“የቅንጅት ሊቀ መንበር ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል ዘጠና ዘጠኝ ከመቶ ልደቱ ወያኔ ነው ብለው ደጋግመው ነገረውኝ ነበር፤ ይህንኑ እውነት እኔም እመሰክራለሁ” አንጋፋ የኦሮሞ ፖለቲከኛ

Date:

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — “ልደቱ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ ወያኔ ነው” በማለት የቀድሞ የቅንጅት ሊቀመንበር ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል ነግረውኝ ነበር ሲሉ ስማቸውን ለጊዜው መናገር ያልፈለጉ አንጋፋ የኦሮሞ ፖለቲከኛ አስታወቁ።

“”የቅንጅት ሊቀ መንበር ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል ዘጠና ዘጠኝ ከመቶ ልደቱ ወያኔ ነው ብለው ደጋግመው ነገረውኝ ነበር” በማለት ሟቹ የቅንጅት ሊቀመንበር ኢንጂነር ኃይሉ ልደቱን እየጠራጠሩ እንደተቀበሉት ያስታወሱት አንጋፋው ፖለቲከኛ “አሁን እሳቸውም አልፈዋል። እኛም ሸምግለናል። ልደቱም በቀድሞ ማንነቱ ቀጥሏል” በማለት የልደቱ አለመቀየር እንደገረማቸው አመልክተዋል። “ዛሬ እኔ ሽማግሌ ነኝ ይህንኑ እውነት እኔም እመሰክራለሁ” ብለዋል

“ሰማይ አንቀጥቅጥ” የተባለ የበይነ መረብ ሰላማዊ ሰልፍ በጠራበት ወቅት አሁን ለተፈጠረው “ጥምር” (ወይም ጽምዶ) እንዳጫቸው የተናገሩት ፖለቲከኛ “ልደቱ እኔም ዘጠና ዘጠኝ በመቶ አላምንህም” በማለት ኢንጂነር የነገሩዋቸውን በማስታወስ ጥያቄውን ሳይቀበሉ መቅረታቸውን አመልክተዋል።

እነ ልደቱ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ተደብቀው የጀመሩት ጥምረት ዴሞክራሲና ነጻነትን የማያጎናጽፍ ስብስብ እንደሆነ ለመረዳት ነቢይ ወይም ፖለቲከኛ መሆን እንደማያስፈልግ ያመለከቱት አንጋፋው ፖለቲከኛ፣ የስብሰቡ አባላት ተፈጥሮና የተግባር ተሞክሯቸው እንደሚያመሰክርባቸው ተናግረዋል።

“ነጻ እናወጣዋለን፣ የሚሉትን ሕዝብ በየአቅጣጫው መከራ ውስጥ የከተቱ ታጣቂዎች፣ በመንግስትነት ሃያ ሰባት ዓመት ተሞክሮ የወደቀ አፋኝ አገዛዝ፣ አገር ብሎ ኤርትራን ከመሰረተ በኋላ ህዝቡ ላይ ከርችሞ ወደ ጋርዮሽ የመመለሰ መንግስትና በዚሁ አገዛዝ ስልጠናና መመሪያ የተደራጁ ታጣቂዎች እገሌ ከገሌ ሳይባሉ እንዴት ዴሞክራሲና ነጻነትን ለህዝብ ያጎናጽፋሉ” በማለት የሚጠይቁት እኚሁ አንጋፋ ፖለቲከኛ “በዚህ ሁሉ የስብስቡ ማንነት ላይ ልደቱ ሲታከልበት የሚያስተውል አብዝቶ ይሸሻል እንጂ አይጠጋም”ብለዋል።

በቢሯቸው የነበሩ ሌላ ባልደረባችን፣ “ሱዳን ፈራርሳለች፣ ሶማሊያ የጎበዝ አለቃ መፈንጫ ሆናለች፣ ደቡብ ሱዳን በወጉ መንግስት መሆን አቅቷት በዜጎቿ ህይወት እየተጫወተች ነው። ኤርትራ የአንድ ሰው መቀለጃ ሆና የድንጋይ ዘመን ምሳሌ ሆናለች፣ ህወሃት ትግራይን የመከራ ምድር አድርጓታል። ፋኖ አማራ ክልልን ወዶና ፈቅዶ እያፈረሰ፣ ህጻናትን አደንቁሮ ክልሉን ኤርትራን እያስመስለው ነው፣ ኦላ የራሱን ህዝብ ሳይቀር እያሰቃየ፣ እንደ ፋኖ ያልቀለበውን ሰንጋና ሙክት እያረደ የሚበላ…” እነዚህ ተጣምረው ለኢትዮጵያ ምን ሊያመጡ ነው በማለት ጽሁፋቸውን ይቅርታ ጠይቀው አክለዋል።

በመካከል የገቡት አስተያየት ሰጪ እንደጨረሱ “ልደቱ ከህብረት ወደ ቅንጅት ሲያመራ ቅንጅትን እንደሚያፈርሰው ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል ያውቁ ነበር። ችግር የሆነው ስብስቡ ተማምኖ ለመደማመጥ ጊዜ ያልነበረው የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት በመሆኑ እያወቁ የፈሩት እንደደረሰ አመልክተዋል።

“ልደቱ አያሌው እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ በማለት በቲቪ፣ በጋዜጣ፣ በመጽሐፍት፣ በዩቲዩብ ቻናሎች፣ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ በራሱ እጅ በተጻፉ መከራከሪያዎች የወንጀል አጠባ ቢያካሂድም ሕዝብ ስም ሰጥቶታል። ስሙንም ሊቀይርለት ስላልቻለ ዩቲዩብ ከፍቶ ለመደጎሚያ ዘፍኗል” በማለት አንጋፋው ፖለቲከኛ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ፅምዶ ሻጭና ገዢ የተገናኙበት ገበያ መሆኑን ብ.ጄ ፍስሃ ማንጁስ አስታወቁ፤

​አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — ”ከሁሉም በላይ ትግላችን አጠናክረን...

ጽምዶ የደረሰበትን ተቃውሞ ለማለሳለስ ህወሃት ለተዋጊ ኃይሉ ያዘጋጀው የመወያያ ሰነድ፤ እንደወረደ

በህወሓት የፖለቲካዊ ጉዳዮች ማዕከል ተዘጋጅቶ ለውይይት የቀረበው “ጽምዶ/ጥምረት” የተሰኘ...

ጽምዶ ኢትዮጵያን ሶስት አገር የሚያደርግ ዕቅድ አለው፤ “ዩጎዝላቪያን የበተኗት እንደዚህ ነው”

“ሻዕቢያን የሚያክል ጠላት ከጀርባችን አስቀምጠን፣ አማራ የሚያክል ህዝብ በጠላትነት...

በሶማሌ ክልል ለሽብር ተግባር አባላትን እንዲመለምል የተመደበው ገንዘብ ዘርፎ ጠፋ

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — ከሶማሌ ክልል የሚነሳ የሽብር...