ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዴት ተቋረጡ? እንዴትስ እንዲጀምሩ ተወሰነ?

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ላለፉት አምስት ቀናት የተቋረጠው የአየር ትራንስፖርት በትግራይ ሰላማዊ ሕዝብ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ የፈጠረው ቀውስ በቀላሉ አይገለጽም። መነሻ ምክንያቱ ጦርነት በመሆኑ የትግራይ ሕዝብ የተጠየፈው አክሳሪ ጦርነት ዳግም እንደሚቀጣጠል ምልክት አድርጎ ወስዶት ነበር። ከባንክ አገልግሎት መስትጓጎል ጋር ተዳምሮ ጦርነት ዳግም ትግራይን ሊያደቃት እንደሆነ የሰጉ አሁን ላይ መልካም ዜና ሰምተዋል። የመቀለ ተባባሪያችን እንዳለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ዛሬ እንደሚጀመር መገለጹ እረፍት እንዲሰማቸው አድርጓል።

ከማክሰኞ ጥር 26 ቀን 2018 ጀምሮ ዳግም በሚጀመረው የበረራ አገልግሎት ለመስተናገድ የቲኬት ሽያጭ ተጀምሯል። የመቅለ ተባባሪያችን እንዳለው በድንገት በረራ በመቋረጡ መጉላላት የገጠማቸው ሻንጣቸውን ሸክፈው ዛሬን እየጠበቁ ነው።

አየር መንገድ እንዴት በረራውን አቋረጠ?

ከታህሳስ ጀምሮ በስፋት ሲሰራጭና ቀጠሮ ሲሰጥበት የነበረው ወልቃይትን መልሶ የመረከብ ዕቅድ ተግባራዊነቱ ጥር 18/2018 ጀምሮ “ፅንፈኛ” የሚባለው የትህነግ ቡድን በተለያዩ አቅጣጫዎች በከፈተው ጦርነት ተጀመረ። በዘፈንና ቀረርቶ “ሽሬ ደህና ሁኚ፣ እናመስግናለን” በሚል በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያሉ እናቶች እያስጨፈሩ ቅስቀሳ የጀመሩት የትህነግ የጦር መሪዎችና ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተናበው የከፈቱት ጦርነት ከውጭና ከውስጥ ተናባእው በሚሰሩ ሚዲያዎች ተወደሰ። “ውሮ ወሸባዬ” ተባለለት።

ጥቂት የፅንፈኛ አመራሮች በታጣቂ ሃይል በመታገዝ ከትጥቅ እንቅስቃሴ ነጻ ሊሆን በሚገባው የአየር መነገድ መሰረተልማት ላይ ታጥቂዎችን አፈሰሱ። ባሰፈሯቸው ታጣቂዎቻቸው አማካይነት የሲቪሊያን መጓጓዣዎችን ዒላማ ያደረገ ጫና ለመፍጠር ተንቀሳቀሱ፤ ይህን ተከትሎ አየር መንገዱ በረራውን አቆመ። ዳፋው ለሕዝብ ሆነ።

በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት በዓለም ዓቀፍ ህግም ሆነ በማንናውም አግባብ ለተሳፊሪዎች ደኅንነት አመቺ ባለመሆኑ ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የክልሉ መሪ እንደመሆናቸው መላ እንዲፈልጉ ተጠየቁ። እሳቸውን “ጄነራሎቹ አይታዘዙም” በማለት አምታቱ። አብረው እየዶለቱ ራሳቸውን ንጹህ ለማስመሰል የሚላላጡት ታደሰ ወረደ በዳግም የጦርነቱ ክተት ውስጥ አለመነከራቸውን ለማሳየት “አዲስ አበባ ለመሄድ የያዝኩት ዕቅድ በበረራ መሰረዝ የተነሳ ተስትጓጎለ” በማለት በሚቀርቧቸው ሚዲያዎች በኩል አለቃቀሱ።

በአየር መንገድ አሰራር እና የደኅንነት መርህ መነሻ፣ በጦርነት ቀጠና ውስጥ የአቪኤሽን ደኅንነትን ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ፣ የኢትዮጵያን አየር መንገድ በትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎችን አቋርጠ። ቅድሚያ ደህንነት ነውና አየር መንገዱ ዓለም ላይ ያሉ አቻ ተቋማት እንደሚያደርጉት ውሳኔው ለማንም ወገን ግልጽና ትክክል ነበር።

አየር መንገዱ እንዴት በረራ ለመጀመር ወሰነ

አየር መንገድ በረራ ካቋረጠ በኋላ በዋናነት የተወሰዱ እርምጃዎች ሶስት እንደሆኑ ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ተናግረዋል። ለዳግም ጦርነት ቃታ ጎትቶ በተለያዩ አቅጣጫዎች ጦርነት የከፈተውን “ጽንፈኛ” ኃይል መመከት፣ በንግግር ይህ ኃይል ከጀመረው የውክልና ጦርነት በአስቸኳይ እጁን እንዲሰበስብ፣ አመራሩ በአደባባይ ለሕዝብ ሃቁን እንዲናገር ማድረግ።

ጦርነት የለኮሰው ኃይል በአገር መከላከያ አማካይነት “ተገቢና አስተማሪ” የተባለ ምላሽ ከተሰጠው በኋላ ነው። በትግራይ ግጭት እያወጁና በየአቅጣጫው ጦርነት እየከፈቱ ያሉት የሻዕቢያና ግብጽ ተላላኪ ጄኔራሎች አስተዳደሩን እንደማይሰሙና አስተዳደሩ ጦርነቱን እንደማይፈልገው በይፋ ለሕዝብ እንዲያሳውቁ መመሪያ የተሰጣቸው ታደሰ ወረደ አደባባይ የወጡት።

በወቅቱ አዲስ ሪፖርተር በደረሰው መረጃ እንዳለው አየር መንገድ የተለመደውን በረራ ለመጀመር ታደሰ ወረደ በአደባባይ ዋስትና እንዲሰጡም ታዘው ነበር። መንግስት ቁርጠኛ አቋም በመያዝ ማሳሰቢያ የሰጠበት ሌላ ጉዳይ በትግራይ የአየር ማረፊያዎች ውስጥ እንዲሰፍሩ የተደረጉ የትሀንግ ታጣቂዎች በአስቸኳይ ወደ ሚቀመጡበት ካምፕ እንዲመለሱ እንዲደረግ ነበር።

በጦርነት ግንባር እንዳልተሳካ መረጃ የቀረበላቸው ታደሰ ወረደ፣ “የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መሪ ከሆኑ፣መደበኛ በረራ እንዲጀመር እንደ መንግስት ዋስትና ስጡ” ለተባሉትና፣ በአየር ማረፊያዎች ውስጥ ያሰማሩትን ታጣቂ እንዲያስወጡ በታዘዙት መሰረት መስማማታቸውን አስታወቁ።  

ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ይህንኑ  በገቡት ቃል መሰረት ተግባራዊ ማድረጋቸው ሲረጋገጥ፣ አየር መንገድ በረራ ቢጀምር ስጋት እንደማይገጥመው በመታመኑ በረራው ከዛሬ ጀምሮ እንዲጀመር ተወሰነ።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ በኃይል ከስልጣን በተነሱት አቶ ጌታቸው ረዳ እግር ሲተኩ “ትህነግ ከሻዕቢያ ጋር የጀመረውን ከሕገ መንግሥቱን እና ከሀገር ሉዐላዊነት፤ ያፈነገጡ ግንኙነቶችን እንዲአስቆሙ ኃላፊነትን የሚጥልባቸው የቃል ኪዳን ሰነድ በዓለም ዓቀፍ ታዛቢዎችና ዲፕሎአቶች ፊት መፈረማቸው ይታወሳል።

“ፅንፈኛ” የሚባለው ኃይል ለጀመረው የትንኮሳና የውክልና ጦርነት አስተማሪ እርምጃ መወሰዱን ለኦፕሬሽኑ ቅርብ የሆኑ ወገኖች አመልክተዋል። አስተማሪ ከተባለው እርምጃ ጋር በተያያዘ በዚሁ “ጽንፈኛ” በተባለ ኃይል ላይ ስለደረሰው ጉዳትና ኪሳራ ወደፊት በይፋ እንደሚገልጽ ያስታወቁት ክፍሎች እንዳሉት፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ በክልሉ ለተፈጠረው ችግር መሉ ኃላፊነት ወስዷል። ተመሳሳይ ጥፋት እንደማይደገም በፅሑፍ አረጋግጧል። ይህ “ጽንፈኛ” ኃይል በተደጋጋሚ ሽንፈት ሲደርስበትና ያሰበው ሲከሽፍበት መዋሸት፣ የመተንፈሻ ጊዜ ለመውሰድ አጣዳፊ ስምምነቶችን መፈጸም መለያ ተግባሩ እንደሆነ ቢታወቅም፣ ከዚህ በኋላ ከመወራጨት ያለፈ ኃይል ስለሌለው ለህዝብ ሲባል ውሳኔው መተላለፉን ለመረዳት ተችሏል።

ምንም እንኳን ይህ ኃይል ከህዝብ እየተለየና በመፈረካከስ ላይ ያለ ቢሆንም፣ በክልሉ ያለው የጸጥታ ስጋት ሙሉ ለሙሉ አልተወገድም። ይህ ቡድን ከስህተቱ የማይማር፣ ለሕዝብ ደንታ የሌለው፣ እንደሆነ ቢታወቅም ፣ የትግራይ ህዝብ የአየር በረራ አገልግሎት የማግኘት መብቱን ከማረጋገጥ አንጻር አሰተዳደሩ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ውል ገብቶ አገልግሎቱ ክፍት እንዲሆን ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጀምር ሲፈቀድ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሊያደርግ ቃል የገባውን ማጓደል እንደማይቻል፣ በዚህም መንግስት እንደ ከዚህ በፊቱ እንደማይለሳለስ በጥብቅ መገለጹ፣ እርምጃው የት ድረስ ሊሆን እንደሚችል ማስታወቁን አዲስ ሪፖርተር ከታማኝ የመረጃ ምንጮች አረጋግጣለች።

የአዲስ ሪፖርተር የመቀለ ተባባሪ ኤርፖርት ሰፍሮ የሚገኘውን አርሚ 22 ታጣቂዎች መሆናቸውን ባለፈው እሁድ አረጋግጧል። ታደሰ ወረደ ይህን ታጣቂ ኃይል ከአየር ማረፊያው እንደሚያነሱ በደብዳቤ ቀን ቆርጠው ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኦፕሬሽን እና አገልግሎት ላይ የሚደረግ ጫና እና ጣልቃገብነትን ሙሉ ለሙሉ እንደሚያስወግዱ ተስማምተዋል። ሙሉ መተማመኛም ሰጥተዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኦነግ/ኦነስ በቄለም ወለጋ በሴቶችና ህጻናት ላይ የፈጸማቸው ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች “የጦርወንጀል” እንደሆነ ተገለፀ

አዲስ ሪፓርተር- አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው አዲስ መግለጫ በቄለም ወለጋ...

ሻዕቢያ እንደትላንቱ መስሎት እንዳይስት አብይ አሕመድ መከሩ፤ “ሻዕቢያ ማጥቃት ከሞከረ የመጨረሻው ይሆናል”

አዲስ ሪፖርተር - ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከዲያስፖራ ሰፈር የሚሰራጨው...

ስምረት ፓርቲ የጠ.ሚ አብይን ቃለ ምልልስ ተከትሎ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ ሰጥቷል አለ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም፣...