ካጃዋር ጋር ገጥመው የነበሩት አቶ ነዓምን ከኦሮሞዎች ጋር መስራት እንደማይቻል አስታወቁ፤ “ተረኛ መሆናቸውን እያወቅን ዝም ብንልም አልገባቸውም”

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና – ምርጫ እንዳይደረግ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግና በኢትዮጵያ አመጽ ለማስነሳት የተለያዩ አደረጃጀቶችና ማህበራትን አንድ ላይ በማሰባሰብ ግብረኃይል መስርተው የነበሩት አቶ ነዓምን ዘለቀ ከኦሮሞሞዎች ጋር አብሮ መስራት እንደማይቻል አስታውቁ።

እሁድ ግንቦት 16 ቀን ወይም ኤርትራዊያን በሚጠቀሙበት የተውሶ የነጮቹ አቆጣጠር ግንቦት 24 ቀን 2026 የሚከበረውን የኤርትራዊያን የድል ቀን አስመልክቶ በዋዜማው በአሜሪካ ኤርትራ ኤምባሲ በተዘጋጀው ጠበል ጻዲቅ ላይ አቶ ነዓምን እና ባልደረባቸው አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በመጋበዛቸው ሊሰጥ የነበረው የግብረኃይሉ የዓየር ላይ መግለጫ ለረቡዕ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ተላልፎ ነበር።

በውቅቱ መግለጫ እንዲሰጡ የተመደቡት ከኦሮሞ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል፣ ከሶማሌ ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴ፣ ከደቡብ መመህር ደምሰው፣ ከአማራ አቶ ልደቱ አያሌው፣ ከህወሃት አቶ አባይ ግደይ ነበሩ። ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት መሪ ጃልመሮ አማካሪና ቃል አቀባይ አቶ ጂረኛ በትናንትናው ዕለት ተለምነው እንዲገቡ ተደርጎ ነበር።

ቀኑ ከመዛወሩም በፊት እየተመናመነና በጥርጣሬ በየስብሰባው አለመግባባት እያስተናገደ ሲያዘግም የነበረው አቶ ነዓምንና አቶ ልደቱ የሚመሩት የአመጽ አደራጁ ግብረኃይል፣ ከጸበል ጻዲቅ ግብዣው የተነሳ በተያዘው ተለዋጭ ዕለት ረቡዕ ግንቦት 19 ቀን 2918 ዓ.ም መግለጫው ሲሰጥ ቀድሞ የተደለደሉት አሻፈረኝ ማለታቸውን የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግተን ዘጋቢ አመልክቶ እንደነበር ይታወሳል።

በእለቱ መግለጫ ሲሰጥ እንደታየው የቡድኑ ዋና አለቃና የሻዕቢያ ወኪል አቶ ነዓምን፣ አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም፣ ኢንጂነር ግደይ፣ አቶ አባይ እና አቶ ልደቱ ነበሩ የተገኙት። ተባባሪያችን በወቅቱ ባሰባሰበው መረጃ መሰረት የግብረኃይሉ አመራሮች ራሳቸው በመግለጫው ላይ የተሰየሙት ቀደም ብሎ የተመደቡት ለመገኘት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነበር። ፈቃደኛ ካልሆኑት መካከል “አሁን ላይ ሁሉም ወደ አለመተማመን ደረጃ ደርሷል። የግብጽ ብር የሚቀበሉና እኛን ማዳመቂያ ያደረጉን አሁን ተግባብተናል” ሲሉ ምክንያታቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ ቀደም ለአዲስ ሪፖርተር በደረሰ የግብረኃይሉ ስብሰባ የድምጽ መረጃ “እኛ ከኤርትራና ግብጽ ገንዘብ ገንዘብ አንቀበልም። እናንተ ገንዘብ እየወሰዳችሁ እኛን መጠቀሚያ አታድርጉን” በሚል ተቃውሞ መነሳት እንደተጀመረ መዘገባችን አይዘነጋም።

ቀደም ሲል በወጣው ዝርዝር መርሃ ግብር መሰረት ሃያ ሶስት የተለያዩ ሚዲያዎች የዙም ጋዜጣዊ መግለጫውን በቀጥታ ያስተላልፉታል ቢባልም የተገኙት ግን፣ “ታማኝ” የሚባሉት ኢኤምኤስ፣ የሃሳብ ገበታና ፍሪ ፕሬስ ብቻ መሆናቸው ታይቷል።

ከዚህ መግለጫ በኋላ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ጋቢሳ “ይህ የአቢሲሲኒያ ስብስብ ነው” በማለት መተቸታቸውን የሰሙትና በግብረኃይሉ ውስጥ የነበሩ ኦሮሞዎች ራሳቸውን በማግለላቸው አቶ ነዓምን “ከኦሮሞዎች ጋር መስራት አይቻልም” በማለት ኦሮሞ ላልሆኑት የግብረኃይሉ አባላት በግል ተናግረዋል። “ኦሮሞዎቹ በቅርቡ በአሜሪካ ትልቅ ስብሰባ ለማካሄድ አስበዋል። ስብሰባውን እኛ አንቀበለውም” ብለዋል።

“ተረኛ መሆናቸውን እያውቅን ችለን አብረን ለመስራት ብዙ ዋጋ ብንከፍልም ሊገባቸው አልቻለም” ሲሉ በብስጭት የተናገሩት አቶ ነዓምን ከኦሮሞ በቀር ሌሎች ብሄሮችን በማሰባሰብ ስራው እንደሚቀጥልም በግል ሲያናግሯቸው ለነበሩት ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል “ግብረኃይሉን የተቀላቀልነው ልናፈርሰው ነው” በማለት ቀደም ሲል ለሚቀርቧቸው የግብረኃይሉ አባላት መናገራቸውንና እሳቸው በሚመሰርቱት አዲስ ህብረት ውስጥ ለመታቀፍ እንዲዘጋጁ አሳስበው እንደነበር አዲስ ሪፖርተር ከወር በፊት ሪፖርት አቅርቦ ነበር።

የዋሽንግቶን ተባባሪ ሪፖርተር እንዳለው አቶ ነዓምን ከፍተኛ በጀት እየተመደበላቸው በኢትዮጵያ አመጽ እንዲቀሰቀስ የሰሩት ስራ ፍሬ አለማፍራቱ በቀጣይ “በሳልና የተከበሩ ሰዎችን ወደፊት ማምጣቱ የተሻለ ነው። አቶ ነዓምን የብስለት፣ የአመራርና ብልሃትና የፖለቲካ አቅም የሌለው ጉልበተኛ በመሆኑ ለእሱ የማህበራዊ ሚዲያውን ብቻ እንዲያነቀሳቅስ ይደረግ” የሚል ሃሳብ ለሻዕቢያ እንደቀረበ ከግብረኃይሉ የበላይ አመራሮች ቅርብ ከሆኑ ለመስማት ተችሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ በግልጽ ባይታወቅም ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በአዲስ መልኩ ብረት ያነሱ ኃይሎችን የማሰባሰብ ስራ መጀመራቸው ታውቋል። ሻለቃ ዳዊት ሲኒየር የሻዕቢያ አጋር፣ አቶ ነዓምን ደግሞ ጁኒየር መሆናቸው ይታወቃል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የኢትዮጵያ የምርጫ ዋዜማ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዛቢዎችና ሚዲያዎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች አቀኑ፤

አዲስ አበባ አዲስ ሪፖርተር ዜና - ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ...

“የብልጽግናን ሚስጢራዊ መረጃ ማግኘት አለመቻላችን እየፈረካከሰን ነው” የግብረኃይሉ አባላት፤

የኢሳያስ ዝምታ በጽምዶ አባላት ውስጥ ቅሬታና ልዩነት አስነሳ አዲስ...

ስቴት ዲፓርተመንት የህወሃትን የውጭ ግንኙነት ኃላፊዎች “የአደራድሩን” ጥያቄ ውድቅ አደረገ፤

አዲስ ሪፖርተር ዜና - በስምምነት የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አፍርሶ...