የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። ምርመራው ቀጥሎ ማስተባበያው ሃሰት ከሆን የከፋ ቀጣት ይጠበቃቸዋል።

ባለፉት ጥቂት ወራት የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ የኢልሀን ኦማር እና የባለቤታቸው ቲም ማይኔት ሀብት ከ51,000 ዶላር ወደ 30 ሚሊዮን ዶላር በድንገት ማደጉን ያሳዩ ነበር።

ይህ የ3,500 በመቶ ጭማሪ በሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት እና በተለያዩ ተቋማት ዘንድ “ይህ ገንዘብ ከየት መጣ?” የሚል ጥያቄና ምርመራ አስነሳ።

በዚህ ሳምንት ሚያዝያ 21/2026 የኢልሀን ኦማር ጽህፈት ቤት በሰጠው መግለጫ፣ ቀደም ሲል የቀረበው ሰነድ የተሳሳተ መሆኑን አስታወቀ። እንደ መግለጫው ከሆነ፦
የስህተቱ አይነት፦የባለቤታቸው ኩባንያዎች ያላቸውን ጠቅላላ ንብረት እንጂ ያለባቸውን ዕዳ (liabilities) ሳይቀንስ በመመዝገቡ የመጣው ስህተት ሀአብታቸውን ከ30 ሚሊዮን በላይ አደረገው።

ጩኸቱ ከበረከተ በኃላ አሁን በተስተካከለው መረጃ መሠረት፣ የኢልሀን ኦማር እና የባለቤታቸው አጠቃላይ ሀብት በ18,004 እና በ 95,000 ዶላር መካከል ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

የጽህፈት ቤቱ ቃል አቀባይ “ኢለሃን ሚሊየነር አይደለችም፤ እንዲያውም እስካሁን ያልተከፈለ የተማሪ ብድር አለባት” በማለት ወሬውን ለማስተባበል ሞክረዋል።

ምንም እንኳን የኢልሀን ኦማር ወገን “ስህተቱ ታርሟል” ቢልም፣ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪዎች ግን “30 ሚሊዮን ዶላር እንዴት በስህተት ይመዘገባል?” በሚል ጥርጣሬያቸውን እየገለጹ ነው። የምክር ቤቱ የቁጥጥር ኮሚቴ (House Oversight Committee) ጉዳዩን በጥልቀት መመርመሩን እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አሜሪካና ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ምን እያሰቡ ነው? “አሜሪካ የኢትዮጵያን የባህር ፍላጎት ማሳካት ህልውናዋ ነው”

ኢትዮጵያ የቀጥታ የባህር ዳርቻ ባይኖራትም፣ በወታደራዊ አቅሟ እና የባህር...

“የአሜሪካና ኢትዮጵያ ወዳጅነት አደገኛ ነው፤ ከማን ጋር እንደምንዋጋ አልገባንም፤አሳልፋ ልትሰጠን ትችላለች”

አዲስ ሪፖርተር - በአገር ቤት ሕዝባዊ አመጽ ለማነሳሳት የተደራጀው...

ኤርትራ ለህወሃት መሪዎች የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የመስጠት ስምምነት አገደች

አዲስ ሪፖርተር - የኤርትራ መንግስት ለህወሃት አመራሮችና ከፈተኛ ወታደራዊ...