ኤርትራ ሰራዊቷን ከአርሚ 70 ጋር አቀላቀለች፤ የትህነግ ተዋጊዎች መበተን

Date:

ራሳቸውን የትግራይ ሰላም ኃይሎች በማለት የሚጠሩት ወገኖች፣ ከአፋር ክልል ሃራ መሬት ለቀው ወደ ትግራይ እየገቡ መሆኑ ታውቋል። በስፍራው ከሚገኙ አመራሮች በተገኘ መረጃ፣ አሁን ላይ በዋጅራት አቅጣጫ ባህር ጽባን ይዘዋል። በቀጣይ ዒላማቸው አዲ ጉዶምን መቆጣጠር እንደሆነ ታውቋል። አሁን ላይ አዲጉዶምን በሃያ ኪሎሜትር የተጠጉትን የሰማ ኃይሎች ለማስቆም አርሚ 50 ተጨማሪ ኃይል ሆኖ እንዲገባ ተደርጓል።

  • የትህነግ ተዋጊዎች እየተበተኑ ነው፤
  • በመሆኒ አቅጣጫ የሰላም ኃይሎች እየገፉ ነው፤
  • ትህነግ እስረኞችን ወደ አዲጎዶም አጋዘ
  • በዋጅራት ጦርነቱ ቀጥሎ ባህር ጽባ ተያዘች  
  • የሰላም ኃይሎች አዲጎደም ለመያዝ ሃያ አምስት ኪሎሜትር ቀርቷቸዋል፤
  • ትህነግ አዲጎደምን ለመከላከል ሰፊ ኃይል አፍሷል፣ አንዋጋም ያሉ ጠፉ

አዲስ ሪፖርተር – ጋሽ ባርካ የነበረው የኤርትራ 65ኛ ክ/ሰራዊት 1ኛና 3ኛ ብርጌድ፣ ወደ ሱዳን ሃምዳይት መግባቱ ታውቋል። ቀደም ሲል ጀምሮ በሱዳን ሰፍሮ ለአልቡርሃን የሚያዋጋው አርሚ 70 መቀለ ላለው የትህነግ የሰራዊት አዛዦች መላኩን የዘገበው የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ የመቀለ ተባባሪ ነው።

መልዕክቱን ከተቀበሉት የትህነግ አመራሮች በተገኘው መረጃ መሰረት ወደ ሱዳን ሃምዳይት የገባው የሻዕቢያ ጦር፣ በኤርትራ አቅም ከባድ የተባለ መሳሪያ የታጠቀ ነው። በስፍራው ኡስማን የተባለ የሱዳን ደህንነት መኮንን አቀባበል እንዳደረገላቸው በቪዲዮ የተደገፈው መረጃ ያስረዳል።

የሻዕቢያ ተዋጊዎች ወደ ስፍራው ያቀኑት ባለፉት ሳምንታት የትህነግ፣ ኤርትራና ሱዳን ኃይሎች የፋኖ አመራሮችን አካተው ጥምረት መፍጠራቸውን ይፋ ካደረጉ በሁዋላ እንደሆነም ታውቋል።

አዲስ የተቋቋመው የአማራ ፋኖ በሄራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አስረሳ ማረ ዳምጤ ከዚህ ጥምረት በሁዋላ “የአፍሪቃ ቀንድ የሚበለጽገው ይህ ሕብረት መንግስት ሲሆን ነው” በማለት መናገሩ የሚታወሳ ነው።

የሻዕቢያ ወታደሮች ወደ ሱዳን ሃምዳይት መግባታቸውን ተከትሎ በተለምዶ ሳምሪ የሚባሉት፣ የአርሚ 70 እና የፋኖ ኃይል በጣምራ በወልቃይት በኩል ጥቃት ለመሰንዘር በዝግጅት ላይ መሆናቸው በተደጋጋሚ ሲገልጽ ነበር።

የዚሁ ዕቅድ አካል ይሁን አይሁን በይፋ ባይገለጽም፣ የፋኖ ታጣቂዎች በወልቃይት አቅጣጫ ጥቃት እፈጸማቸውን ከስፍራው የሚወጡ ዜናዎች አመልክተዋል። በወልቃይት ጠገዴ እንባጋላይ በተባለ ቀበሌ ጥቃት ከፈቱ ስለተባሉት የፋኖ ኃይሎች የዞኑ አስተዳደር በይፋ መግለጫ እንዲሰጥ ከአዲስ ሪፖርተር ቢጠየቅም ለጊዜው ዝምታን መርጧል።

ቴዎድሮስ ዕዝ 33ኛ ክፍለ ጦር አመራር ጋር የተደረገ የስልክ ልውውጥ እንዳረጋገጠው ጥቃቱ የሚፈጸመው ከትህነግ ጋር በጣምራ ነው።  

“ከሳምሪ ጋር አብረን እንሰራለን” ሲል የሚደመጠው አመራር፣ ዋናው ጉዳይ የወልቃይት ሳይሆን፣ ይህን መንግስት መጣል እንደሆነ በይፋ አስታውቋል። በስልክ ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበሩም ተቃውሞ አሰምተው “ይህ ተግባራችሁ በታሪክ ይቀመጣል” በማለት የስልክ ንትርካቸውን አቋመዋል።

ዘመነ ካሴም “አራት ኪሎ እንጂ ወልቃይት አጀንዳችን አይደለም” በማለት የተናገረበት መረጃ ይፋ መሆኑ አይዘነጋም። ይህ በመላው አገሪቱ፣ በአማራ ማህበረሰና በተለይም በአካባቢው ሕዝብ ዘንድ በክህደት የተመዘገበ ታሪክ ተደርጎ ተወስዷል። ይህንኑ የሕዝብ ቁጣና በአማራ ፋኖ መካከል ከፍተኛ ልዩነት ያስነሳ ጉዳይ ለማስተባበል የትህነግና ሻዕቢያ ሚዲያዎች “የአማራ ተቆርቋሪ ነን” ከሚሉ ጋር ተከታታይ የእርምት የሚመስል ፕሮፓጋንዳ እየሰሩ ይገኛሉ።

በሌላ ዜና ትህነግ በተለያዩ አርሚዎች ከፋፍሎ ያደራጃቸው ታጣቂዎቹ እየተበተኑበት መሆኑን የአዲስ ሪፖርተር የመቀለ ተባባሪ አስታወቀ።

በዚሁ መሰረት አርሚ 17 ከአዲ ቀየ ወደ አዲ ጉዶም ሲሸሽ፣ አርሚ 33 ከመሆኒ ወደ ማይጨው ማምለጡ ታውቋል። ታጣቂዎቹ የሸሹት ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

ራሳቸውን የትግራይ ሰላም ኃይሎች በማለት የሚጠሩት ወገኖች፣ ከአፋር ክልል ሃራ መሬት ለቀው ወደ ትግራይ እየገቡ መሆኑ ታውቋል። በስፍራው ከሚገኙ አመራሮች በተገኘ መረጃ፣ አሁን ላይ በዋጅራት አቅጣጫ ባህር ጽባን ይዘዋል። በቀጣይ ዒላማቸው አዲ ጉዶምን መቆጣጠር እንደሆነ ታውቋል። አሁን ላይ አዲጉዶምን በሃያ ኪሎሜትር የተጠጉትን የሰማ ኃይሎች ለማስቆም አርሚ 50 ተጨማሪ ኃይል ሆኖ እንዲገባ ተደርጓል።

አርሚ 50 ቀደም ሲል አሁን የሰላም ኃይሉን የሚመሩት ወዲ ሃንጽሩ ይመሩት የነበረ ኃይል ሲሆን እሁድ ዕለት “አልዋጋም” በማለት ተቃውሞ አስነስቶ እንደነበር መረጃውን ያጋሩን አመልክተዋል።

ትህነግ ቀደም ሲል ከዋጅራት ወደ አዲ ጉዶም አግዟቸው የነበሩትን እስረኞች ወደ መቀለ ለማጓጓዝ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የዓይን እማኞች አመልክተዋል።

የትግራይ ሰላም ኃይሎች አዲ ጉዶምን ከተቆጣጠሩ ሙሉ ደቡብ ትግራይ ነጻ እንደሚወጣ ስለ ኦፕሬሽኑ የሚያውቁ ይናገራሉ። ይህ ከሆነ ደግሞ በመጪው የድርድር ስብሰባ ላይ የትግራይ ሰላም ኃይሎችም ይሳተፋሉ። ይህን የተረዳው ትህነግ የሰላም ኃይሎችን ከትግራይ መሬት ለማስወጣት ኃይሉን አስተባብሮ እየተዋጋ ነው። በየአቅጣጫው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ትህነግ ሰራዊቱ እየተበተነ፣ ሕዝብ እየከዳው በመሆኑ ያሰበውን ለመተግበር አቅም አይኖረውም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኦነግ/ኦነስ በቄለም ወለጋ በሴቶችና ህጻናት ላይ የፈጸማቸው ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች “የጦርወንጀል” እንደሆነ ተገለፀ

አዲስ ሪፓርተር- አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው አዲስ መግለጫ በቄለም ወለጋ...

ሻዕቢያ እንደትላንቱ መስሎት እንዳይስት አብይ አሕመድ መከሩ፤ “ሻዕቢያ ማጥቃት ከሞከረ የመጨረሻው ይሆናል”

አዲስ ሪፖርተር - ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከዲያስፖራ ሰፈር የሚሰራጨው...

ስምረት ፓርቲ የጠ.ሚ አብይን ቃለ ምልልስ ተከትሎ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ ሰጥቷል አለ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም፣...