“የትግራይ ተወላጆች በወልቃይት በደል ይፈጸምባቸዋል” አስተዳደሩ ገለልተኛ አካል ያጣራው ይላል

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች አከራካሪ ከሚባሉት ቦታዎች አንዱ በሆነው ወልቃይት “ባለስልጣናት እና የጸጥታ ኃይሎች የትግራይ ተወላጆችን በዘፈቀደ እያሠሩ፣ እንቅስቃሴና ሥራቸውን በእጅጉ እየገደቡ ነው” ሲል ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ዞኑ በበኩሉ ለዘላቂ ሰላም ሲባል ካልተረጋገጡ ትረካዎች ይልቅ ለሀገራዊ የሕግ ማዕቀፎች እና በማስረጃ ላይ ለተመሰረተ ግምገማ ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ በማሳሰብ ሪፖርቱን ውድቅ አድርጓል።

ሂውማን ራይትስ ዎች እ.እ.እ አቆጣጠር መጋቢት 20 ለኢትዮጵያ መንግስት መነሻ ሪፖርቱን አቅርቦ ማላሽ እነዳላገኘ በመግለጽ ይፋ ባደርገው ሪፖርት፣ ከ2020-2022 በነበረው ግጭት “ቤታቸውን፣ የንግድ ሥራቸውን፣ መሬታቸውን ያጡ በዞኑ ውስጥ ያሉ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት ትንኮሳ፣ ዕገዳና እና በደል እያጋጠማቸው መሆኑን አመልክቷል።

የዞኑ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ሪፖርቱን የተቀነባበረ ትረካ ላይ ያተኮረ መሆኑን እንደሚገነዘብ አመልክቷል። ሪፖርቱ ያቀረባቸው የውሳኔ ሃሳቦች፣ የታለመ ማዕቀብ እና ዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነትን ጨምሮ፣ ያሉትን ውጥረቶች ከመፍታት ይልቅ የሚያባብሱ እንደሆኑ አመልክቷል። እንዲህ ዓይነቶቹ እርምጃዎች ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ፋይዳ የሌላቸው ከመሆኑም በላይ፣ ለአካባቢው ግጭት መከሰት መነሻ የነበሩ አካላት በድጋሚ እንዲመለሱ በር የሚከፍት አካሄድ እንደሆነ አመልክቷል።

የሂውማን ራይትስ ዎች አርባ ሰዎችን በርቀት ቃለ መጠይቅ ማድረጉን፣ ስምንት የእርዳታ ድርጅት ሠራተኞችን እና ዲፕሎማቶችን ማነጋገሩን ጠቅሶ ባወጣው መረጃ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ዓለም አቀፍ አጋሮቻቸው በስፍራው ያሉ “የትግራይ ተወላጆችን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የሚያደርግ ያለውን አያያዝ ችላ ማለት የወሰኑ ይመስላል” ሲል ከሷል።

ወደ 2014 ሪፖርት በመመለስ የመብት ተሟጋች ድርጅቱን በራሱ ሪፖርት የሚሞግተው የዞኑ አስተዳደር፣ በሚያዝያ ወር 2014 ዓ.ም በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ውስጥ “የዘር ማጽዳት እና የግዳጅ ማፈናቀል ተፈጽሟል በሚል ያወጣውን ሪፖርት እናስታውሳለን፤ ይህ የቀድሞ ክስ ትክክል ቢሆን ኖሮ፣ አሁን እየተካሄደ ነው የተባለው ተቋማዊ መድልዎ መሬት ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ይሆን ነበር። ይህ ግልጽ ቅራኔ የሚያሳየው የቀድሞው ሪፖርት ባልተረጋገጠ ወይም ያልተሟላ መረጃ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው” ሲል የያዘውን አቋም ያጣጥላል።

በስፍራው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መታወቂያ እንደሚነፈጋቸው፣ ለመንቀሳቀስ ምቾት እንደማይሰማቸው እና የሚንቀሳቀሱት አማራጭ ከሌለ ብቻ እንደሆነ መገንዘቡንም በሪፖርቱ አካቷል። የአካባቢው ባለሥልጣናት የትግራይ ተወላጆች በአካባቢው ካሉ ከተሞች ለመውጣት “ጊዜያዊ ፈቃድ እንዲያገኙ ይጠይቃሉ” ሲል ሂውማን ራይጽ ዎች የከሳል።

ሂውማን ራይትስ ዎች አከራካሪ ከሚባሉት ቦታዎች አንዱ በሆነው ወልቃይት “ባለስልጣናት እና የጸጥታ ኃይሎች የትግራይ ተወላጆችን በዘፈቀደ እያሠሩ፣ እንቅስቃሴና ሥራቸውን በእጅጉ እየገደቡ ነው” በሚል ባወጣው ዘገባ፣የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ለማስቆም፣ ደርሷል ባለው “ከባድ በደል የተሳተፉ ባለስልጣናትን ለማገድ፣ ለመመርመር እና ተጠያቂ ለማድረግ መወሰን አለበት” የሚል ማሳሰቢያ አስፍሯል።

አክሎም በወልቃይት የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ዘርፈ ብዙ ቸግር እንደሚያጋጥማቸውና ህይወት እንደከበዳቸው ከደምዳሜ ደርሷል። ሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ላቲቲያ ባደር “የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና አጋሮቻቸው የትግራይ ተወላጆችን ችላ ያሉ ይመስላል” ማለታቸውም በሪፖርቱ ተካቷል።

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር ሰብሳቢና የወልቃይት ጠገዴ ማንነትና ወስን አስመላሽ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዶከተር ገሰሰው ወንድም የመብት ተሟጋቹን ድርጅት ክሶች “መሰረተ ቢስ፣ ሚዛን የጎደለው፣ በበቂ መረጃ ያልተደገፈ እንደሆነ በመግለጽ ውድቅ አድርገውታል።

“አስተዳደራችን ለሚከተሉት ቁርጠኛ መሆኑን ያረጋግጣል” በማለት ከተቃውሞ በዘለለ ጥያቄዎችን ለመብት ተሟጋቹ እየነቀሰ አቅርቧል።

  1. ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ፣ የሲቪሎችን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ገለልተኛ የሆኑ የማጣራት እና የማረጋገጥ ስራዎችን ማከናወን፤
  2. ተፈናቃዮች በክብር ስለመመለስ፣ በየወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ሁመራ ዞን ውስጥ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችን ሳይጨምር፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በፈቃደኝነት እና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ማድረግ፤
  3. ውዝግቡን በሕገ-መንግስታዊ ማዕቀፍ መፍታት፡ ማንኛውንም ችግር በሕገ-መንግስታዊ እና በሕጋዊ አሰራሮች ብቻ መፍታት፤
  4. የሕግ የበላይነት፡ ማንኛውንም ግለሰብ የብሄር ማንነት ሳይለይ ለፈጸመው የተለየ ወንጀል ተጠያቂ ማድረግ፤ እንዲሁም መሰረተ ቢስ እና ፖለቲካዊ ዓላማ ያላቸውን ክሶች ውድቅ ማድረግ።

ይህን በዝርዝር በማቅረብ የመፍትሄውን አቅጣጫ ያመላከተው የዞኑ መግለጫ፣ “የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዚህ ሪፖርት ውስጥ የቀረቡትን ያልተረጋገጡ እና ሚዛናዊ ያልሆኑ ክሶችን ወደ ጎን በመተው፣ ለዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋት፣ ፍትህ እና እርቅ ዋስትና ለሚሰጠው በኢትዮጵያውያን ለሚመራው የሰላም ሂደት ድጋፉን እንዲሰጥ በአክብሮት እንጠይቃለን” ሲል አሳቡን ይቋጫል።

በስም ተጠቅሰው ማዕቀብ እንዲጣልባቸው ለተጠየቀው ኮሎኔል ደመቀ ለቢቢሲ የሰጡትን ማላሽ ከስር ያንብቡ

ሂዩማን ራይትስ ዎች ረቡዕ ዕለት ባወጣው ሪፖርት ደግሞ የኢትዮጵያ አጋር የሆኑ አካላት “እንደ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ” ያሉ አመራሮችን “ዒላማ ያደረገ ማዕቀብ” እንዲጥሉ ጠይቋል።

ኮሎኔሉ ለዚህ ምላሽ ሲሰጡ ” (ስቀው). . .እኔ እነዚህን ከትግራይ ሰዎች ውጪ ናቸው አልልም፤ እነዚህ ህወሓት ትናንትና በየቦታው ያስቀመጣቸው በስመ ሂውማን ራይትስ ዎች ተቋሙን ተጠቅመው የሚያራምዱት የራሳቸውን የፖለቲካ ፍላጎት ለማስተግበር ካልሆነ እኔን የሚመለከት ነው ብዬ አላስብም” ብለዋል።

አስተዳደሩ “ገለልተኛ” የሆነ አካል በአካባቢው ተፈጽሟል የሚላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አጣራለሁ የሚል ከሆነ ፈቃደኛ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“ገለልተኛ” የሆኑ የመገናኛ ብዙኃን እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች “የትግራይ ሰዎች ላይ የደረሰውን ብቻ ሳይሆን የወልቃይት ሰዎች ላይም የደረሰውን የሚያጣራ ከሆነ” አስተዳደራቸው በሩ ክፍት መሆኑን ተናግረዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከአካባቢው የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች አስተዳደሩ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ስር ከሆነ በኋላ ምን ያህል ተመልሰዋል ተብለው የተጠየቁት ኮሎኔል ደመቀ “ከአስር ሺህ በላይ እዚህ አለ። በራሱም አልሄድም ብሎም የቀረ አለ። ተደናግጦም ወጥቶ የተመለሰም አለ። ኢትዮጵያዊ ነኝ እስካለ ድረስ የመኖር መብቱ የተጠበቀ ነው” ብለዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አሜሪካና ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ምን እያሰቡ ነው? “አሜሪካ የኢትዮጵያን የባህር ፍላጎት ማሳካት ህልውናዋ ነው”

ኢትዮጵያ የቀጥታ የባህር ዳርቻ ባይኖራትም፣ በወታደራዊ አቅሟ እና የባህር...

“የአሜሪካና ኢትዮጵያ ወዳጅነት አደገኛ ነው፤ ከማን ጋር እንደምንዋጋ አልገባንም፤አሳልፋ ልትሰጠን ትችላለች”

አዲስ ሪፖርተር - በአገር ቤት ሕዝባዊ አመጽ ለማነሳሳት የተደራጀው...

ኤርትራ ለህወሃት መሪዎች የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የመስጠት ስምምነት አገደች

አዲስ ሪፖርተር - የኤርትራ መንግስት ለህወሃት አመራሮችና ከፈተኛ ወታደራዊ...