ኢትዮጵያ “የፈርዖን ቀንበር ተሸካሚዎችን” አስመልክቶ አግባብ ላላቸው ዓለም ዓቀፍ የወታደራዊና የፖላቲክ ማህበርሰብ አባላት መረጃ ሰጠች፤

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና – “አባቱም አያቱም ይታወቃሉ” በማለት የገለጹት “ጽምዶ” የተሰኘ ኢትዮጵያን የማጥቃት ትብብር ቅንጣት ታክል ትንኮሳ ከጀመረ ምላሹ እጅግ የከፋና የማንንም ፈቃድ የሚጠይቅ እንዳልሆነ የአገር መከላከያ የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ አስታወቁ።

“አሮጌ በሬና ቀበሮ” ተጣምደው ሊያርሱ እንደማይችሉ ሁሉ ይህ ተፈጠረ የተባለው ጥምረት ለኢትዮጵያ እዚህ ግባ የሚባል ስጋት እንዳልሆነ ያመለከቱት ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ፣ እንቅስቃሴ ዙሪያ የሚደረጉ ጥረቶችን “ቅዠት” ብለዋቸዋል።

“ምንም እንኳን ስጋት ባይሆንም” አሉ ጄነራሉ፣ እሳቤው ግን ጸረ ሉዐላዊ፣ ክብረ ነክ፣ የፈርኦነን ቀንበር የመሸከም ባንዳነት እንደሆነ ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ  አስታውቀዋል። አሳቡ በፍጹም ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል አመልክተው፣ ይህንን “ቅዠት” ያሉትን ምኞት “ወደ መሬት እናወርዳለን” ብለው ስንዝር ታክል እንቅስቃሴ በሚያደርጉ አካላት ላይ የሚወሰደውን ርምጃ ጠንካራ ይቅርታ የሌለው እንደሚሆን ፍንጭ ሰጥተዋል።

ይህንኑ “ቅዠት” ያሉትን የ”ጥምዶ” አሳብና እንቅስቃሴ በአገር ውስጥ ለሚገኙ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አስቀድሞ ማሳወቁን ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ አመልክተዋል። ይህም የሆነው በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥና በእንቅስቃሴው ዙሪያ የጠራ መረጃ ለማስጨበጥ በሚል እሳቤ እንደሆነ አመለክተዋል።

የመከላከያ የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ በሳምንቱ ማብቂያ አርብ በብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡትና አጭር ቃለ መጠይቅ ፤ “ቅዠት” ለመተግበር የሚሞክሩ ኃይሎችን ክፉኛ ባስጠነቀቁበት ወቅት ነው ይህን የተናገሩት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ሐሙስ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋን ካነሳች በኋላ ከግብፅ በኩል “ውጥረት፣ ትንኮሳ የሚመስሉ ነገሮች እየታዩ” መሆናቸውን መናገራቸውን ተከትሎ ነው ጄነራሉ ማስጠንቀቂያ የሰጡጥ አምባሳደር ነብያት ግብፅ “ከበባ በሚመስል መልኩ” እየተንቀሳቀሰች መሆኗን ለመጀመሪያ ጊዜ ስም ጠርተው ይፋ አድርገዋል።

ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ ገና ከጥንስሱ ይታወቅ እንደነበር የገለፁትን እንቅስቃሴ፣ ቀንበሩን የጫነባቸውን አካል አጀንዳ ለመተግበር ትንሽ ከሞከረ፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ሥራ እንደሚሠራ አካል፤ የሚወሰደው ርምጃ ሰም በእሳት እንደሚቀልጥ የሚያቀልጣቸው እንደሚሆን በግልጽ ተናግረዋል። “ይህም እንደሚሆን ነው የምናስበው፣ የምናምነው” ብለዋል።

ሰሞኑን በፖርት ሱዳን ኢትዮጵያን ተባብሮ ለማጥቃት በተደረገው የጥምረት ስብሰባ “የአማራ ወኪል ነኝ” በማለት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የኤርተራ መንግስት አማካሪ መሆናቸውን የሚናገሩት ፕሮፌሰር መሐመድ ሃሰን የሶማሌን ሕዝብ በመወከል፣ የኦጋዴን ነጻ አውጪ፣ ከኤርትራ ጋዜጠኛ የተባለ፣ በይፋ ያልታዩ የትህነግና የሌሎች አቶ አንዳርጋቸው “አናሳዎች ናቸው የተገኙት” ያሏቸው ተገኝተው ነበር።

ይህንኑ ተከትሎ ህዝብ በከፍተኛ ተቃውሞ እያወገዘውና በ”ባንዳነት” እየፈረጀው ያለው ይህ ከሱዳን፣ ግብጽ፣ኤርትራ መስለ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር አብሮ ኢትዮጵያን የመውጋት ዕቅድ በውጭ አገር ያሉትን የተለያዩ የተቃውሞ አደረጃጀቶችን ሳይቀር አናግቷል። “እንደዚህ መሆኑ አልገባንም ነበር” በማለት ራሳቸውንም ያገለሉ አሉ። አዲስ ሪፖርተር ራሳቸውን ያገለሉትን በማነጋገር ዜና ሪፖርት አቅርቦ ነበር።

ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ የሕዝቡን ቁጥ ጠቆም በማድረግ፣ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ የቅድመ-ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አመልክተው፣ ሰራዊቱ ነገ ሊፈጠር ለሚችለው ሁኔታ “በራሱ ቻናል ተቀማጭነታቸውን በኢትዮጵያ ካደረጉ የወታደራዊ አታሼ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ሰፊ የግንዛቤ ሥራ አከናውኗል” ብለዋል። ይህ ማስገንዘቢያ ያስፈለገበት ዋና ምክንያ፣ ቀዳሚ መረጃ ለመስጠት ታስቦ እንደሆነ እና  በዚህ በግብፅ የሚመራ እንቅስቃሴ ላይ አስፈላጊ ሲሆን እርጃ ለመውሰድ የማንንም ፈቃድ አንደማይጠየቅ፣ ርምጃውም እንግዳ እንዳይሆን ነው።

ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ትልቅ ወታደራዊ እርምጃ በሚወሰድበት ወቅት የማንንም ፈቃድ መጠየቅ ባያስፈልግም፣ የውጭ ወዳጆችና አብረው የሚሠሩ አካላት ሐሳቡን አስቀድመው እንዲረዱት ለማድረግ ሰፊ ስራ መሰራቱን አስታውቀዋል። ሜጀር ጄነራል ተሾመ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም በዚሁ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ የዲፕሎማሲ ሥራ ያከናውናል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ይህ የ”ጽምዶ” እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ሰላምና ደኅንነት አስጊ ተደርጎ እንደማይወሰድ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ስብሰቡ “ጫንቃቸውን ለፈርኦን ቀንበር” በሰጡ የኢትዮጵያ አካላት እና አካባቢው ላይ ያሉ ሌሎች እንደሆነ‍ ገልጸው፣ ዓላማውም “ፀረ ሉዓላዊነት” እንደሆነ ተናግረዋል።

የተለያዩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች፣ የሱዳንና የኤርትራ ሀይሎች በሱዳኗ ፖርት ሱዳን ከተማ ስብሰባ ማድረጋቸውን የሚያሳይ ቪዲዮ ከቀናት በፊት ከኤርትራ መንግሥት ጋር ግንኙነት ባለው ‘ህድሞና ቲቪ’ የዩቲዩብ ቻናል ላይ መለቀቁ ይታወሳል። ከዚሁ የቪዲኦ መረጃ ቆንጥረው አቶ አንዳርጋቸው “ምን ታመጣላቹህ” በማለት በራሳቸው የማህበራዊ ገጽ አስራጭተዋል።

ለኢትዮጵያ ችግር የሱዳን፣ የግብጽና የኤርትራ እንዲሆንም ሌሎች ከጀርባ ካሉ ተዋንያኖች ጋር በመሆን መፍትሄ እናመጣለን በሚል የዘመናት የኢትዮጵያ ጠላቶች መናኸሪያ በሆነችው ሱዳን ከትመው የመከሩት “ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉ ክፍሎች በግልጽ “ኢትዮጵያ ሱዳንን አጥቅታለች፣ ኢትዮጵያ በሱዳን ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች” በማለት “አገራችን” የሚሏትን ኢትዮጵያ ሲከሱ መሰማት የዘመኑ ነውር እንደሆነ የተበሳጩ ኢትዮጵያዊያን እየተናገሩ ነው።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኤፍሬም ማዴቦና ነዓምን በሻዕቢያ በዓል ላይ ታዳሚ በመሆናቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ለኢድ ቀን ተላለፈ፤

አዲስ ረፖርተር ዜና - አባላቶቹ በመበተናቸው መደበኛ ስብሰባውንና ሊያካሂዳቸው...

በሻዕቢያ የሚመራው የእነ ነዓምን ዘለቀ ግብረ ኃይል ተበተነ፤ ስብሰባ፣ ቅስቀሳ፣ ሰላማዊ ስለፍ በይፋ ቆመ፤

አዲስ ሪፖርተር ዜና - በኢትዮጵያ ምርጫ እንዳይካሄድ ለማደናቀፍ ተደራጅቶ...

[ሞዐ ተዋህዶ] አዲስ የድህረ ምርጫ ህዝባዊ አመጽ ዕቅድ በኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ ቀረበ

አዲስ ሪፖርተር ዜና - ምርጫ መካሄድ እንደሌለበት በተቀመጠው አግባብ...

አሜሪካና ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ምን እያሰቡ ነው? “አሜሪካ የኢትዮጵያን የባህር ፍላጎት ማሳካት ህልውናዋ ነው”

ኢትዮጵያ የቀጥታ የባህር ዳርቻ ባይኖራትም፣ በወታደራዊ አቅሟ እና የባህር...