በሶማሌ ክልል ለሽብር ተግባር አባላትን እንዲመለምል የተመደበው የጅግጅጋ ተወላጅ በሚሊዮን ዶላር ተቀብሎ ጠፋ፤ ዜናው ውዝግብ አስነስቷል

Date:

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — ከሶማሌ ክልል የሚነሳ የሽብር ኃይል እንዲያደራጅ ተመርጦ ከፍተኛ ገንዘብ የወሰደው የጅግጅጋ ተወላጅ ራሱን መሰወሩ ተሰማ። ስሙና አድራሻው የሚታወቀው ይህ ሰው ሞቃዲሾ ደርሶ ገንዘብ ከተላለፈለት በኋላ መሰወሩ በመልማዮቹ ዘንድ ከፍተኛ ንትርክና አለመግባባት ፈጥሯል።

ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስት ጋር የቅርብ ወዳጅ ነው የተባለው የጅግጅጋ ተወላጅ ለዚህ ተግባር የተመለመለው ህወሃት በፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ክንፍ በኩል በሶማሊያ እየተዘረጋ ባለው መዋቅር አማካይነት እንደሆነ የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ የዘወትር የመረጃ ምንጮቹን ጠቅሶ አስታውቋል። ፕሮፌሰሩ በተመሳሳይ ስራ ሞቃዲሾ፣ ቱርክና ናይሮቢ እንደሚመላለሱ የሶማሊላንድ አክቲቪስቶቭ “ኢትዮጵያዊያን ንቁ” በማለት በተደጋጋሚ ለአዲስ ሪፖርተር መረጃ መላካቸውን አመልክተን ዘግበን።

ተባባሪያችን እንዳለው አዲስ በተፈጠረው “ጽምዶ” የተሰኘ ጥምረት “የአገር መከላከያን በግንባር መግጠም ኪሳራው ስለሚበዛ፣ በደፈጣ ጥቃት ለማጥቃት በየክልሉ በሚመለመሉ ጥቃት ሰንዛሪዎች ማዳከም” እንደ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በሰላማዊ ትግል ስም እነ አቶ ልደቱና አቶ ነዓምን ተጣምረው የሚመሩት የትርምስ አመቻች ጋራ መድረክ ላይ ከደቡብ፣ ከሶማሌ ክልል፣ ከአፋር፣ ከጋምቤላና ከቤኒሻንጉል ወዘተ የተወከሉ ውጤታማ ስራ እየሰሩና በመሬት ላይ አጥጋቢ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን የህወሃት ተወካይ ከሆኑት መካከል አቶ አባይ ግደይ መናገራቸውን ጠቅሰን ዘግበን ነበር። በዚህ ዜና ላይ የህወሃት ኃይልም ወደ ሙሉ ውጊያ ለመዘዋወር ለድሮን ጥቃት እንዳይጋለጥ በጋማ ከብት ከባድ መሳሪያና ሎጂስቲክ ወደ ተመረጡ አካባቢዎች እያንቀሳቀሰ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

ይህ መረጃ ከተሰማ በኋላ በሸረሪና፣ መረዋ እና በተለያዩ አካባቢዎች በህወሃት የመሳሪያ ክምችትና ኮምቦይ ላይ ተከታታይ ጥቃት መፈጸሙ፣ ህዝብ የወትሮውን ድጋፍ በመከልከሉ፣ ወደ ቀድሞው የትግል ዘመን አድፍጦ ማጥቃት እና ቁልፍ የመገናኛ አውታሮችን የመምታት ዕቅድ መያዙን መረጃው ያላቸውን የጋራ መደረኩን አባላት ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

በጥምረቱ ውስጥ አባል የሆነው የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ተዋጊም ሆነ ደጋፊ ስለሌለው አዲስ የሽብር ስራ ላይ ያተኮረ ኃይል መገንባት በሚል በተያዘው ዕቅድ ከጅግጅጋ ተመልምሎ ለስራው ማስፈጸሚያ ከተያዘለት ከበጀት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆተር ገንዘብ በውጭ ምንዛሬ ወስዶ የተሰወረው ሰው ለጊዜው የት እንዳለ ዜናውን ያጋሩት አላስታወቁም። የገንዘቡን መጠንና ገንዘቡ እንዴት እንደተዘዋወረ ለጊዜው ይፋ ላላደረጉም። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ብር ሃያ ስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ቀደም ሲል እንደተሰጠው እንደሚያውቁ የዜናው ባለቤቶች አመልክተዋል።

ከአፋር አቅጣጫ ከሚደራጀው የጥፋት ኃይል ጋር በመቀናጀት የኢትዮ ጅቡቲን የባቡር መስመር መቁረጥ ወይም በማጥቃት ማስተጓጎል፣ ተሽከርካሪዎች ጭነት እንዳያመላልሱ እክል መፍጠር የሚለውን የስራ መመሪያ እንዲያስፈጽም የተመለመለው ይህ የጅግጅጋ ተወላጅ መኮብለሉን ወደ ኤርትራ የሸሸውና ሻዕቢያ ያደራጀውን የአፋር አማጺ መሪ በተዛዋሪ ለአዲስ ሪፖርተር አረጋግጧል። በተዘረፈው ገንዘብና በመልመላው ዙሪያ የተነሳውን ውዝግብና ግጭት አዲስ ሪፖርተር ሙሉ መረጃውን አጠናክሮ ያቀርባል።

በተመሳሳይ የዋሽንግቶን ተባባሪያችን እንዳለው የጋራ መደረኩ ባለፈው ረቡዕ ባደረገው ስብሰባ ሻዕቢያ በግብጽ ተቆጣጣሪነት የሚመራው ጽምዶን አስመልክቶ የተለያየ አቋም ተይዟል። “ኢትዮጵያ ላይ ያላቸው አቋም አይታወቅም” በሚል የግልጽነትና የዓላማ አንድነት እንደሌለ በማመልከት ክርከር በተነሳበት በዚህ ስብሰባ አቶ ነዓምን ምንም አልተነፈሱም።

የሃሳብ ልዩነት በተነሳበትና ኦሮሞን እንወክላለን የሚሉት አካላት ሙሉ በሙሉ መገኘት ባቆሙበት በዚህ ስብሰባ፣ ጽምዶ መንግስት ከገለበጠው በኋላ ስለሚያከናውነው ተግባር በግልጽ እንዲያስረዳ፣ የጋራ መድረኩም በጽምዶ ላይ የተነሳውን ተቃውሞ ለማርገብ የፕሮፓጋንዳ ስራ እንዲሰራ ሰብሰቢው ተናግረዋል። በጋራ መደረኩ ላይ ፕሮፌሰር ህዝቅዔል የህወሃት ተወካይ ከሆኑት መካከል አዘውትረው ሱዳን በሚመላለሱት አቶ አባይ ግደይ እንደሚወከሉ በይፋ መገለጹን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። ይህ ሲዘገብ ፕሮእፌሰሩ “ማን ነው ለአዲስ ሪፖርተር መረጃ የሚሰጠው” በሚል በውስጥ የግንኙነት መስመራቸው ላይ የሰላ ተቃውሞ መስንዘራቸው አይዘነጋም። በዚህ መነሻ እሳቸው ባይገኙም ወኪላቸው በስብሰባው ስለሚገኙ በጋራ መደረኩ የኦሮሞ ይተወላጆች ሸሹ የሚለው ዜና እሳቸውን አይመለከትም።

በተደጋጋሚ በአዲስ ሪፖርተር እንደተዘገበው፣ አቶ ልደቱ አቶ ጃዋር ስልክ እንደማያነሱላቸው በመጥቀስ የሚቀርቧቸው ስብሰባውን እንዲካፈሉ እንዲያደርጉ ተማጽነው ነበር። ይህንኑ ዜና የሚያረጋግጥ መረጃ ሰሞኑን የሰጡት አቶ ልደቱ “ጃዋር ስልክ አያነሳልኝም፣ አዲስ አበባም እያለን ቤቱ ቀጥሮኝ ስሄድ ተፈትሼ፣ ስልኬን ተቀምቼ ነበር የማገኘው” በማለት በምሬት ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዐት ጽምዶ ውስጥ አለበት የሚባለው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ጦር ቃል አቀባይን ጨምሮ አንድም የኦሮሞ ተወላጅ በጋራ መደረኩ ሰብሰባ ላይ እንደማይገኝ የዋሽንግቶን ተባባሪያችን አመልክቷል።

ፎቶው በኤአይ የተሰራ

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ፋኖን ፍርሃቻ የአማራ እናቶች እንጀራ በሌሊት ይጋግራሉ” ፋኖ ሻዕቢያ በላካችው አስራ አንድ አመራሮችን ይመራል

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — አማራ ክልል የትጥቅ እንቅስቃሴ...

“የኦባሳንጆ የትግራይ ምልልስ በጽምዶ ውስጥ ያሉትን ቡድኖች ጥርጥር ውስጥ ከቷል”

ህወሃት አሁን ላይ በራሱ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም። በቅርቡ...

የቻይናና ግብፅ ባለ21 ነጥብ ስምምነት…የናይል ውኃና የቀይ ባሕር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ምን መልዕክት አለው?

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ —  የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ...

ኤፍሬም ማዴቦ “ጽምዶ ኢትዮጵያን መንግሥት አልባ ያደርጋል” ያሉበት ሚስጢር ታወቀ፤

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ —  ኤፍሬም ማዴቦ “ሀገሬ እንደ...