሩ ብለን ነው እንጂ  ድሮም ዝም ያልነው    ሴረኛ መሆኑ ጠፍቶን አይደለም። አሸናፊዎቹ  እኛው አማራዎች ነን!!” በባንዳነት ልክፍት፣ የዘሬ ያንዘርዝረኝ ብሎ ኢትዮጵያን እንደ ዘነዘና ለመደድበ ለግርዳናው በርካታ የሚገረደዱ ቀጥሮ ኢትዮጵያን ለማናጋት ሲለቀለቅና መርዝ ሲያመርት የሚውለው ተላላኪ ከብረሃን ፈጥኖ የለጠፈው ነው። የለጠፈው ደግሞ ኮሎኔል ፈንታሁን መሃባ “ለምን የሰላም መንገድ መረጡ” ብሎ ነው እናም ምስሎቹን አየሁና “የሁለት ፎቶዎች ወግ” አልኩ።

በአክሊሉ ኃይሉ

የሁለት ፎቶዎች ወግ፡ የሰላምና የባንዳ መንገዶች

በግራ በኩል የሚታየው ምስል የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩትን ካፒቴን ማስረሻ ሰጤን እና ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃባን ነው። ማስረሻ የትጥቅ ትግልን ትተው  ወደ ሰላማዊ ትግል  እንደሱ የተመለሱትን ኮለኔል ፋንታሁን አቀባበል እያደረገላቸው ነው። ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ አማራጭ የተደረገን ሽግግር ያመላክታል።

ሁለቱ አመራሮች የሀገሪቱንና የቀጠናውን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት በመረዳት፣ የትጥቅ ትግል አማራጭ የሕዝብን እንግልት ከማብዛት፣ መንግሥትንና ሀገርን ከማዳከም ባለፈ ለአማራ ሕዝብ ዘላቂ መፍትሔ እንደማያመጣ በመገንዘብ ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመልሰዋል።

ይህ ውሳኔ ሀገርን ለታሪካዊ ጠላቶች ተጋላጭ ከሚያደርግ የውጭ ኃይሎች ተላላኪነት በመውጣት፣ በውይይትና በሰላም ለሕዝብ መብት መቆምን የመረጠ የብስለት መንገድ እንደሆነ ይነበባል።

በተቃራኒው በቀኝ በኩል የሚታየው ምስል ነዓምን ዘለቀ እና የተመድ የኤርትራ አምባሳደር የሆነችውን ተጋዳላይ ሶፍያ ተስፋማርያምን ጎን ለጎን ያሳያል። ይህ ምስል በግልጽ እንደሚያሳየው፣ ነዓምን በነፃነት ትግል ስም ተሰልፎ ሳለ ከውጭ ዲፕሎማቶች ጋር የሚያደርገው ጥብቅ ግንኙነት ነው። እንደ ዘሮቹ ዘሩን ቆጥሮ በኢትዮጵያ ማሊያ እየተገረደደ እንደሚኖር ማሳያ ነው። ኢትዮጵያን እያተራመሰ ትራፊ የሚለቅም ባንዳ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

የነዓምን መንገድ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለጎረቤት ሀገር አጀንዳ ማስፈጸሚያነት አሳልፎ የመስጠት ግልጽ የባንዳነት መገለጫ ብቻ ሳይሆን ዘመን ቆጥሮ የዘሮቹን ታሪክ ያደሰ መሆኑን ጭምር ነው። ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላትን ተሰሚነትና የኢኮኖሚ ጥንካሬ ለማዳከም የሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች፣ የውስጥ ቅራኔዎችን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ሀገሪቱን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ እየሰሩ እንደሆነ የሚያሳየው የዚሁ የባንዳ ሽንት ምስል በጅምላ ለሚጮሁትና ከሱ ጋር ሆነው ሌት ተቀን ለሚያሰሩት “ኢትዮጵያዊያን ነን” ባዮችም ውርደታቸው ነው።

ይህ የነዓምን ፎቶ ወዶና ፈቅዶ በነፃነት ትግል ስም በውክልና ጦርነት (Proxy War) የሀገርን ሰላምና ሉዓላዊነት በማናጋት፣ የታሪካዊ ጠላቶችን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር የሚደረግ ብሄራዊ ክህደት  እንቅስቃሴ በመሆኑ ከትግል ይልቅ በታሪክ ተጠያቂ የሚያደርግ የክህደት ጉዞ መሆኑን ያመላክታል። እሱ ብቻ ሳይሆን አብረው የሚገረደዱት የባንዳዎች አለቅላቂዎችንም ያጠቃልላል። እነ አብሮነቶች!!

እነዚህ ሁለት ምስሎች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ ውስጥ ያሉትን ሁለት ተቃራኒ ዋልታዎች በግልጽ ያሳያሉ። በአንድ በኩል ለሀገር አንድነትና ለሕዝብ ደህንነት ሲባል የጦር መሣሪያን ጥሎ ወደ ሰላም የመጣው የካፒቴን ማስረሻ እና የኮሎኔል ፈንታሁን አስተዋይ መንገድ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገርን ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅም ለባዕዳን አሳልፎ በመስጠት በባንዳነት ስሌት ውስጥ መዘፈቅን የሚያሳየው ነዓምን ዘለቀን እና እሱ የሚነዳቸውን ገረዶቹን አሰላለፍ ያሳያል።

ጂኦፖለቲካዊ አንድምታው

ከቀጠናው ጂኦፖለቲካ አንጻር ሲታይ፣ እነዚህ ሁለት ፎቶዎች በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የኃይል ሚዛን ፍጥጫ ያሳያሉ። ካፒቴን ማስረሻ እና ኮሎኔል ፈንታሁን ወደ ሰላም መመለሳቸው፣ ይህንን የውጭ ኃይሎች ስትራቴጂ በማክሸፍ የሀገርን የውስጥ አንድነት የሚያጠናክርና ለቀጠናዊ መረጋጋት ፋይዳ ያለው እርምጃ ነው።

በሌላ በኩል፣ የነአመን ዘለቀ ከኤርትራ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ጋር መቧደን፣መዘፈቅ አደገኛ ጂኦፖለቲካዊ አዝማሚያን ያሳያል። ይህም የሀገርን ዳር ድንበርና የባሕር በር ጥቅሞች አሳልፎ ከመስጠት ጀምሮ፣ ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላትን የፖለቲካ የበላይነት ለመቀልበስ ለሚሰሩ ኃይሎች መንገድ መጥረግ ነው።

 በአጠቃላይ፣ ፎቶዎቹ የሚያስተላልፉት መልእክት ግልጽ ነው፦ አንደኛው መንገድ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለቀጠናው ሰላም የሚቆም ሲሆን፣ ሁለተኛው ግን ብሔራዊ ጥቅምን ለባዕዳን አሳልፎ በመስጠት ሀገርን የመበተን የባንድነት ፖለቲካ ውጤት ነው።

ዝግጅት ክፍሉ ይህ አስተያየት የጸሐፊው አሳብ ነው። የዝግጅት ክፍሉን አሳብ አይወክልም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በፀረ-ሽብርተኝነት እና በመፈራረስ መካከል ያለቸው ሶማሊያ “ሌላ አፍጋኒስታን?” የአሜሪካና አቋምና የአል-ሸባብ….

አዲስ ሪፖርተር - እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2021 ዓለምን ያስገረመው የአፍጋኒስታን...

የኢትዮጵያ፣ ህንድ እና እስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት የቀጠናው ፖለቲካዊ ትኩሳት፤ የኤርትራ መጨማደድ

አዲስ ሪፖርተር - ባለፈው ማክሰኞ በኢየሩሳሌም የተካሄደው የህንድ እና...

ጀርመንና ሕንድ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት አሳደጉ

አዲስ ሪፓርተር - የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ፍሪድሪክ ሜርዝ በሕንድ...

መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ ኬላ ላይ ተያዘ፤ መዳረሻው ሸዋ ሮቢት ነበር

አዲስ ሪፖርተር - መነሻውን ኤርትራ ያደረገ የጦር መሳሪያ ወልደያ...