አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማህበርን ዓመታዊ እራት ለመታደም ተሰብስበዋል። ከ2600 ባልይ እንግዶች ፊት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በክብር መድረኩ ላይ ተቀምጠዋል። ሴሽታው እየተጠበቀ ባለበት ሰዓት ድንገት አዳራሹን የሚያናውጥ የተኩስ ድምጽ ተሰማ። የደስታው መንፈስ በቅጽበት ወደ ድንጋጤ ተቀየረ፤ እንግዶች እንደዘነጡ ጠረጴዛቸው ስር ወለል ላይ ተኙ ተባሉ። በዓለም ዙሪያ ያሉ ሚዲያዎችም ትኩረታቸውን ሁሉ ወደ ዋሽንግተን ሂልተን ሆነ።” ዓለም በድንጋጤና በደስታ እንዲሁም ዜናውን በማጋራት ተጠመደች።
የተኩሱ መሰማት ዜና እንደሆነ አፍታም ሳይቆይ በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች እንደ X እና Telegram ላይ “ፕሬዝዳንቱ ቆስለዋል” ወይም “ተመትተዋል” የሚሉ ያልተረጋገጡ መረጃዎች በተኑ። ፕሬዝዳንቱ በሚታዩ ልዩ የጥበቃ አባሎቻቸውና በሚስጢራዊ የሴኩሪቲ ሰዎች ተከበው በፍጥነት ከመድረክ ሲወርዱ የታየው ትዕይንት ብዙዎችን ግራ እያጋባ ባለበት ቅጽበት ትራምፕ ሞተዋል የሚለው ዘገባ ቀድሞ አየሩን ሞላው።
“የአሜሪካ የጸጥታ ተቋማት ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም (April 25, 2026) በኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች እራት ላይ ተኩስ የከፈተው ግለሰብ ኮል ቶማስ አለን መሆኑን ለይተዋል። ግለሰቡ ከፍተኛ ትምህርት ያለውና እ.ኤ.አ በ2024 የዓመቱ ምርጥ መምህር ሽልማትን ማሸነፉን የሚጠቁሙ መረጃዎችም ወጥተዋል።”

ከራሳቸው የፖለቲካ ፍላጎት በመነሳት፣ እንዲሁም የትራምፕ ተቃዋሚዎች የሆኑ አጋጣሚውን “የትራምፕ የጸጥታ መላላት” አድርገው ለማቅረብ የሞከሩ አልታጡም። የፕሬዚዳንት ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው በበኩላቸው “በትራምፕ ላይ የተቃጣ ሌላ የግድያ ሙከራ” እንደሆን አስታወቁ ወይም ዘገቡ። በዚህ የስሜት ፍትጊያ ውስጥ የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ እና የሴኩሪቲ አገልግሎቱ ፕሬዝዳንቱ ምንም ዓይነት ጥይት እንዳልነካቸው፤ እንዳልቆሰሉ ይፋ አደረጉ። የተመታው አንድ የጸጥታ አባል ብቻ መሆኑን አመለከቱ።
“ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሰላም መመለሳቸውን ለማብሰር ነጩ ቤተመንግስታቸው ከተመለሱ በኋላ በሰጡት መግለጫ ላይ፣ በደህና መውጣታቸውን ጠቅሰው፤ “ብቸኛው መጥፎ ነገር የእራት ግብዣዬ መቋረጡ ነው” በማለት በቀልድ መልክ ተናግረዋል። ይህ ንግግራቸው በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ‘የጥንካሬ ምልክት’ ተደርጎ ተወስዶላቸዋል።” ዝርዝሩ ምን ይመስላል?
ተኩሱ እንደተሰማ የሚስጥራዊ ጥበቃ አባላት ፕሬዝዳንት ትራምፕን እና ባለቤታቸውን በመክበብ አፋፍሰዋቸው ወዲያውኑ ከመድረክ አስወገዷቸው። ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴትን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የካቢኔ አባላት በሆቴሉ ውስጥ ወደሚገኝ አስተማማኝ ክፍል እንዲሸሹ ተደረገ። በአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ከ2,600 በላይ እንግዶች መሬት ወለል ላይ እንዲተኙ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ባሉበት ያሸበረቀ ጠረጴዛ ስር ተኙ ወይም ተመሸጉ።
አንድ የጽጥታ አባል በጥይት ከመመታቱ በቀር ሌላ ምንም ጉዳይ ሳይከተል ትዕይንንቱ አበቃ። የተጎዳው ሴኩሪቲ በለበሰው ጥይት መከላከያ ልብስ ምክንያት ከቅርብ ርቀት ቢመታም ምንም ደም ሳይፈሰው ከሞት ተርፎ ወደ ህክምና ተላከ። ፖሊስ ወዲያውኑ ተጠርጣሪውን ኮል ቶማስ አለን የተባለ የ31 ዓመት የካሊፎርኒያ ነዋሪ መሆኑን ለየ። ግለሰቡ በወቅቱ አደንዛዥ ጠመንጃ (Shotgun)፣ ሽጉጥ እና በርካታ ቢላዎችን ይዞ እንደነበር ተናገረ።
ከጥቃቱ በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ኋይት ሃውስ ከተመለሱ በኋላ በሰጡት መግለጫ ” ሚስጥራዊ አገልግሎት እና የህግ አስከባሪ አካላት ድንቅ ስራ ሰርተዋል። በፍጥነት እና በጀግንነት እርምጃ ወስደዋል።” በማለት አመስግነዋል። አክለውም ግለሰቡን “ጠኢንነት የጎደለው ብቸኛ ተኩላ” ሲሉ ጠርተውታል።
ምንም እንኳን ፕሬዝዳንቱ ፕሮግራሙ እንዲቀጥል ቢፈልጉም፣ በጸጥታ ስጋት ምክንያት ዝግጅቱ ተቋርጦ እንግዶች እንዲበተኑ ተደርጓል። ዝግጅቱ በሚቀጥሉት 30 ቀናት ውስጥ በድጋሚ እንደሚካሄድም ቃል ተገብቷል።
ተኩሱ በተሰማበት ወቅት በአዳራሹ ውስጥ የነበሩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ታዋቂ ጋዜጠኞች እና ባለስልጣናት በአንድ ላይ ሆነው በጠረጴዛ ስር ተደብቀው የነበረበት ትዕይንት እጅግ አስገራሚ ነበር። በተለይ የቀጥታ ስርጭት ሲያስተላልፉ የነበሩ ጋዜጠኞች ካሜራቸውን ሳይዘጉ ሁኔታውን ለመዘገብ የሞከሩበት ድፍረት ለታሪክ የሚቀመጥ ትዕይንት ሆኖ አልፏል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ “ብቸኛው ተኩላ፣ በሽተኛ” ያሉት የ31 ዓመቱ ኮል አለንን የቶራንስ፣ ካሊፎርኒያ (Torrance, California) ነዋሪው ግለሰብ ከፍተኛ ትምህርት ያለው ሲሆን፣ በካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ (Caltech) በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን እንዲሁም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪውን አግኝቷል። በሙያው አስተማሪ ሲሆን የቪዲዮ ጌም አልሚ (Game Developer) እንደነበር የግል ማህደሩ ያስረዳል።
ተጠርጣሪው ወንጀሉን ለመፈጸም የተነሳሳበት ዝርዝር ምክንያት እስካሁን በይፋ ባይገለጽም፣ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት የመንግስት ባለስልጣናትን ለመግደል አስቦ እንደነበር ለፖሊስ መናገሩ ተዘግቧል። በተያዘበት የተገዳዮች ዝርዝር ውስጥ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ጭምሮ ሌሎች ባለስልጣናትና ጋዜጠኞችም ይግኙበታል።
አቃቤ ህግ በግለሰቡ ላይ ሁለት ዋና ዋና ክሶችን መመስረቱ ተሰምቷል። በጥቃት ወቅት የጦር መሣሪያ መጠቀም። በፌዴራል የጸጥታ አካል ላይ በከባድ መሣሪያ ጥቃት መፈጸም። የሚሉት ክሶች ቀርበውበታል።
በአሁኑ ወቅት ፖሊስ በካሊፎርኒያ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤቱን እየበረበረ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ከማንኛውም የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት እንደነበረው የሚያሳይ ማስረጃ እስካሁን አልተገኘም። ግለሰቡ የጥቃቱ ሰለባ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ዝርዝር ይዞ እንደነበርም አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






