ሲጀመር “ይፈርሳል” የተባለው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን [አደዋ]፤ “ብልጽግና አጀንዳዎቻችን ሊመልስ ነው” በአመጽ አመቻች የጋራ መድረክ የተነሳ ስጋት

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገና ከጅምሩ ጎራዴ ተስቦበት “ፈርሷል” ተብሎ የተመረተ ዕለት ዜና ተሰርቶበት ነበር። ዛሬ ደግሞ “ብልጽግና አጀንዳችንን ነጠቀን፤ በፕሮፓጋንዳ እናክሽፈው” በማለት አዲስ ምክክር የያዙ፣ ከምክክሩ መጀመር ጎን ለጎን ሂደቱን ይፈታተናል ያሉትን ዓየር ላይ ለማዋል ተዘጋጅተዋል።

የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪና የሻዕቢያ ወኪል ናቸው የሚባሉት አቶ ነዓምን “ብልጽግና አጀንዳችንን ነጠቀን በማለት መከፋፈል ተፈጥሯል። አዳዲስ አጀንዳዎች በመፍጠር በሚዲያዎቻችንና በማኅበራዊ ሚዲያ ደጋፊዎቻችን በኩል ቶሎ ቶሎ ማሰራጨት አለብን። በተለይ አማራ ክልል ላይ ትልቅ ችግር ገጥሞናል” በማለት ከሁለት ሳምንት በፊት በጋራ መድረኩ ስብሰባ ላይ መናገራቸውን የመረጃ ምንጮቹን ጠቅሶ ጽፏል።

ከጅምሩ አንስቶ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሲቀርብበት የነበረው ኮሚሽኑ “በሥራውና በተግባሩ ተገምግሞ ይውደቅ እንጂ ምንም ሳይታይ ከወዲሁ መቃወሙ አግባብ አይደለም” በማለት የተከራከሩ፣ በስፋት ተሰባሰቡ የተባሉት ሕዝብ የጠላቸው፣ በተለያዩ መድረኮች የተቃወማቸው፣ የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈትኑ፣ አብሮ መኖርን የሚያፈርሱና የዜጎችን ነጻነት የሚፈታተኑ ጉዳዮች የኮሚሽኑ ዋና አጀንዳዎች መሆናቸው ተስፋ የሰጣቸው ጥቂት አይደሉም።

ለዚህም ይመስላል አቶ ጃዋር መሐመድ ብልጽግናን ያሳጣ፣ መንግሥትን ያንቋሸሸ መስሎት ያቀረበው ቅድመ ትንተና እና “ከብልጽግና የዝግ ስብሰባ ያገኘሁት” ሲል ይፋ ያደረጋቸው መረጃዎች ተመልሰው “ድሮም ብልጽግና እንደሆንክ እናውቃለን” በሚል ያስተቹት።

በሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚጀመረው ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ነው። ከየወረዳው የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች (ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች)፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና ተወካዮች፣ የሲቪክ ማኅበራትና የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ የፌደራልና የክልል መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት በድምሩ አራት ሺሕ ተሳታፊዎችን ያካትታል።

ጉባኤው ከመጀመሩ በፊት በታችኛው መዋቅር (በየወረዳውና በየክልሉ) በተካሄዱት የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የተወካዮች ምርጫ መድረኮች ላይ የተሳተፈው አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ከፍተኛ ነው። በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ 1,195 ወረዳዎች ውስጥ በአሥር ሺዎች በሚቆጠሩ መድረኮች (ከመቶ ሺሕ በላይ) ዜጎች በቀጥታ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ላይ ተሳትፈዋል። ሂደቱ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ለማካተት 10 ማኅበራዊ መሠረቶችን (ለምሳሌ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ መምህራን፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ ገበሬዎችና አርብቶ አደሮች ወዘተ) መሠረት አድርጎ የተከናወነ መሆኑን ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው መረጃ ያስረዳል።

ከ4,000 ዋና ተመካካሪዎች በተጨማሪ፣ ሂደቱን በዕውቀትና በምክንያታዊነት ለመደገፍ ከ150 በላይ አመካካሪዎች (Facilitators) እና ከ70 በላይ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች በጉባኤው ላይ ይሳተፋሉ።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፣ ተመካካሪዎች ስሜታዊነትን አስወግደውና ኢትዮጵያን ማዕከል አድርገው የሰላሙን መንገድ ያቀናሉ የሚል ትልቅ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። ጉባኤተኞቹ በአምስት መቶ ቡድን ተከፋፍለው ለ30 ቀናት በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ የሚወያዩ ሲሆን፥ ይህም በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን ተመልክቷል።

የጉባኤውን መጀመር ዋዜማ በማስመልከትም በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች የመከላከያ ማርሽ ባንድ የሙዚቃ ትርኢት ሲያቀርብ ውሏል።

“ኢትዮጵያ ለታሪካዊውና ታላቁ የሀገራዊ ምክክር በምትሰናዳበት በዚህ ወሳኝ ታሪካዊ ወቅት፤ ለመላው የሀገሬ ልጆች የማስተላልፈው ታላቅና የከበረ ጥሪ አለኝ። ነገ የሚጀመረው ውይይት ፍቱን የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን፣ የእኛን እና የመጪውን ትውልድ ዕጣ ፈንታና የወደፊት ተስፋ ሙሉ በሙሉ የሚወስን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ጭምር ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግል የማኅበራዊ ገጻቸው አመልክተዋል።

“ሁላችንም ኢትዮጵያውያን የአድዋን መንፈስ ሰንቀን ለሀገር ግንባታ ያዳበርነውን ልምድ ወደ ምክክር እና መግባባት መቀየር ያስፈልገናል” ሲሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለሚሳተፉ ተመካካሪዎች የቅድመ ምክክር ገለጻ ሲሰጡ አስታውቀዋል። ኮሚሽነሩ አንድ ክፍለ ዘመን ወደኋላ ሄደው አንድነት “በክፍለ ዘመኑ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከሰት ድንቅ ታሪክ” ባለቤት እንደሚያደርግ አስታውሰዋል።

“ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትና ሁለንተናዊ ብልጽግና የምትተጉ፣ የኢትዮጵያ ታላቅነት ግድ የሚላችሁ ሁሉ፤ ፈረሱም ሜዳውም ይኸው! ትናንት አባቶቻችንና እናቶቻችን በዓድዋ ለሀገር ነጻነት፣ ለሉዓላዊነትና ለክብር ሲሉ በደማቸውና በአጥንታቸው እንደተዋደቁላት ሁሉ፣ ዛሬም ኢትዮጵያ የታሪክ አደራ የሚሸከሙ የቁርጥ ቀን ልጆቿን ትፈልጋለች” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጉባኤውን ጥልቅ ትርጉም በክፍለ ዘመን አንዴ ብቻ ከሚያጋጥም ክስተት — ከዓድዋ ድል ጋር አያይዘውታል።

በመሣሪያ ባነሱ አካላት የተሰላቸና ምሬት ውስጥ የገባው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም አካላት ወደ ሰላማዊ ውይይትና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመሩ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲጠይቅ በመኖሩ ይህ ቀን ልዩ እንደሚሆንና በምክክሩ ማጠቃለያ ሕዝብ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ እንዲሆን እንደሚደረግ የኮሚሽኑ አባላት በተለያዩ አጋጣሚዎች መናገራቸው አይዘነጋም።

“ዛሬ ሀገራችን የምትሻው ጠመንጃ ያነገቡ ሳይሆን በሀሳብ ብስለት፣ በእውነት፣ በዕውቀትና በጽናት ታጥቀው የተሰናዱ የሰላም ታጋዮችን ነው። እኛ ዛሬም እንደ ትናንቱ በታላቅ የድል ዋዜማ ላይ እንገኛለን፤ ምክንያቱም የኢትዮጵያና የሕዝቦቿ ማሸነፍ አይቀሬ ነው! በሰለጠነ ንግግር፣ በሰላማዊ ውይይትና ሀገራዊ መግባባት የገጠሙንን ፈተናዎች በሙሉ አልፈን ወደ ብልጽግና በጋራ እንሻገራለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ከምርጫው መጠናቀቅ በኋላ የሚጀመረው የምክክር መድረክ ታሪካዊ ውሳኔ ላይ ደርሶ ለመጨረሻ ውሳኔ ለሕዝብ እንደሚተላለፍ በርካቶች ተስፋ አድርገዋል። በተለይም በስምንት ምድብ ሥር የተካተቱት የመወያያ አጀንዳዎች ከወሬ ይልቅ በግልጽ በሀገሪቱ ሚዲያዎች ሲቀርቡ የሚፈጠረው ስሜት ከወዲሁ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የዘመን ክስተት አደዋና የምክክር ኮሚሽኑ ጥሪ!! ፓርቲም፣ መንግሥትም፣ ሰዎችም ያልፋሉ፤ ኢትዮጵያ ግን ትቀጥላለች!

አዲስ ሪፖርተር ርዕሰ አንቀጽ - “...አንድ የአፍሪካ አገር በአውሮፓ...

50 ሚሊዮን ብር ዓመታዊ ግብር የሚከፍል ድርጅት እንዴት “የፍትህ ያለህ” ጩኸት ተሰማበት

አዲስ ሪፖርተር ዜና - የዚህ ሪፖርት አቅራቢ ወደ ሬስቶራንቱ...

ትህነግና ሻዕቢያ በጋራ የተቃውሞ መግለጫ አወጡ፤ “ኢትዮጵያ የባህር በር እንዲኖራት አትፈቅድም”

አዲስ ሪፖርተር - በመጥረቢያው ብረትና በእንጨቱ እጀታ የተሳሉት ሻዕቢያና...

በኩርሙክ ግንባር የቀጠለው ጦርነት የአርሚ 70 ተዋጊዎችም ከባድ ጉዳት ድርሶባቸዋል

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ/ካርቱም | ሐምሌ 9 ቀን...