የወደፊቱን ትውልድ የማዳን ጥሪ ለትግራይ – “13ኛ አሃድ አሁን ላይ የለም፤ 500 በላይ ቁስለኞችን የአገር መከላከያ እያከማቸው ነው” ብ/ጄ ገብረእግዚሕአብሔር በየነ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – አጥፊው ቡድን በከፈተው አላስፈላጊ ውጊያ ምክንያት “13ኛ አሃድ” በመባል የሚታወቀው ዋና የጦር ክፍል ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ መሆኑንና አሁን ላይ በሕይወት አለመኖሩን ብርጋዴር ጄኔራል ገብረእግዚአብሔር በየነ (ወዲ እንጥሩ) አስታወቁ።

እጅግ አስከፊ በሆነው የውጊያ ሂደት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት ይህ ኃይል፣ በአሁኑ ወቅት የተበተነ ሲሆን ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑት ቁስለኞች በኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት ሙሉ ሕክምናና እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ጄኔራሉ ገልፀዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ገብረእግዚአብሔር በየነ የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የመሣሪያዎች ሚና ከፍተኛ ተጽዕኖ በታየበት በዚህ ውጊያ፣ ጦሩ በእግር እየተጓዘ ሲዋጋ በመመታቱ የደረሰበት ጉዳት እጅግ ከፍተኛና አሰቃቂ የሚባል እንደነበር አመልክተዋል።

ቀደም ሲል በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ በርካታ አባላት የነበሩት ይህ ስብስብ፣ በስህተት አመራርና በዕውር ድንብሩ ውጊያ ምክንያት ተደምስሶ በአሁኑ ወቅት ጥቂቶቹ ብቻ መቅረታቸውን ያመለከቱት ጄኔራሉ፣ ለዚህ ሁሉ ጥፋት አሁን ትግራይን እየመራ ያለውን ቡድን ተጠያቂ አድርገዋል።

በውጊያው መካከል የተረፉትና የቆሰሉት አባላት ወደ መከላከያ ሠራዊት እየመጡ የሚገኙ ሲሆን፣ ሠራዊቱም ሰብዓዊነቱን በማስመስከር ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑትን ቁስለኞች በግንባር ቀደምትነት እያከመና እያስተናገደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

“የወደፊቱን ትውልድ ለማዳንና የሕዝቡን እንግልት ለማስቆም ከግጭት ይልቅ ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለስ ብቸኛው አማራጭ መሆኑን የጠቆሙት ጄኔራሉ፤ በየአካባቢው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ይህንን አደጋ ተረድተው የሕዝቡን ስቃይ የሚያስቆም ትክክለኛ ውሳኔ ላይ መድረስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ከዚህም በኋላ በክልሉ የሚደረግ ማንኛውም ጦርነት የትግራይ ሕዝብን ጥያቄ ለመፍታት ያለመ አለመሆኑን ጠቅሰው፤ ‘የጥፋት ጦርነት አይበቃኝም፤ እዋጋለሁ፣ እረብሻለሁ’ የሚለው የሕወሓት ቡድን ሕዝቡን ላለፉት መከራዎች ዳርጓል” ሲሉ ቡድኑ ከትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ጋር መቆሙን ሃፍረት መሆኑን ገልጸዋል።

«ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን ጦርነት የመረጠው አቅዶበት ሳይሆን ማመዛዘን አቅቶት ነው» ያሉት ጄኔራሉ፤ ቡድኑ ከጦርነት በኋላ የሚመጣው ኪሳራ ጠፍቶት ሳይሆን፣ ሰላም ቢሰፍን ተጠያቂ እሆናለሁ የሚል ሥጋት ስላለበትና በባሕሪው ያለጦርነት መኖር ስለማይችል መሆኑን በመግለጽ ጦርነት የተመረጠበትን ምክንያት አስረድተዋል።  

በተካሄዱ ውጊያዎች በተሳተፉ ተዋጊዎች ላይ የሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን ገልጸዋል። ታሪክ መሆኑን በመጠቆም ትኩረታችን ትውልዱን ማዳን ላይ መሆን አለበት ብለዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አገር መከላከያ መቀሌ ከተማ አቅራቢያ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ህወሃት ገለጸ፤ ገለልተኛ አካል አልረጋገጠም

አዲስ ሪፖርተር - የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌ ከተማ...

እነ ክርስቲያስን ላይ ዘመቻ ሊከፈት ነው፤ ሰነዱ ላይ በመፈረም ይቅርታ መጠየቃቸው ተሰማ፤

አዲስ ሪፖርተር — ከአማራ ክልል ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ...

ግብጽ በኤርትራ በኩል በጀት ለቀቀች፤ አዲስ የትግል ስልት ተጀመረ፤ ኦሮሚያን ለማበጣበጥ ሰነድ ተዘጋጀ፤

ኦሮሚያ እስካልተረበሸ ድረስ የዲፕሎማሲ ጫና መፍጠር አንችልም። ስለዚህ ኦሮሚያ...

በአዲሱ መንግሥት የባለሥልጣናትና የካቢኔ ሹም ሽር ይካሄዳል፤ ሌብነት ዋና አጀንዳ ነው፤

አዲስ ሪፖርተር፦ "አሁን አሁን በአዲስ አበባም ሆነ በኢትዮጵያ ደረጃ...