ኢሳያስ የሃያ ሁለት ዓመታት ተቃዋሚያቸውን “እየፈረሰ ነው” ለተባለው “ጽምዶ” የቅስቀሳ አስተባባሪ አድርገው ሾሙ

Date:

ሰሞኑን የሚሰሙት መረጃዎች የጽምዶን ሞት አመላካች ናቸው እየተባለ ነው። ጥምረቱ የኦሮሞ ልሂቃንና የኦሮሞ ጠብመንጃ አንጋቾች እንደሌሉበት ይፋ አድርጓል። የደቡብ፣ የሶማሌ፣ የጋምቤላና የቤኒሻንጉል ተወካዮችን በይፋ ያገለለው ይህ ጥምረት በባለቤቱ ሻዕቢያ አማካይነት አዲስ የሚዲያ ክንፍ መሪ ሰይሟል። “በጦርነት የሚሆነው እስከሚታወቅ በፕሮፓጋንዳ ከፍተኛ ዘመቻ ይደረግ” በማለት በጀት የመደበው ሻዕቢያ በጽምዶ ስም የሾማቸው ሰው ኢትዮጵያዊ ቆዳ ያላቸውን እየወሰወሱ እንደሆነ ተሰምቷል። በሻዕቢያ ስር የሚተዳደሩት ሚዲያዎን አካቶ ኢትዮጵያ ላይ የትርምስ ፕሮፓጋንዳ ለማሰራጨት የተሾሙት ሰው “ኤርትራን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተሰሚ እንድትሆንና የነበረባትን መገለለ ለመቅረፍ እሰራለሁ” ብለዋል። ሃያ ሁለት ዓመት ሻዕቢያን ሲከሱ የነበሩት አዲሱ ሹመኛ፣ ሻዕቢያን ትተው ኢትዮጵያን ለማፍረስ …

አዲስ ሪፖርተር ዜና | አዲስ አበባ – ግብጽ ኢትዮጵያን ለመክበቡ በሱዳን፣ በሶማሊያ፣ በኤርትራና በጅቡቲ በኩል ከፍተኛ ሃብት እያፈሰሰች ባለችበት ወቅት  “በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት” ስም “ጽምዶ” የሚባል ጠብመንጃ ያነሱ ቡድኖችን ያሰባሰብ ህብረት መፈጠሩ ግጥምጥሞሽ አይደለም። 

ግብጽ ኢትዮጵያን የመክበብ ስትራቴጂያቸውን ለማስፋት እያደረገችው ካለው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ኢትዮጵያን በውስጥ ተቃዋሚዎች የማዳከምና የማባላት የኖረ ስልቷን ከቀድሞ በበለጠ እይሰራችበት ነው። ለዚህ ተግብሯ ደግሞ ሻዕቢያንና ወያኔን ከማስታረቅ ጀምሮ ከፍተኛ በጀት መድባ እያሰራች መሆኗም የአደባባይ ሚስጢር ነው። አዲስ ሪፖርተር ከተቋቋመች ጀምሮ በትግራይ፣ በኤርትራ፣ ሱዳን፣ ቱርክ፣ ሞቃዲሾ፣ ግብጽ ወዘተ የተደረጉ ስብሰባዎችን ዝርዝር ሪፖርት ስታቀርብ መቆየቷ አይዘነጋም። 

የኤርትራ መንግስት ለተባበሩት መንግስታት ሳይቀር “ለቀጠናው አስተማማኝ ሰላም መፍትሄ” በማሰብ ጽምዶ መቋቋሙን አስታውቆ ደብዳቤ የጻፈለት ይህ ጥምረት ኤርትራን፣ ትግራይ ክልልን፣ አፋርን፣ አማራን፣ እና በሶማሊያ፣ በሱዳንና በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ማካተቱ ለዚሁ ጥምረት የተዘጋጀው ድረ ገጽ ይፋ አድርጓል። ይህ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በግልጽ የጣሰ “የሰሜኖች ስብስብ” የሚባለው ማህበር በግልጽ ኢትዮጵያን የመበተን እቅድ እንዳለው በተለያዩ ግዜያት መገለጹም አይዘነጋም። 

ኦሮሞን፣ ደቡብ ኢትዮጵያን፣ ሶማሌ ክልልን፣ ያገለለው የሻዕቢያ “ጽምዶ” የተሰኘ ማህበር ትግራይን ማካተቱን ቢገልጽም፣ በትግራይ ዘንዳ እንኳን ተቀባይነት ሊያገኝ፣ ሻዕቢያ በትግራይ ህዝብ ላይ በፈጸመው ወንጀል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ህግ ፊት ሊቀርብ እየንደሚገባው እየተጠየቀ ነው። 

በዚሁ የግብጽና የሻዕቢያ ማህበር ውስጥ “አለበት” የተባለው የአማራ ክልል በማንና በየትኛው ድርጅት ውሳኔ እንደተወከለ አይታወቅም። የተለያዩ የፋኖ አደረጃጀቶች “አማራን ለመሸጥ፣ ኢትዮጵያን ለማፍረስ አልታገልንም” በማለት እየተቃወሙት ነው። እስክንድር ነጋም ስለውሳኔው ከተወሰኑ አመራሮች [እነ ዘመነ ለማለት ነው] በስተቀር የሚያውቁት ነገር እንደሌለ አመልክቶ “ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበር በታሪክም ያስጠይቃል” ብሏል። ይህንኑ በማስገንዘብ ባለሰባት ነጥብ ደብዳቤ ለአፋብን ስራ አስፈጻሚ መላኩን አመልክቷል።

“ህብረት ማለት አብሮ መኖር፣ ያለ አንዳች ልዩነት የሰውን ልጅ በሰውነቱ ማክበር ነው። ኢትዮጵያ ‘አፋኝና ቅኝ ገዢ’ ያሏትን ኤርትራዊያንን ጨምሮ፣ የሶማሊያ፣ የሱዳን፣ እንዲሁም የነርካታ አገር ዜጎችን አቅፋ እያኖረች ነው። ከጉሊት ድንች ንግድ ጀምሮ እስከ ከፍተኛው… እንዲሁም በመንግስት መስሪያቤት ተቀጥረው እና የመንግስት ቤቶች ውስጥ ከዜጋ በላይ ሆነው የሚጠቀሙ ያሉባት አገር ናት፤ እንዲህ ዓይነት ወግ የሌለው ሻዕቢያ ያቋቋመው ጽምዶ፣ ሳይጀመር የፈረሰ ቢሆንም ዓላማው ግልጽ ነው። ከእፉኚት እርግብ የሚጠብቅ ሞኝ የለም” የጋራ መድረክ አባል

አፋር እንዳለበት ቢገልጽም፣ ወደ ኤርትራ የሸሹት የአፋር ተወላጅ በስደት ካሉበት ኤርትራ እንደገለጹት ያላቸው ኃይል እዚህ ግባ የማይባል ነው። ወደ ኤርትራም የሄዱት በደሞዝ ክፍያ በተፈጠረ አለመግባባት ነው። ሻዕቢያ ያደራጀው ይህ “ጽምዶ” የተሰኘ የሽብር ኃይሎች ስብስብ በጠብ መንጃ አልሆን ስላለ በፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሰፊ ቅስቀሳ እንዲሰራ መመሪያ ማስተላለፉን፣ ስብሰባው ላይ የተገኙ ጠቅሰን ዘግበን ነበር። 

የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች “ጥምረቱ ስጋት ባይሆንም፣ ቅዠታቸውን ተግባራዊ ለማድረግ የተነቀሳቀሱ እለት እንደ ሻማ እናቀልጣቸዋለን” ከማለት ውጪ ሌላ ዝርዝር ጉዳይ አያነሱም። ከመንግስት ወገን በይፋ መግለጫም ሆነ ምላሽ የማይሰጠው ይህ በህዝብ ለህዝብ መተሳሰር ስም የተመስረተ ጥምረት፣ አዲስ የሚዲያ አስተባባሪ እንደተሾመለት ተሰምቷል።  

“ምንጩ ሌላ ቢሆንም ከፋይ ያዛል” የሚሉት ወገኖች፣ ሻዕቢያ በኢትዮጵያዊያኑ የሚዲያ ክንፎች ላይ ስለሾማቸው አዲስ አስተባባሪ ለማስረዳት እንኳን ፈቃደኛ አልሆነም ይላሉ። በስብሰባ ሳይሆን በቀጥታ በሻዕቢያ የተሾሙት ሰው ከሹመታቸው ጎን ለጎን ተቃውሞ ተነስቶባቸዋል። እሱም ለሻዕቢያ ከቁብ የሚገባ አይደለም ተብሏል።  

የኤርትራን መንግሥት (ህግደፍ) “አምባገነን እና ለውጥ የማይቀበል፣ አፋኝ፣ ኤርትራን ወደ ዘመነ ድንጋይ የመለሰ፣” ብለው ይገልጹ የነበሩ፣ በኤርትራ መንግሥት ላይ ማዕቀብና የዲፕሎማሲ ጫና እንዲደረግ ከሚመስሏቸው ጋር ሲሞግቱ ከሃያ ዓመት በላይ ያሳለፉ፣ አሁን ግን “ማዕቀብ ህዝቡን ጎዳ እንጂ ለውጥ አላመጣም” በሚል ከሻዕቢያ ጋር ላለፉት ሶስት ዓመታት ግለ ሂስ አካሂደው መስራት የጀመሩት አዲሱ የሚዲያ ፊት አውራሪ፣ ኢትዮጵያ ላይ የሚዲያ ጦርነት እንዲያስተባበሩ ተመድበዋል። የኢሳያስ አምባገነናዊ መንግስትን “መንግሥት የለውጥ አካል መሆን አለበት፤ አብሮ መስራት ይገባል” የሚል የአቋም ለውጥ ካደረጉ ጀምሮ በዲያስፖራ ኤርትራዊያን ተቃዋሚዎች ዘንዳ አቋማቸው እንደ ክህደት ተቆጥሮባቸዋል። 

እኚህ “መርህ አልባ” የሚባሉት፣ የቆሙለትን የትግል መርህ የካዱ መሆናቸውን በማንሳት የሚተቹት፣ “ከሃጂ” በሚል አብረዋቸው የሻዕቢያን አፋኝ አገዛዝ ከሃያ ዓመት ሲታገሉ የቆዩት ባልደረቦቻቸውና የጸረ ሻዕቢያ ትግል አጋሮቻቸው የሚወነጅሏቸው አቶ ዳንኤል ተክላይ፣ ኤርትራዊ ሲሆኑ በፖርት ሱዳን በተደረገ ኢትዮጵያን የመበተን ስብሰባ ላይ የ“ጽምዶ” የሚዲያ ፊት አውራሪ ሆነው መሾማቸውን እሳቸው ከሚያስተዳድሯቸው ሚዲያዎች አንዱ በሆነው የጽምዶ ገጽ ላይ ይፋ አድርገዋል።  

“….. ዛሬ ጽምዶ (Ximdo) ወደ ዓለም አቀፍ እውቅና የሚያደርገውን ጉዞ ለማፋጠን በምናደርገው ጥረት ውስጥ ጉልህ ሚና እንድትጫወቱ ታላቅ ኃላፊነት ጥለንባችኋል” በሚል ጥሪ የሚያቀርበው የማስተዋወቂያ የግርጌ ማስታወሻ፣ “የዓለም አቀፍ እውቅናው መንገድ በዓላማና በተደራጀ ሁኔታ መመራቱን ለማረጋገጥ፣ የኤርትራ ኔክስት (EritreaNEXT) ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ዳንኤል ተክላይን ኦፊሴላዊ ተወካያችን አድርገን መሾማችንን በደስታ እንገልጻለን። በዚህም መሠረት አቶ ዳንኤል ተክላይ በሚፈለገው ደረጃ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቀርቡ ቃለ-መጠይቆችንና የማስተዋወቅ ሥራዎችን ጨምሮ ሁሉንም ከሚዲያ ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎችን ይመራሉ፣ ያጠናክራሉም” በማለት በፖርት ሱዳን በተደረገ ስብሰባ መሾማቸውን ያበስራል።  

አቶ ዳንኤል አገሪቱ ሕገ-መንግሥታዊ መዋቅር የምርጫ ስርዓት ሳይበጅላት ከሰላሳ ዓመታት በላይ ወደ ጨለማ ማዝገሟን፣ የሕግ የበላይነትና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ ነፃ የዜና ማደያዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ መታገዳቸው፣ አያሌ የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲሰወሩ መደረጋቸውን በመዘዘር ሲታገሉ ነበር። “ጥያቄው ምን ለውጥ ተገኝቶ ነው ዛሬ የሻዕቢያ የሚዲያ ክንፍ አዝማች ሆነው፣ ለሻዕቢያ ለመስራት የተስማሙት” በማለት በኖርዌይ የሚገኝ የኢሳያስ አገዛዝ ተቃዋሚ ይናገራሉ።  

ገደብ የሌለውና በግዳጅ የሚፈጸመው ብሔራዊ ወታደራዊ አገልግሎት የበርካታ ወጣቶችን ሕይወትና ተስፋ በማጨለም፣ ለከፍተኛ የሰዎች ስደትና ለቤተሰብ መፍረስ ምክንያት የሆነው፣ ብሚከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ አገሪቱን ወደ ድህነትና ውድቀት ያመራ፣ መንግሥት የሚከተለው የውጭ ፖሊሲ አገሪቱን ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያገለለና ቀጠናዊ አለመረጋጋትን የሚፈጥር በመሆኑ ኢሳያስ የሚመሩትን አገዛዝ አምርረው የሚተቹ። አቶ ዳንኤል ከዚህ ትግል ታጥፈው በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስም ለተቋቋመው ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ህብረት ሚዲያ መሪ ሆነው መሾማቸውን በርካቶችን አስገርሟል። 

“ኤርትራ፣ ትግራይና አማራ አንድ ላይ ከፈለግን አገር እንሆናለን” የሚለውና ኢትዮጵያ ስትበታተን የማየት ምኞት እንዳለው በገሃድ በራሱ ሚዲያ የሚናገረው ስታሊን የሚባለው የህወሃት ሚዲያ አጋፋሪ፣ አቶ ዳንኤልን እንደማይቀበላቸው አመልክቷል። በፖርት ሱዳን ስብሰባ ህወሃት አልነበረም ስለዚህ ሹመቱ በኤርትራ በኩል ብቻ ነው የሚል መቃወሚያ አለው። በሚለቃቸው ቪዲዮዎች “ጮርቃ ፖለቲከኛ” በሚል እንደ መዝናኛ ወይም ኮሜዲያን የሚወሰደው ስታሊን አስመራ ደርሶ ኢሳያስን ጨብጦ መመለሱ አይዘነጋም። ስታሊን አስመራ ደርሶ ሲመለስ “የናፈቀኝን ሜሎቲ ቢራ ጠጣሁ” ማለቱ የዛን ሰሞን ቀልድም ነበር።  

የተለያዩ አስተያየት ያሰባሰበው የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ እንዳለው ሻዕቢያ ከሚመራቸው ኢትዮጵያዊ ቆዳ ከለበሱ ሚዲያዎች መካከል አንዱ የሆነው የአንከር ሚዲያ ባለቤት መሳይ መኮንን “ሻዕቢያ አለቃ ሾመልን” በማለት ማሽሟጠጡ ተሰምቷል። ከመሳይ ጋር የሚቀርቡ እንደተናገሩት “እንዴት እሱ ይሾምብናል” በማለት ምክንያቱን ግልጽ ሳያደርግ ቅሬታውን አሰምቷል። ከአንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ እንደሚመክር አመልክቷል። 

አቶ ስታሊን፣ አርበኛ መሳይ መኮንን፣ ቀንዲል የሚባለው የሻዕቢያ ሚዲያ ሁሉም ሚዲያዎች ሻዕቢያ የሚመራቸውና የስራ መደብ በሚያወርድላቸው በአቶ ነዓምን በኩል እንደነበር አዲስ ሪፖርተር የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ መርሃግብርና የተናጋሪዎች ዝርዝር ከአጀንዳው ጋር አንድ ላይ የሚደለደልበትን ዝርዝር ይፋ በማድረግ ስትገልጽ ቆይታለች። 

አዲሱ የሚዲያ ዘርፍ አስተባባሪ ሆነው የተሾሙትና ሻዕቢያን ላለፉት ሃያ ዓመታት ሲቃወሙ የነበሩት ዳንኤል፣ የአቶ ነዓምን አለቃ ይሁኑ አየሁኑ እስካሁን አልታወቀም። ሻዕቢያ ያደራጀውን በግንቦት የተከናወነውን ምርጫ ለማጨናገፍ ተቋቁሞ የነበረውን “የአመጽ አደራጅ የጋራ መድረክ” በዋናነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ነዓምን ምርጫው እንዲደናቀፍ ይህ ነው የሚባል ስራ አለመስራታቸው እንዳስገመገማቸው ጠቅሶ የዋሽንግቶን ተባባሪያችን ማመልከቱ አይዘነጋም።  

እንደ እነ መሳይና ሳታሊን በገሃድ “ጽምዶ ንኝ” ሳይል አብሮ እየሰራ ያለው ሃብታሙ አያሌውም “በእኛ በኩል ያሉት ታጣቂዎች አልነገሩንም” በማለት ሹመቱ በሻዕቢያ ብቻ የተከናወነ መሆኑን ሲናገር ተደምጧል።  

አቶ ዳንዔል በፖርት ሱዳኑ ኢትዮጵያን የማበጣበጥ ሴራ ስብሰባ ላይ መሾማቸው ይፋ መደረጉን ተከትሎ፣ የተለያዩ ሚዲያዎችን ለማቅረብ /የሎቢ ስራ እየሰራ መሆኑን፣ አብረው እንዲሰሩ ለሚመለመሉት ሚዲያዎች ክፍያ እንደሚፈጸም፣ በሚቀርብላቸው የፕሮፓጋንዳ ሰነድ አማካይነት ተናበው ኢትዮጵያን በማወክ ተግባር እንዲሳተፉ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኝ ተባባሪያችን አመልክቷል። የፕሮፓጋንዳው ዋና ዒላማ “ሌሎች ተባብራቹኽ የኦሮሙማን መንግስት አስወግዱ” በሚል እንደሆነም ታውቋል።  

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related