ከግንቦት በኋላ የሚፈርሰው የአመጽ አደራጅ ግብረሃይል እስከሚፈስርስበት ወር ድረስ እቅድ አወጣ፤ አዲስ ስታንዳርድን ለትርክት ግንባታ መረጠ

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና የየህዝባዊ እምቢተኝነት ለማደራጀት የተቋቋመው ግብረ ሃይል የህዝብ ግንኙነት እስከ ግንቦት ወር የሚያካሂደውን የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ አደረገ። ይህ የትርምስ አመቻች ግብርኋይል ምርጫ እንዳይካሄድ ከማድረግ የዘለለ ዓላማና አደረጃጀት እንደሌለው አቶ ነዓምን አስታውቀው ነበር። በዕቅዱ መሰረት ከግንቦት በኋላ ይፈርሳል።

በግንቦት እድሜውን የሚጨርሰው ይህ ስብስብ ለቅሰቀሳ ባዘጋጀውና ለአባላቱ በበተነው ሰነድ ላይ ለቅሰቀሳ ስራ የሚሳተፉ አባላቱ ለፈጠራ ትርክት ይረዳቸው ዘነዳ አዲስ ስታንዳርድን ላይ የተለጠፉ መረጃዎችን እንዲከታተሉ ሊንክ ወይም ማስፈንጠሪያ አኑሯል። ለ”አዲስ ትርክት ግንባታ ግብአት” በማለት ካኖራቸው አስር የተመረጡ ሰነዶች ውስጥ ስድስቱ የአዲስ ስታንዳርድ ሲሆን፣ አራቱ ከፍሪደም ሃውስና ከአምነስቲ ሪፖርት እንዲቀዳ አመላክቷል።

ሰነዱ እንደሚለው የህዝብ ግንኙነት ዘርፉ ተጠሪነቱ ለህዝባዊ እምቢተኝነት መድረክ ስራ አስፈጻሚ ሆኖ፣ በስሩ ሰባት አባላትን የያዘ ንዑስ ኮሚቴ አዋቅሯል።

ዋና ዓላማው በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ምዕራፍ እንዲመጣ የሚያስችሉ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራዎችን ማከናወን እንደሆነ በሰነዱ የተመለከተ ሲሆን፣ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ ህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባላት ከተለያዩ ሚዲያዎች ጋር በመተባበር በአቶ ገለታው አስተባባሪነት ከምን አለሽ መቲ ሚዲያ፣ ከአንከር ሚዲያ ከEMS ሚዲያ፣ ከዕዮት ሚዲያ እና የሃሳብ ገበታ እንዲሁም ሌሎች የተመረጡ ሚዲያዎች ጋር በመናበብ እንደሚሰራ ተመልክቷል። ሰነዱ እነዚህን ሚዲያዎች “ለውጥ ፈላጊዎች” ብሏቸዋል። በሰነዱ ከአገር ውስጥ አብረው የሚሰሩትን ሚዲያዎች አልጠቀሰም።

ከኤፕሪል መጨረሻ ጀምሮ በየሳምንቱ እሁድ መግለጫዎችን ለህዝብ ማቅረብ እና ለውጥ ከሚፈልጉ ሚዲያዎች ጋር የበይነ መረብ (Online) ኮንፈረንስ የማካሄድ ዕቅድ ተያዟል። በሜይ 17 ቀን 2026 ህዝቡን ለሰላማዊ ትግል የሚያበረታታ የሰማይ ላይ ኮንፈረንስ ለማዘጋጀት ቀተሮ ይዟል።

ባለፈው ቅዳሜ በተደረገ ምርጫ አምባሳደር ብርሃነ፣ አቶ ነዓምን፣ አቶ አባይ፣ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ፣ እና አቶ ልደቱ የዋሽንግቶኑን ሰልፍ እንዲያደራጁ ተመርጠዋል። በዲፖሎማሲ በኩል ጫና ለማሳደር አቶ ነዓምን፣ ኢንጂነር ግደይ፣አምባሳደር ብርሃነ ተመድበዋል። ለሎንደኑ ሰልፍ ደግሞ የፊታችን ሃሙስ ሰባት ሰዎች እንደሚመረጡ ለማወቅ ተችሏል። ይህን ዕቅድ ፋኖ አድንቆ እውቅና እንደሚሰጠው በአስረስ አማካይነት በፌስ ቡክ ተለጥፏል።

በሎንደንና ዋሽንግቶን ለማካሄደ የታሰበው ሰልፍ በበርካታ ምክንያቶች የተሳካ እንደማይሆን ዶክተር ሚካኤል ከጅምሩ ማሳሰባቸው ይታውሳል። አቶ ነዓምንም ተመሳሳይ አሳብ አራምደው “መሞከር ነው” ማለታቸው በአዲስ ሪፖርተር የስብሰባውን ኦዲዮ በማመሳከር መዘገቡ አይዘነጋም። የስጋቱ ምንጭ ደግሞ አሜሪካ የየዛችው ወቅታዊ አቋምና በቅርቡ ከአሜሪካ ወደ አገሩ እንዲመለስ የተደረገው ኢትዮጵያዊ ጉዳዩ ከሽብር ጋር በመያያዙ ነው። ከዚህም በተጨማሪ አፋብን ወልቃይት ላይ የያዘው አቋምና ከሻዕቢያ ጋር የተፈጠሩ ጥምረቶች በርካቶችን ማሳዘኑ በጋራ ተቃውሞ ለመውጣት የማያስችል ሌላ ምክንያት ሆኗል። ያም ሆኑ ዕቅዱ እነ አቶ ነዓምን የሚመሩት ኮሚቴ በሚያዘው መሰረት እንዲሰራ ተብሏል።

የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ዘፈን የፈጠረው መነቃቃት እይቀዘቀዘ በመሆኑ የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴው ከኤፕሪል 30 ጀምሮ በየሳምንቱ የህዝቡን ችግር የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ማሰራጨት እና ከሜይ 1 ጀምሮ በየ15 ቀኑ ንቅናቄን የሚፈጥሩ ግጥሞችንና ጽሁፎችን በስፋት እንዲሰራጩ አዟል። ይህንን የሚያስፈጽሙት አቶ ገለታው እና አቶ ነዓምን እንደሆኑም ተመልክቷል።

እቅዱ ለታቀደው ዓላማ ይረዳሉ በሚል ለትርክት ግንባታ እንደ አዲስ ስታንዳርድ (Addis Standard)፣ ፍሪደም ሃውስ (Freedom House) እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያሉ ተአማኒ ተቋማት ያወጧቸውን መረጃዎች በተለያዩ ሚዲያዎች ቀርበው የሚናገሩ አባላቱ እና ተጨማሪ የሚመለመሉ ሃያ አምስት ሰዎች እንዲጠቀሙበት ደጋግሞ ወትውቷል። የአቅም ኝባታም እንደሚሰራ አመልክቷል።

ዋና ትኩረቱም በኢትዮጵያ ያለው የሰላም፣ የዴሞክራሲ እና የህግ የበላይነት ሁኔታ ለነጻ ምርጫ እንደማይፈቅድ የሚያሳዩ መረጃዎች ላይ ማተኮር እነደሆን ደጋግሞ የሚገልጸው ዕቅድ “የተለያዩ ስርዓቱን የሚኮንኑ፣ የህዝቡን ብሶት ቁልጭ አድረገው የሚያሳዩ፣ ለለውጥ የሚነሽጡ ግጥሞችን እና አጫጭር ጽሁፎችን እያመረቱ በፌስ ቡክ፣ በዩቱብ፣ በትዊተር እና በኢሜየል ማሰራጨት፣ ይህንን የሚሰሩ ታለንት ያላቸውን ሰዎች በማፈላለግ ወደፊት ሰው ይመደባል” ይላል።

የስራ አስፈጻሚ አባላትን በየተራ ወደ ሚዲያ እንዲቀርቡ እቅድ ማውጣት፣ ከስራ አስፈጻሚ አባላት ውጭ ሃያ አምስት የሚሆኑ ተናጋሪዎችን መለየት እና ወደ ሚዲያ እንዲቀርቡ ማድረግ፣ የሚተላለፉትን ፕሮግራሞች ተከታትሎ የንቅናቄው ግብረ ሃይል በዚህ ኮሚቴ በኩል እንዲሰራ የሚሰጣቸውን ተግባራት ደረጃ በደረጃ መፈጸም እና ግምገማ ማድረግን በዕቅዱ ያሰፈረው ሰነድ፣ “የንቅናቄውን የስራ አስፈጻሚ አባላት እና ከአጠቃላይ ምክር ቤቱ እንዲሁም ትግሉን የሚደግፉ ሰዎችን እየመደብን በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ እየቀረቡ የንቅናቄውን ዓላማዎች፣ ተግባራት እንዲገልጹ ወቅታዊ ጉዳይ እያነሱ ህዝብ እንዲያነቁ ማድረግ” ወቅታዊ ጉዳይ መሆኑን አመልክቷል።

የኮሚቴው አባላት ስብስቡ ወጥ መተዳደሪያ ደንብና ድርጅታዊ ቅርጽ ያለው እንዲሆን፣ መተማመን ሊፈጥር የሚችል አሰራር እንዲከተል ሲጠየቅ “ቅንጅት፣ህብረት፣አንድነት፣ጥምረት ወዘተ የሚባሉ ልምምዶች አሉ፤ ይህ ስብሰብ ዓላማው ምርጫ እንዳይካሄድ ማድረግ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ይፈርሳል” ሲሉ ኮሚቴዎቹንና ግብረኋይሉን የሚመሩት የሻዕቢያ ወኪል አቶ ነዓምን መልስ መስጠታቸው አይዘነጋም። ይህ ምላሻቸው “ስብሰቡ ዝም ብሎ መግበስበስ ይሆናል” ያሉትን ዶክተር ሚኒሊክን አበሳጭቶ ነበር። በዕቅዱ መሰረት ከግንቦት በኋላ ምንም ተግባር የሌለው ይህ ስብሰብ እንደሚበተን ለማወቅ ተችሏል። ምርጫው የሚካሄደው በግንቦት 24 መሆኑ ይታወቃል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአሜሪካ ዲፕሎማት እና ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ህውሃትን ማዕቀብን እንደሚጣል አስጠነቀቁ

ወደ መቀለ የመጣው የአሜሪካ ልኡክ ከፍተኛ ወታደራዊ ኃላፊዎች የተገኙበትና፣...

“ከመብረቃዊ ጥቃት” መግለጫ በኋላ የሴኮ ቱሬ የመጨረሻ ሳምንታት፤ “አማራ ስለሆንክ አጋለጥከን” የድምጸ ወያኔ ምስክርነት

አዲስ ሪፖርተር - በአብዮታዊ ዴሞክራሲ መጽሄትና ጋዜጣ ዝግጅት መሪነት...

“ሻዕቢያ ገድሎናል፣ አርዶናል፣ወግቶናል ዓለም ዓቀፍ ፍትህ እንፈልጋለን፣ አሁን ግን ጊዜው አይደለም”

“እርግጥ አርደውናል፣ ገለውናል፣ ወግተውናል፣እውነት ነው፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ፣ ከዓለም...