ስቴት ዲፓርተመንት የህወሃትን የውጭ ግንኙነት ኃላፊዎች “የአደራድሩን” ጥያቄ ውድቅ አደረገ፤

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና – በስምምነት የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አፍርሶ ስልጣን የተቆጣጠረው የህወሃት አንድ ክንፍ የውጭ ግንኙነት መሪዎች ከስቴት ዲፓርተመንት ባለስልጣናት ጋር ለመገናኘትና የ”አደራድሩን” ጥያቄ ለማቅረብ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ተሰማ። “ከመንግስት ጋር ተነጋገሩ” ተብለዋል።

የአዲስ ሪፖርተር የአሜሪካ ተባባሪ ከአምባሰደር ፍስሃ አስገዶም ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ከተወያዩ ወገኖች ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ እንዳለው የዩኤስ ስቴት ዲፓርትመን የቀረበለትን የውይይትና የ”አደራድሩን” ጥያቄ ውድቅ እንዳደርገው ያሳወቀው በሳምንቱ መጀመሪያ ነው።

በጦርነቱ ወቅት በፈለጉት ደረጃና መጠን ከስቴት ዲፓርትመንት ሰዎች ጋር የሚመክሩት የህወሃት ሰዎች ስቴት ዲፓርትመንት የሰጣቸው ምላሽ ከተደጋጋሚ ጥያቄ በኋላና ከወስዋሾች ጉትጎታ በኋላ መሆኑ ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነ ከመረጃው ባለቤቶች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

ዶክተር አዲስ ዓለም ቤሌማ በቅርቡ ከትግራይ የዲያስፖራ አባላት ጋር በዙም ባደረጉት ገለጻ በዲፕሎማሲው ረገድ ተቀባይነት ማጣታቸውን መግለጻቸውና የክልሉ ተወላጆች በጦርነቱ ወቅት ሲያደርጉት እንደነበረው በሚኖሩባቸው አገራት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ጫና እንዲያሳድሩ መጠየቃቸው አይዘነጋም።

ባለፈው ወር የአሜሪካ ባለስልጣናትና ከፍተኛ ወታደራዊ አዝዦች መቀለ በመገኘት ጦርነት የሚባል ነገር እንዳያስቡ፣ በቀጠናው አሜሪካ የራሷ ፍላጎትና ስትራቴጂካል ግብ ስላላት ጦርነት የሚያነሱ ከሆነ ማዕቀብ እንደምትጥል ማስጠንቀቋ በተለያዩ መገናኛዎች መዘገቡ አይዘነጋም።

በትግራይ ሕዝብ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ማህበራትና በተለይም ወጣቶች በገሃድ እየተናገሩና ትግራይን ለቀው እየወጡ መሆኑን ራሳቸውን የለውጥ ኃይሎች የሚሉት ክፍሎች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እየገለጹ እንደሆነ ይታወቃል።

የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን፣ ወታደራዊ መኮተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን፣ ወታደራዊ መኮንኖችን፣ የሲቪክ ማህበራትን፣ ምሁራንና የሚመለከታቸው ያሏቸውን አሰባስቦ ይትቋቋመው የትግራይ ለውጥ ፈላጊዎች ንቅናቄ በትግራይ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አቅጣጫ ለመቀየር እንቅስቃሴ ምክር ቤት አቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታውቃል። ይህ ምክር ቤት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አግባብ መሰረት እንደሚሰራ ለዓለም አቀፍ የዲፕሎማት መድረክ በተደጋጋሚ መናገሩና ከመንግስት ጋር አብሮ እንደሚሰራ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

መቀለ ከጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር በስምምነት አስተዳደር አፍርሶ ስልጣኑን የተቆጣጠረው የእነ ዶክተር ደብርጽዮን ቡድን አስመልክቶ የፌደራል መንግስት ይህ እስከተጻፈ ድረስ ምንም አላለም። በህወሃት በኩል ግን ከፋኖ ኃይሎች ጋር በመሆን ሌሎችን አስተባብሮ የተቀናጀ ጦርነት ለመክፈት ዝግጅት ላይ መሆኑን እያስታወቀ ነው።

የትግራይ ሰላም ኃይሎች እንደሚሉት ህወሃት “ፋኖ ድፍን አማራን ተቆጣጥሯል” በማለት የተወሰኑ ቦታዎችን በመያዝ ለመደራደር እንዲቻል ጦርነት እንደሚከፍቱ በግዳጅ ለሚመለምሏቸውና ለነባር ታጣቂዎቻቸው ስልጠና እየሰጡ ነው።

ይህ እየሆነ ባለበት በአሜሪካ የሚኖሩ የህወሃት ሰዎች ያቀረቡት የ”አደራድሩን” ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ድንጋጤ ቢፈጥርም በአካሄዱ ቅሬታ ለተሰማው ለሻእቢያ ዜናው መልካም እንደሆነለት ለመረዳት ተችሏል። ተባባሪያችን እንዳለው የአሜሪካ አቋም ህወሃት ከሻዕቢያ ውጭ ሌላ አማራጭ እንዳይኖረው ያደርገዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ምርጫ ለማጨናገፍ የተቋቋመው የእነ ነዓምን ቡድን ተከፋፈለ፤ ከዙም መግለጫ አባላቱ አፈገፈጉ፤

አዲስ ሪፖርተር ዜና - ኤርትራ ከኢትዮጵያ የተለየችበትን ቀን በምታከብርበት...

ዳውድ ኢብሳና መረራ ጉዲና አለመታሰራቸውን አረጋገጡ፤ “በምርጫው ዋዜማ ታስረዋል”

አዲስ ሪፖርተር ዜና - "አቶ ዳውድ ኢብሳና ፕሮፌሰር መረራ...

ኤፍሬም ማዴቦና ነዓምን በሻዕቢያ በዓል ላይ ታዳሚ በመሆናቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ለኢድ ቀን ተላለፈ፤

አዲስ ረፖርተር ዜና - አባላቶቹ በመበተናቸው መደበኛ ስብሰባውንና ሊያካሂዳቸው...