ባይቶና የምርጫ ቦርድን ውሳኔ በሕጋዊ፣ ፖለቲካዊና ሰላማዊ አማራጮች ሁሉ እቃወማለሁ አለ

Date:

  • አዲስ ሪፖርተር – ባይቶና አባይ ትግራይ “ተቀባይነት የለውም” ሲል የተቃወመውን የምርጫ ቦርድ ውሳኔ “በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የመጣውን ያልፀና ሰላም አደጋ ላይ የሚጥልና የትግራይ ህዝብና መንግሥት ሕገ-መንግሥታዊ አንድነትን የሚፈታተን በመሆኑ ይህንን ውሳኔ ለመቃወም ያሉትን ሕጋዊ፣ ፖለቲካዊና ሰላማዊ አማራጮች እንጠቀማለን” ሲል አሳሰበ። ሙሉ መግለጫውን ያንብቡ፤

“ተቀባይነት የለውም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “አወዛጋቢ” ብሎ በጠራቸው የትግራይ የምርጫ ክልሎችን ኣስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ከብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) የተሰጠ መግለጫ

ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) በሑመራ፣ ዓዲ ረመፅ፣ ፀለምቲ፣ በኮረም ኦፍላ እና በራያ አላማጣ የምርጫ ክልሎች ፤ ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደራዊ ዕውቅና ውጪ “ቀጥተኛ የፓርላማ ምርጫ” ለማካሄድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተላለፈውን ውሳኔ በይፋ እና በማያሻማ ሁኔታ ይቃወማል።

ይህ ውሳኔ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን እንዲሁም የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መንፈስና ቃል በከፍተኛ ሁኔታ የሚጥስ ነው። በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግሥት መሠረት ከላይ የተጠቀሱት ግዛቶች የትግራይ ክልላዊ መንግሥት አካል መሆናቸው ይታወቃል። ማንኛውም የክልል አስተዳደራዊ ወሰን ለውጥ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቶችን መከተል ይኖርበታል። በወረራ የተያዙ የትግራይ ግዛቶች በኢ.ፈ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት እና በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ከጦርነት በፊት ወደነበሩበት የትግራይ ክልላዊ ኣስተዳደር እንዲመለሱ በምንጠብቅበት ሰኣት፤ አወዛጋቢ ለተባሉ ጥያቄዎች ሕጋዊና ሕገ-መንግሥታዊ መፍትሔ ሳይሰጥ፣ ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ በማድረግ በእነዚህ አካባቢዎች ምርጫ ለማካሄድ መወሰን፤ ቦርዱም ሆነ ምክር ቤቱ ሊያስከብሩት የሚገባውን ሕገ-መንግሥታዊ ማዕቀፍ የሚፃረርና በአንድ ወገን የሚደረግ የአስተዳደር ለውጥ በመሆኑ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው።

ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ሰላማዊ፣ ሕጋዊና ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲኖር የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ በ2018 ዓ/ም በሚካሄደው አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ የመጨረሻ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ያለበት ሁኔታ መኖሩ ይታወቃል። ሆኖም ግን፣ አሁን የተላለፈው ኢ-ህገ መንግስታዊ ውሳኔ የሰላም መንገድን የሚቀለብስ ፣ ምርጫውን እና ምርጫ የሚያካሂደውን ተቋም ተአማኒነትና ሁሉን አቀፍነት መሠረት የሚንድ በመሆኑ ይህ ውሳኔ በአስቸኳይ ተቀይሮ እነዚህ አካባቢዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ ባወጣው የምርጫ ክልሎች ኣወቃቀር መሰረት ካልተደረገ በስተቀር፤ ባይቶና ዕጩዎቹን የሚያነሳና ከ2018ቱ አጠቃላይ ምርጫ ሙሉ በሙሉ የሚወጣ መሆኑን እንገልፃለን።

ይህ አካሄድ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የመጣውን ያልፀና ሰላም አደጋ ላይ የሚጥልና የትግራይ ህዝብና መንግሥት ሕገ-መንግሥታዊ አንድነትን የሚፈታተን በመሆኑ ይህንን ውሳኔ ለመቃወም ያሉትን ሕጋዊ፣ ፖለቲካዊና ሰላማዊ አማራጮች ሁሉ እንደምንጠቀም በድጋሚ እንገልፃለን።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ የምርጫ ተቋም ሆኖ የተሰጠውን ኃላፊነት እንዲወጣ፣ የፌዴራል ኣካላትም ሕገ-መንግሥቱንና የአገሪቱን አውዳሚ ጦርነት የቋጩ ስምምነቶችን እንዲያከብሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና)
የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም
መቐለ ትግራይ.

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

Egypt’s Red Sea Signal: Opening the Door to a Historic Nile Agreement with Ethiopia

"sources like The National indicating Egypt's conditional openness to...

አብን በሁመራ፣ አዲረመጥ፣ ኮረም ኦፍላ፣ ጠለምት ራያና አላማጣ ሕዝቡ ለክልልም ምርጫም መሳተፍ አለበት አለ

አዲስ ሪፖርተር - "ህዝባችን ለክልሉ ምክርቤት ጭምር ምርጫ መካሄድ...

“ለዓመታት የፖለቲካ መብታቸው ተገፎ ለኖሩ ዜጎች የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ታሪካዊ እርምጃ” ወልቃይት

አዲስ ሪፖርተር - የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ...

“ለአራተኛ ጊዜ ተወረናል” ከወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ከሚቴ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ ሪፖርተር - "መንግሥትም የህዝቡን የማንነት እና የራስ አስተዳደር...