ምርጫ ለማጨናገፍ የተቋቋመው የእነ ነዓምን ቡድን ተከፋፈለ፤ ከዙም መግለጫ አባላቱ አፈገፈጉ፤

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና – ኤርትራ ከኢትዮጵያ የተለየችበትን ቀን በምታከብርበት ቀን ሊደረግ የነበረው የአመጽ አደረጃ ግብረኃይል የዙም ጋዜጣዊ መግለጫ ለሙስሊሞች በዓለ ኢድ ቀን የተላለፈው ዋናው የግብረኃይሉ መሪዎች በአሜሪካ የኤርትራ ኤምባሲ ተጋባዥ ስለነበሩ ነበር። በዚሁ መሰረት ዛሬ በተካሄደው መግለጫ ግብረኃይሉ መቀጠል እማይችልበት ደረጃ መድረሱን አመላካች መረጃዎች ይፋ ሆነዋል።

የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ የዘወትር የግብረሃይል የመረጃ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው በዛሬው የዙም መግለጫ ላይ ይገኛሉ ተብለው አስቀድመው ስማቸው ይፋ ይሆነው፣ ከኦሮሞ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል፣ ከሶማሌ ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴ፣ ከደቡብ መመህር ደምሰው፣ ከአማራ አቶ ልደቱ አያሌው፣ ከህወሃት አቶ አባይ ግደይ ነበሩ። ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት መሪ ጃልመሮ አማካሪና ቃል አቀባይ አቶ ጂረኛ በትናንትናው ዕለት ተለምነው እንዲገቡ ተደርጎ ነበር።

በዛሬው እለት መግለጫ ሲሰጥ እነደታየው የቡድኑ ዋና አለቃና የሻዕቢያ ወኪል አቶ ነዓምን፣ አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም፣ ኢንጂነር ግደይ፣ አቶ አባይ እና አቶ ልደቱ ነበሩ የተገኙት። ተባባሪያችን ባሰባሰበው መረጃ መሰረት የግብረኃይሉ አመራሮች ራሳቸው በመግለጫው ላይ የተሰየሙት ቀደም ብሎ የተመደቡት ለመገኘት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው። ፈቃደኛ ካልሆኑት መካከል “አሁን ላይ ሁሉም ወደ አለመተማመን ደረጃ ደርሷል። የግብጽ ብር የሚቀበሉና ማዳመቂያ የሆኑት ተግባብተዋል” ሲሉ ምክንያታቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ ቀደም ለአዲስ ሪፖርተር በደረሰ የግብረኃይሉ ስብሰባ የድምጽ መረጃ “እኛ ከኤርትራና ግብጽ ገንዘብ ገንዘብ አንቀበልም። እናንተ ገንዘብ እየወሰዳችሁ እኛን መጠቀሚያ አታድርጉን” በሚል ተቃውሞ መነሳት እንደተጀመረ መዘገባችን አይዘነጋም።

ቀደም ሲል በወጣው ዝርዝር መርሃ ግብር መሰረት ሃያ ሶስት የተለያዩ ሚዲያዎች የዙም ጋዜጣዊ መግለጫውን በቀጥታ ያስተላልፉታል የተባለ ቢሆንም የተገኙት አንከር፣ ኢኤምኤስ፣ ገበታና ፍሪ ፕሬስ ብቻ መሆናቸው ታይቷል።

የህወሃት ወኪል የሆኑት አቶ አባይ የሚዲያዎቹን አለመገኘትና መግለጫ እንዲሰጡ በብሄር ተመልምለው ያልተገኙት በሌሎች ላይ ጫና እንዳያሳድሩ “ከሰባ በላይ ድርጅቶች ወክለውን ነው እዚህ የተገኘነው” በማለት መናገራቸውን በማንሳት የተቹት የግብረኃይሉ አባል፣ “የተመረጡት አልመጣም ሲሉ ዛሬ ነው የተሰባሰቡ፣ የተሰባሰቡትም ከሁለት ብሄርና ከሻዕቢያ ወኪል ብቻ ነው። ሰባ ድርጅት የተባለው ቀልድ ነው” ብለዋል።

ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል “ይህ የአቢሲኒያ ስብስብ ነው። ምን አደርጋለሁ” በማለት ለሌላ ያተገኘ ባልደረባቸው በለበጣ መልክ መናገራቸው ተሰምቷል። ፕሮፌሰሩ ሌላ ስብሰብ እያዋቀሩ እንደሆነም ተመልክቷል።

አሁን ላይ ግብረኃይሉ እርስ በርስ መተማመን የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ያመለከቱት የቡድኑ አባል፣ መረጃ አስቀድሞ ይፋ እየሆነና በድብቅ ከኤርትራና ግብጽ ጋር የሚሰሩትን ይፋ የሚያወጡ አባላት ሊታወቁ አለመቻላቸው አብሮ ለመቀጠል አስቸጋሪ እንደሆነ ሰብሳቢዎቹ መናገራቸውን አመልክተዋል። በዚሁ መሰረት የተፈጠረው ጥርጣሬ አድጎ ወደ መፈራራትና አሁን ይፋ ከሆነው በላይ መረጃ እንዳይወጣ ስጋት መንገሱን አመልክተዋል። በአሜሪካ ኤርትራ ኤምባሲ ተገኝተው “እንኳን ከጨቋኟ ኢትዮጵያ ነጻ ለወታችሁበት ቀን አደረሳችሁ” በማለት ኬክ የቆረሱት አቶ ነዓምንና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ እንደሆኑ በዕለቱ መዘገባችን አይዘነጋም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ስቴት ዲፓርተመንት የህወሃትን የውጭ ግንኙነት ኃላፊዎች “የአደራድሩን” ጥያቄ ውድቅ አደረገ፤

አዲስ ሪፖርተር ዜና - በስምምነት የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አፍርሶ...

ዳውድ ኢብሳና መረራ ጉዲና አለመታሰራቸውን አረጋገጡ፤ “በምርጫው ዋዜማ ታስረዋል”

አዲስ ሪፖርተር ዜና - "አቶ ዳውድ ኢብሳና ፕሮፌሰር መረራ...

ኤፍሬም ማዴቦና ነዓምን በሻዕቢያ በዓል ላይ ታዳሚ በመሆናቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ለኢድ ቀን ተላለፈ፤

አዲስ ረፖርተር ዜና - አባላቶቹ በመበተናቸው መደበኛ ስብሰባውንና ሊያካሂዳቸው...