ስለ ጦርነቱ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጠ፤ ትህነግ የመጀመሪያና ሁለተኛ የጦርነት ሒሳቡን ይፋ አደረገ፤ “በዲፕሎማሲ ተበልጠናል”

Date:

  • አዲስ ሪፖርተር – የጦርነት ስጋት አይሏል፤ ሻዕቢያ ታንክ ይዞ ወደ ድንበር ጥሶ ገብቷል፤ ትህነግ በሳምንት ውስጥ አዲስ አበባ እንደሚገባ አስታውቋል፤ በርካታ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች መስረጋቸውን የተለያዩ ሪፖርቶች እያስታወቁ ነው፤ በትግራይ የተቋቋመው ሴንትራል ኮማንድ ፖስት የተለያዩ መመሪያዎችን እያወደ ይገኛል፤ በትግራይ የጦርነት ዝግጅት ተጧጡፏል።ድርቆች፣ በርበሬ፣ ቆሎ፣ በሶ፣ እንዲያዘጋጁ የታዘዙ በየደጃቸው ደፋ ቀና እያሉ ነው። በአጭር ቀን መንግስት እንደሚገለበጥ እየተሰማ መሆኑን ከዛው የሚወጡ መረጃዎች ያመልክታሉ። ከመንግስት ወገን ግን ምንም የሚሰማ ነገር የለም።  

ዛሬ እሁድ በትናንትናው ዕለት ዶክተር ደብረጽዮን የሚመሩት ኮማንድ ፖስት በገመገመው መሰረት ከሻለቃ ጀምሮ ወታደራዊ አመራሮች የተሳተፉበት ግምገማ ተደርጓል። የአዲስ ሪፖርተር የመቀለ ተባባሪ ያጠናከረው ሪፖርት እንደሚያመልክተው በዛሬው ግምገማ ስለ ጦርነቱ፣ ስለጦርነቱ የኃይል አሰላለፍ፣ ስለጦርነቱ ቁልፍ ዒላማዎች፣ እንዲሁም ስለ ጥቃት አቅጣጫና ከኤርትራ በኩል ስለሚገባው የመሳሪያና የኃይል ድጋፍ ተነስቷል።

ጦርነቱን አስመልክቶ በራያ በኩል ያለ የሌለ ኃይል በማሰለፍ የሚሌን መንገድ መቁረጥ ዋናው ስትራቴጂ ሲሆን፣ በዛ ቢባል በወር ጊዜ ውስጥ ያፋኖ ኃይል መሐሉን ተቆጣጥሮ አዲስ አበባ እንደሚገባ ተመልክቷል።

በውጭ አገር ካሉ የኦሮሞ ልሂቃን ጋር መግባባት መደረሱን በማመልከት፣ ኦሮሚያ ላይ በተመሳሳይ ፍጥነት መንግስት አፍርሶ አዲስ የመትከል ስራ እንደሚሰራ ለተሰብሳቢዎቹ ገለጻ ተሰጥቷል። ይህ ገለጻ ጃዋር መሐመድ ከትህነግ ሰዎች ጋር አብሮ መስራት መጀመሩንና ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ከትህነግ የበላይ አመራሮች ጋር በመስማማት ሁሉንም ብሄሮች ያካተተ አዲስ ጥምረት ለመፍጠር የአቶ ልደቱ አያሌውን አብሮነት ጥሎ ከመውጣቱ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ተመክቷል።

የኃይል አሰላለፍን በተመለከተ የቀጠናው አቋቋም ወደ ትህነግ ማድላቱ ተመልክቷል። የቀጠናው የኃይል አሰላለፍ ወደ ትህነግ ማድላቱን ሲያስታውቁ የጎራውን ልዩነት በአገር ደረጃ አላብራሩም።

ለተሰብሳቢዎቹ በግልጽ የተሰጠው መረጃ ግብጽ በኤርትራ በኩል ድሮን ማቅረቧ። በአየር ከፍተኛ ብልጫ እንደሚወሰድባቸው፣ ይሁንና ሃያ አምስት ከመቶ የሚሆነውን ጥቃት ለማክሸፍ ዕቅድ መያዙንና ይህ ከተሳካ ጦርነቱን ማሸነፍ እንደሚቻል ተገልጿል።

ጦርነቱ በታሰበው ደረጃ ባይሆን እንኳን እንደ ፕሪቶሪያው ባዶ እጅ ለድርድር ከመቀመጥ ይልቅ ጫና መፍጠር ሌላው ዕቅድ እንደሆነ ተመልክቷል።

የተወሰኑ አካባቢዎችን በመቆጣጠር የድርድር ጫና ለመፍጠር የተያዘው ዕቅድ ከአማራ ታጣቂዎች ዘንዳ የሚነሳውን የሃሰብ ልዩነት የሚያሳይ ሆኖ ተገኝቷል። ትህነግ የራሱን ፍላጎት ለማሳካት እንጂ ለአማራ ሕዝብ ሲል የሚያደርገው አንዳችም ነገር እንደሌለ የሚገልጹ እንዳሉት በስብሰባው ላይ የተነሳው በውጊያው የተወሰነ ቦታ በመቆጣጠር በድርድር ወቅት ጫና ለመፍጠር የተያዘው ዕቅድ ይፋ መሆኑ ዘግይቶም ቢሆን ይፋ መሆኑ በቀጣይ ምን እንደሚያስነሳ ለጊዜው ተባባሪያችን ያለው የለም።

ከትህነግ ጋር አብሮ የሚሰራው የዘመነ ካሴ ወገን የሆነው የፋኖ አደረጃጀት ትህነግ አራት ኪሎ እንደሚያስገባቸው፣ የወልቃይት ጉዳይ አራት ኪሎ ከገቡ በኃላ አቋም እንደሚይዙበት ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ይህ አቋም ለመከፋፈሉ ዋና መንስዔ የሆነና በጎንደርና ጎጃም ፋኖ መካከል መፈራረጅን ያስከተለ ነው።

የውጭ ጫናን በተመለከተ በዲፕሎማሲ መሸነፋቸውን መገምገማቸውን ለሰራዊቱ አዛዦች አብራርተዋል። አክለውም አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች ጦርነት እንዳይጀምሩ ጫና እያደረጉባቸው መሆኑን አመልክተዋል። አሜሪካንም ሆነች ዲፕሎማቱ ደብዳቤ ከመጻፍና ስልክ ከመደወል ያለፈ ጫና እንደሌላቸው አብራርተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሻዕቢያ ሚካናይዝድ ኃይል በራሱ ሙሉ ቁጥጥርና አመራር የሚንቀሳቀስ ሶስት ክፍለ ጦር በሶስት ግንባሮች አስገብቷል። በሽራሮ፣ በራማ፣ በዛላንበሳ አቅጣጫ የገባው የሻዕቢያ ኃይል ሜካናይዘድ መሆኑ ታውቋል። ስራውም ከጀርባ ሆኖ ለትህነግ እግረኛ ጦር ድጋፍ መስጠት እንደሆነ ተመልክቷል።

ትህነግ በትግራይ ክልል በሁሉም ከተሞች እና ገጠር ወረዳዎች ያቋቋማቸው የሎጂስቲክስ፣ ሞቢላይዜሽን፣ ጸጥታ፣ ክትትል እንዲሁም አግላይ የተባሉ ኮሚቴዎች ከየካቲት 11-19/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ውጊያ እንደሚጀመር የሚገልፅ መረጃ በማህበረሰቡ ዘንድ እያሰራጩ መሆኑን ገልጸን መዘገባችን አይዘነጋም።

የአገር መከላከያ ከ2013 በኋላ አጥፍቶ ጠፊዎቹን ጨምሮ ድሮን ያመርታል፣ የዓለም ዘመናዊ የሚባሉ የጦር ጀቶችን ታጥቋል። በአፍሪካ በእግረኛ ጦር ቀዳሚ ሆኗል በጥቅሉ አምስተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ማናቸውም ዓይነት የከባድና ቀላል መሳሪያ ተተኳሽ ያመርታል። ሰፊና ጥልቀት ያለው ሰራዊት መገንባቱን ታላላቅ አገራት ሳይቅወር እየመሰከሩ ነው። ችግር የሆነበት የውስጥ ጦርነት ላይ አቅሙን መተቀም አለማቻሉ እንደሆነ ይግለጻል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ አፈሳ መጀመሩ ተሰምቷል። መሳሪያ ጥለው አንዋጋም በማለት ወደ ቤታቸው የገቡትን ጨምሮ ወጣቶች እየታፈሱ ወደ ማሰለጠኛ እየገቡ ሲሆን፣ ህዝቡ በከፍተኛ ደረጃ ስጋት ውስጥ መውደቁን የሚያሳዩ ምልክቶች ይታያሉ። አንዳንድ አካባቢ ደግሞ የትግራይን ክልላዊ አርማ በመልበስና በመያዝ “ጊዜው የአንድነት ነው” የሚል ጭፈራም ይስተዋላል።

የትህነግ ሊቀመንበር በተደጋጋሚ ለአፍሪካ ህብረትና ለሊቀመንበሩ፣ እንዲሁም ለተለያዩ ዲፕሎማቶች “የድርድር” ጥያቄ በማንሳት የፌደራል መነግስት ጦሩን ወደ ትግራይ እያስጠጋ መሆኑን ጠቅሰው፣ የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እያሳደረባቸው እንደሆነ በዝርዝር በማስረዳት አቤቱታ ቢያቀርቡም ከመንግስት ወገን የተስጠ ምላሽ የለም።

መንግስት የአፍሪካ ሕብረት ስበሰባ ዝግጅትና እንግዳ መስተንግዶ ላይ መሆኑ፣ የአፍሪካ ጣሊያን ስብሰባ ላይ መጠመዱን ከመግለጽ ውጪ ስለ አገር ውስጥ ታጣቂ ቡድኖች ያለው ነገር የለም።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይና የአገር መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች ጦርነት ከተጀመረ የሚወሰደው እርምጃ ጠንካራ መሆኑን፣ ይህ ሲሆን ለቅሶ እንደማይመልሰው በተደጋጋሚ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

አቶ ጌታቸው ረዳ “የቻይናን ሕዝብም ብታሰልፉ አይሆንም” በማለት የሚያውቁትን ጠቅሰው፤ ዶክተር አብርሃም በላይም በተመሳሳይ “ይቅርባችሁ” በማለት ምክር መለገሳቸው የሚታወስ ነው።

በኢትዮጵያ ደረጃም ሆነ በትግራይ ሕዝብ ጦርነት እንዲቆም ፍላጎቱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ መስማት የተለመደ ነው። አሁን ላይ ከግብጽ፣ ሱዳንና ሻዕቢያ ጋር እየታየ ያለው በጋራ ኢትዮጵያን ለማጥቃት የሚደረግ እንቅስቃሴ ህዝብን ቅር እያሰኘ እንደሆነ አዲስ ሪፖርተር ያሰባሰበችው መረጃ ያስረዳል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ግን 51ኛ የምስረታ በዓሉን በድል ለማክበር ቆርጦ መነሳቱን እያስታወቀ ነው። የመዋጋት አቅሙም እንደ 2013 እንዳልሆነ አመልክቷል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የሮይተርስ የአዲስ አበባ ሰራተኞች የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ፈቃዳቸው ተነጠቀ

ሮይተርስ በአዲስ አበባ ያሰማራቸው ሶስት ጋዜጠኞቹ የስራ ፈቃዳቸው እንዳልታደሰና...

“በመናበብ አመጽና ረብሻ ለመቀስቀስ ከፓርቲዎች ጋር ተስማምተናል” ጃዋር “

አዲስ ሪፖርተር - “እኛና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ሁለት ድርጅት...

ትህነግ የአፍሪካ ህብረት ጫና ፈጥሮ እንዲያደራድረው ነጥቦችን አስቀምጦ ደብዳቤ ጻፈ

አዲስ ሪፖርተር - የፕሪቶሪያው ስምምነት በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረገ የአፍሪካ...