አዲስ ሪፖርተር – በሚኒሶታ ተገኘ የተባለው ተከሰተ የተባለውና በምርመራ መረጃዎች እንደተገኘበት የሚገለጸው የማጭበርበር ቅሌ ፊቱን ወደሚታወቁ ባለስልታናትና የሕዝብ ተመራጮች እያዞረ ነው። በፖለቲካ ዘመቻ ሳይቀር ተፈጽሟል የተባለው የባለስልጣናቱ ቅሌት ጥልቅ ምርመራ እንደሚጀመርም ተስምቷል።
CNN ይዞት በወጣው መረጃ፥ የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት FBIን በሚኒሶታ ግዛት የፖለቲካ ዘመቻዎች በህገወጥ መንገድ ከህዝብ አገልግሎት ድርጅቶች በተፈጸመ ማጭበርበር ተጠቃሚ ሆነዋል ያላቸው አካላት ላይ ምርመራ እንዲጀምር ግፊት ማድረግ መጀመሩን አመልክቷል።
የዋሽንግተን ኤግዛማይነር ዘገባ እንደሚያመላክተው፣ የሚኒሶታው ገዥ የቲም ዋልዝ ተወካይ ኢልሃን ኦማር እና ሌሎች የግዛቱ ፖለቲከኞች በሚኒሶታ የህዝብ ጥቅም ማጭበርበር ቅሌት ውስጥ ከተካተቱ ሰዎች እና የማህበረሰብ እንክብካቤ አቅራቢዎች የዘመቻ ልገሳ ተቀብለዋል ተብለው ከሚጠረጠሩት መሃል እንደሆኑ ይጠቁማል።
ጥያቄው የመጣው ከሁለት ሳምንታት በፊት በምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቶድ ብላንሽ ስር ከሚሰሩ ከፍተኛ የህግ ባለሙያዎች ነው። የህግ ባለሞያዎቹ፣ እንደ ምግብ እርዳታ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና የቤት ውስጥ ጤና አጠባበቅ ማዕከላት ላሉ ድርጅቶች በህገ ወጥ መንገድ የተገኘው ገንዘብ ላይ ምርመራ እንዲጀምር FBIን ጠይቀዋል።

የFBI የህዝብ ሙስና ክፍል ለብላንች ቢሮ እንዳሳወቀው ጉዳዩን በአንክሮ እየተመለከተው እንደሆነ ነገር ግን እስካሁን በዘመቻው ላይ የጥፋት ማስረጃ እንዳላገኘ አሳውቋል። የፍትህ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በቀጣይ ሊኖሩ ስለሚችሉ ምርመራዎች አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።
ነገር ግን የሚኒስቴሩ ቀጣይ እርምጃ በሚኒሶታ የሚገኙ ፖለቲካ መሪዎችን ለመመርመር እና ክስ ለመመስረት እንደሆነ ይታመናል።
የፍትህ ሚኒስቴር ወደ አምስት የሚጠጉ የሚኒሶታ ባለስልጣናትን በመጥሪያ ደብዳቤ አስጠርቶ ምርመራ መጀመሩን CNN በዘገባው አሰፍሯል። ከባለስልጣናቱ መካከል የሚኒሶታው ገዢ ቲም ዋልዝ፣ የሚኒያፖሊስ ከንቲባ ጃኮብ ፍሬይ፣ የሚኒሶታ አቃቤ ህግ ኪት ኤሊሰን እና የሴንት ፖል ከንቲባ ካኦሊ ሄርን ይገኙበታል።
ይህ የዘመቻ ፋይናንስ ምርመራ በሚኒሶታ ያሉ ባለስልጣናትን በመንካት በግዛቷ እና በትራምፕ አስተዳደር መካከል ያለውን የሻከረ ግንኙነት ሊያባብስ እንደሚችል ተሰግቷል።
የፍትህ ሚኒስቴር ለዓመታት በሚኒሶታ በህገወጥ የህዝብ ጥቅም ማጭበርበር ቅሌቶች ጋር ተያይዞ በሚኒሶታ ባለስልጣናት ላይ ምርመራ ሲያካሂድ ቆይቷል። በተለይም እንደ “Feeding our futures” ያሉ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ላይ በሚሰራው ማጭበርበር ላይ ጠንከር ያለ ምርመራ አካሂዷል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚኒያፖሊስ የሚካሄዱ ተቃውሞዎችን ለማረጋጋት ፌዴራል ወታደሮችን ለመላክ እያስቡ እንደሆነም ጠቁመዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተቃውሞዎች እና በICE መኮንኖች ተሳትፎ በሚኒያፖሊስ ላይ በመጻፍ ሀሳቡን ያሰፈረው ብላንች “ዋልዝ እና ፍሬይ፥ የእናንተን አሸባሪነት ለማቆም በማንኛውም መንገድ ትኩረቴን አድርጌያለሁ። ይህ ዛቻ አይደለም። ቃል ነው” ሲል ተደምጧል። ምክትል አቃቤ ህጉ አክሎም “በቢሊዮን የሚቆጠሩ የታክስ ከፋዮች ዶላሮች ወደ ውጭ ወንጀለኞች እየፈሰሱ ናቸው።” በማለት በይፋዊ የትዊተር(X) ገፁ አስፍሯል።
አዲስ ሪፖርተር ከዚህ ቀደም የሚኒሶታ የበጎ አድራጎት ስርዓቶችን የሚጠቀሙ የምስራቅ አፍሪካ የግጭት ቀጠናዎች የማያባራው የአለም አቀፍ የሙስና ሰንሰለት አካል እንደሆኑ እንዲሁም በሚኒሶታ የሚዘረፈው እያንዳንዱ ዶላር የአሜሪካን አመኔታ እንደሚያዳክም እና በአፍሪካ ቀንድ ያሉ አሸባሪ ቡድኖችን ደግሞ እንደሚያጠናክር መዘገቡ ይታወሳል።
አሁንም ታድያ እንዲህ ያለ ለአፍሪካ ቀንድ የአሸባሪ ኃይል የጀርባ አጥንት የሚሆን የማጭበርበር ስራ ላይ የሚወሰድ እርምጃ ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






