በግብጽ አስተባባሪነት ከሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ሱዳን ጋር ጥምረት የፈጠሩ በዲሲና ሎንዶን [ዳስ ይጥላሉ] ተባለ፤ “አናምናችሁም አሉን” ነዓምን

Date:

“አሳቡ አገዛዙን ማውገዝ፣ ሕዝብን በጋራ ማነሳሳት እና አመጽ ማቀጣጠል ከሆነ ለምን አብረን አንሰራም? ለምን እኛ የያዝነውን የሰለፍ ቀን ሰርዘን ከነሱ ቀን ጋር አንጣመርም” በሚል ከዙም ተሰብሳቢዎቹ አንዱ አነሱ። አቶ ነዓምን በፍጠነት ተቀብለው “እኛና እነሱ ዓላማችን ይለያያል። እኛ እነሱን ደግፈን አንሰለፍም” አሉ። ስብሰባው ሲዞርበት የስብሰቡንና ስብስቡ የተቅመጠለትን የስራ መደብ ሳያስቡት አደባባይ የሚያሰጡት አቶ ነዓምን “እኛና እነሱ ዓላማችን አንድ አይደለም” ሲሉ አብረው እንማይሰለፉ የገለጹት፣ እነሱ በሻዕቢያና ህወሃት አጀንዳ ስለተሰሩ ሻዕቢያና ህወሃትን ከማይደግፉት ሰፈር መገኘት ላኪዎቻቸውን መካድ ስለሚሆንባቸው ነው። ልክ አቶ ልደቱ ህወሃት ዙሪያ እንዳላቸው ቀይ መስመር” ሲሉ መረጃውን ያካፈሉን አመልክተዋል።

“ሃምሳ የትግራይ ተወላጆች አይወጡልንም” አቶ አባይ ከትህነግ

አዲስ ሪፖርተር ዜና – በሻዕቢያና በህወሃት መካከል የተጀመረው ጥምረት እያደር እየተሸረሸረ በመሆኑ፣ ነገሮች ከዚህ በላይ እየተበላሹ ሳይሄዱ በፍጥነት “ጊዜ የለም” በሚል የታሰበው ሁሉ እንዲከናወን የሻዕቢያ ወኪል የሆኑት አቶ ነዓምን ዘለቀ እና ሌሎች ተመሳሳይ ማዕረግ የተሰጣቸው አመራር ይወስዳሉ። በየአቅጣጫው ለማስጀመር የታሰበው ጦርነት በትርምስ እንዲታጀብ የተያዘው ዕቅድ በፍጥነት እንዲከናውን መመሪያ የወረደላቸው ሩጫ ይጅምራሉ።

በዚሁ አግባብ እስከ ግንቦት ማብቂያ የሚሰራ የድርጊት መርሃ ግብር ይነደፋል። በዚሁ መርሃ ግብር መሰረት በተመረጡ ሚዲያዎች፣ የተመረጡ የቅስቀሳና የፕሮፓጋንዳ ስራ ያለመታከት እንዲሰራ አቶ ነዓምን፣ አቶ ገለታውና ኢንጂነር ሙሉጌታ ይመደባሉ። በውስጥ ለግብረኃይሉ የተሰራጨው የሁለት ወር መርኃግብር፣ አርቲስቶችን፣ የፈጠራ ሰዎችን በመጠቀም ህዝብን ሆድ ከሚያስብሱ ቅስቀሳዎች ጎን ለጎን “ስሜት ቀስቃሽ” ስራዎች እንዲሰሩ ዕቅድ መያዙን ይገልጻል።

ለፕሮፓጋንዳ ስራ እንዲሆን የተመረጡ ሰዎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣ በተለይም ግብጽ የምትመራው በሻዕቢያ፣ ወያኔ፣ ሱዳንና አፋብን መካከል የተፈጠረው ጥምረት ባስከተለው መለያየት ሳቢያ እነ አቶ ነዓምን የሚመሩት የአመጽ አደረጅ ግብረኃይል ከውስጥና ከውጭ የመፈርከስ ያህል ችግር ላይ ወደቀ።

ይህ እነሱ ካሰቡት ውጭ ዞሮ የጠለፋቸው ጥምረት “ኢትዮጵያን ከባዕድ አጋራት ጋር ሆኖ መውጋት አይሆንም” የሚሉ የአማራ ተወላጆችን አስነሳባቸው። ይህን ለማብረድ ሲሞከር አልሆነ አለ።

በዚሁ ሳቢያ ስራቸው ያሉትን አቶ ልደቱ አያሌውን እና ኢንጂነር ሙሉጌታን በመያዝ የአማራ ተወካዮችን ለማግባባት አቶ ነዓምን ስብሰባ ጠሩና ከእነ አቶ ሽፈራው ጋር ውይይት ቁጭ አሉ። አማራን በመወከል ለውይይት የመጡት “ከአሁን በኋላ ዓይን ለዓይን አንተያይም” ብለው ተለያዩ። ይህንኑ ሪፖርት ይዘው ከትናንት በስቲያ ስብሰባቸው ላይ አቀረቡ። ትርምስ ሆነ።

ልዩነቱ ምንድን ነው?

እነ አቶ ነዓምን የሚመሩት ግብረኃይል የሻዕቢያና የህወሃት አጀንዳ የሚከናወነበት አውድ እንደሆነ “አናሳ” በሚል ተወከለው ከገቡ በኋላ የተገፉት በይፋ፣ በመረጃ የገለጡት፣ ተወካዮቹ የመጡበት ድርጅትና የቀድሞ ፋይላቸው፣ በስብሰባቸው ላይ ሲናገሩ ከሚሰማና ስለስብሰቡ የሚያውቁ በአደባባይ የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው። ይህ አንዱ ቡድን ሲሆን ሻዕቢያ በአቶ ነዓምን፣ ትህነግ በአቶ ልደቱ ተወክለው የሚመሩት ቡድን ነው። እንደ አጀንዳነት የአማራውን፣ የኦሮሞውን፣ ወዘተ አካቶ የብሔር ማንነትን በማንሳት ራሱን ተልዕኮ ተቀባይ እንዳልሆነ ለማሳየት የሚሞክር ነው። አደረጃጀቱም ምርጫውን አሰናክሎ መክሰም ብቻ ነው።

አቶ ነዓምን “በተለምዶ  ህብረት፣ጥምረት፣ ቅንጅት ወዘተ የሚባሉ ነገሮች አሉ። እዚህ እንደዚህ ዓይነት ጉዳይ የለም። ይህ አገዛዝ ምርጫ እንዳያደርግና ህጋዊ ቅቡልነት እንዳይኖረው ካደረገ በኋላ የሚበተን ነው” ማለታቸውን ጠቅሰን ከዚህ በፊት መዘገባችን አይዘነጋም።

ሌሎቹ የአማራ የተለያዩ አደረጃጀቶች ከሻዕቢያም ሆነ ከህወሃት የተደረገላቸውን ግብዣ “ወግድ” ያሉ ናቸው። እነዚህ ወገኖች በኢትዮጵያዊነታቸው፣ በወልቃይት፣ በራያ፣ ወዘተ ጉዳይ “አናሻቅጥም” የሚሉት ወገኖች ናቸው። ስለ ስብስቡ የሚያውቁ አሁን ላይ አማራን እንደሚወክሉ እየተናገሩ የአማራ ክልልን ለማፍረስ፣ ለመቆራረጥ፣ በደሙና አጥንቱ ያስከበረውን ማንነቱን ዳግም ሊያስነጥቁ፣ በየጊዜው ከሱዳን እየተነሱ ድንበር ላይ ያሉ ወገኖችን የሚገሉትን የሚደግፉትን ወዘተ ይቃወማሉ።

በሌላ በኩል፣ በግብረኃይሉ ውስጥ እያደር የተገለጸላቸው፣ ሲጀመር ሰለ “ኢትዮጵያ የመሰላቸው” ወገኖች አሉ። ከነዚህ መካከል ፕሮፓጋንዳው በዳታና በመረጃ ይደገፍ፣ እውነት ላይ እናተኩር፣ ብሔራዊ ጥቅማችንን እናስላ፣ከግብጽና ከሻዕቢያ ጋር የሚደረገው ግንኙነት አገር አይጎዳም ወይ?  ከምንም በላይ አግላይና ዘረኛ የሚባለው ንግግር አደገኛ እና ብሄርሰብ ለይቶ የማጥቃት አካሄድ መሆኑን በማንሳት የሚቃወሙ ድምጾች የሚሰሙበት ሆነ፤ ከዚያም አልፎ “እኛ ከግብጽም ሆነ ካሻዕቢያ አይከፈለንም። “double standard ወይም ብልጣ ብልጥ” አትሁኑብን እስከ ማለት የደረሱም ታዩበት።

የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ በተደጋጋሚ ስብሰባዎቹን በሙሉ በመረጃ አስድገፎ እንደዘገበው፣ ከነዚህ ሰዎች ጥያቂ በኋላ ማብራሪያ የሚሰጡት አቶ ነዓምን በእልቅና ስሜት “ስለ ኤርትራና ብሄራዊ ጉዳይ እዚህ አይነሳም፣ የዚህ ታክስ ፎርስ ስራ ምርጫውን ማወክና ማሰናከል ብቻ ነው። ፋሺስቱን አቢይ አህመድ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ መክፈት ነው” በማለት በየስብሰባው ሲደሰኩሩ ነበር።

መጨረሻ ላይ አካሄዱ ያላማራቸው ጥንቃቄ እየመረጡ ወይም በአቋማቸው መሰረት ከተለያዩ ኮሚቴዎች እየተወገዱ አሁን ላይ ደረሱ። ኃይል ሰብሰቦ ገዝፎ ለመታየት ኢንቨስት ያደርገውና የአቶ ልደቱን አብሮነት የዋጠው የአቶ ነዓምን ቡድን መጨረሻ “አገር አንቀጥቅጥ” የተባለ ሰልፍ ማዘጋጀት ትቶ ዳስ ጥሎ ውይይት ሊቀመጥ ወሰነ።

ያላስማማቸው ጉዳይ ምንድን ነው?

ባለፈው ረቡዕ በተደረገው ስብሰባ ላይ በቀረበ ተደጋጋፊ ሪፖርት “ልናካሂድ ያሰብነው ሰልፍ የሚሳካ አይመስልም፤ ልደቱ ይጨመርበታል” በማለት አቶ ነዓምን ብስጭታቸውን መደበቅ በማይችሉበት አኳኋን ተናገሩ። አቶ ልደቱ ለመጀመሪያ ጊዜ “ከአሜሪካ ውጭ ነኝ” በሚል አለቃቸውን ተቀብለው “በዲያስፖራ ያለው አማራ ቁጥሩ ከፍተኛ ነው” በማለት ጀመሩ። አከሉና “አነጋግረናቸው ፈቃደኛ አልሆኑም። እነሱ አብረውን ስለማይሰለፉ እኛ ማካሄድ አንችልም” ሲሉ አቶ ያሬድ ያቀረቡትን አማራች ሃሳብ አጠነከሩ። “ዳስ ጥሎ” መወያየት፤

እነ አቶ ነዓምን ያቀረቡት ጥያቄ አማራን በመወከል በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሰላማዊ ሰልፎች ለማዘጋጀት ዕቅድ የያዙትን ወገኖች “የእናንተን ፕሮግራም ሰርዙና ከእኛ ጋር በመሆን በጋር እንቁም” የሚል እንደነበር ስብሰባውን የተካፈሉ ገልጸዋል። በምላሹም “አናደርገውም” ተባሉ።

ራሳቸውን የሰው ልጆች መብት ተከራካሪ አድርገው የሚያቀርቡት አቶ ያሬድ፣ አዳራሽ በመከራየት እንግዶችን ጋብዞ ውይይት ማደረጉ እንደሚሻል አስቀድመው ያቀረቡትን አቶ ልደቱ አጎሉት።

ይህን ጊዜ የህወሃት ወኪል የሆኑትና በየለያዩ ጊዜያት ሱዳን እንደሚመላለሱ በስብሰባው ላይ የሚናገሩት አቶ አባይ “እኛ በየሳምንቱ ረቡዕ እንሰለፋለን፤ አሁን ሃምሳ ሰው እንኳን አይወጣልንም” በማለት በትግራይ በኩል ያለውን ክፍፍል አንስተው ሰልፉ እንዲቀር የቀረበውን አሳብ ደገፉ።

የትግራይ ተወላጆች ህወሃት በትግራይ ሕዝብ ላይ ተነገሮ የማያውቅ በደል ከፈጸመው፣ ትግራይን ከዘረፈውና ካወደመው ሻዕቢያ ጋር አብሮ መግጠሙ፣ በጅምላ የትግራይን ልጆች ከጨፈጨፈ፣ በጅምላ ከደፈረና የሃይደር ሕጻናትን በአየር ካጠቃ ዳግም ፍቅር መጀመሩ በምንም መስፈርት አይቀበሉትም። የተጀመረው ፍቅርም የጥቅም እንጂ ዘለቄታ አለው ብለው አያምኑም።

አብረን ከእነሱ ጋር እንስራ

“አሳቡ አገዛዙን ማውገዝ፣ ሕዝብን በጋራ ማነሳሳት እና አመጽ ማቀጣጠል ከሆነ ለምን አብረን አንሰራም? ለምን እኛ የያዝነውን የሰለፍ ቀን ሰርዘን ከነሱ ቀን ጋር አንጣመርም” በሚል ከዙም ተሰብሳቢዎቹ አንዱ አነሱ። አቶ ነዓምን በፍጠነት ተቀብለው “እኛና እነሱ ዓላማችን ይለያያል። እኛ እነሱን ደግፈን አንሰለፍም” አሉ፤

ስብሰባው ሲዞርበት የስብሰቡንና ስብስቡ የተቅመጠለትን የስራ መደብ ሳያስቡት አደባባይ የሚያሰጡት አቶ ነዓምን “እኛና እነሱ ዓላማችን አንድ አይደለም” ሲሉ አብረው እንማይሰለፉ የገለጹት፣ እነሱ በሻዕቢያና ህወሃት አጀንዳ ስለተሰሩ ሻዕቢያና ህወሃትን ከማይደግፉት ሰፈር መገኘት ላኪዎቻቸውን መካድ ስለሚሆንባቸው ነው። ልክ አቶ ልደቱ ህወሃት ዙሪያ እንዳላቸው ቀይ መስመር” ሲሉ መረጃውን ያካፈሉን አመልክተዋል።

መጨረሻውስ

ስብሰባው ሙሉ በሙሉ የሎንዶኑና የዋሽንግቶኑ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተሰረዘ ባይገልጽም፣ ማካሄድ እንደማይቻል ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በዚህ መሰረት ዳስ ይጣላል። ዳሱ የሚጣለው ዋሽንግቶን ዲሲ ነው። በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ያሉ የአማራ ተወላጆችና ትግሬዎች ጀርባቸውን በመስጠታቸው ፕሮግራሙ በዘፈን ብቻም ሊከናወን እንደሚችል እንደሚገምቱ የገለጹት የመረጃው ባለቤት “ በረቡዕ ስብሰባ የገባኝ ትልቅ ነገር ግብረኃይሉ መፈረሱ ነው” ብለዋል።

ይህ ሁሉ ሲባል የኦሮሞ ወኪል ናቸው የተባሉት ስለመኖራቸው አልተሰማምና የዋሽንግቶን ተባባሪያችን ጠይቆ ነበር፣ “ጀርባቸውን የሰጡ ይመስላል አንዳቸውም አልተገኙም” የሚል ምላሽ አግኝቷል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በረከት ገበሬዋን ጨምሮ ከነዳጅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ የተያዙ ክስ ተመሰረተባቸው

አዲስ ሪፖርተር - የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል...

ህወሃት የተለያዩ የስምሪት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ጀመረ ፤ ሰራዊቱን ወደ ሱዳንም እየላከ ነው

አዲስ ሪፖርተር ዜና - የህወሃት አመራሮች በዛሬው ዕለት...

ግብጽ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ህወሃት፣ አፋብን፣ ኦነሰ፣ እና ትንንሽ ታጣቂዎች ኢትዮጵያን ሊወጉ ነው

አዲስ ሪፖርተር - ግብፅ፣ ኢሳያስ እና የሱዳኑ ጄኔራል አል...