ህወሓት የሰነዘረው ክስ መነሻ “የኦባሳንጆ የትግራይ ምልልስ በጽምዶ ውስጥ ያሉትን ቡድኖች ጥርጥር ውስጥ ስለከተታቸው ነው” – ኦባሳንጆ ህወሃትን ልማደኛ አሉት

Date:

ህወሃት አሁን ላይ በራሱ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም። በቅርቡ በተካሄደው የአስመራ ስብሰባ ጦርነት እንዲከፍት ታዟል። ኦባሳንጆ መቀለ መመላለሳቸው ችግር የፈጠረው በዚሁ በሻዕቢያ ውሳኔና መነሻነት ነው። አቶ አማኑኤል “የኦባሳንጆ የመቀለ ምልልስ የጽምዶን አባላት ጥርጥር ውስጥ ከቷል” በማለት ያረጋገጡት ይሕንኑ ሃቅ ነው። ህወሃት ከኤርትራ የውክልና ጦርነት፣ ለግብጽ ታሪካዊ ኢትዮጵያን የማጥፋት ዕቅድ መጠቀሚ እየሆነ መሆኑን ተቀማጭነታቸው አሜሪካ የሆነ የተቃዋሚ አመራሮች ሳይቀሩ እየተቹ ነው። ሻዕቢያ ከፈተኛ በጀት የሚያፈስበት የጋራ መድረክ ውስጥም መሰነታተቅ ፈጥሯል

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — “የኦባሳንጆ ምልልስ ሻዕብያን በጣም አበሳጭቷል፣ አስግቷል” በሚል ለተሰጠው አስተያየት የሚደግፍ መግለጫ አቶ አማኑኤል ሰጡ። ኦባንሳንጆ የህወሓት አመራሮች ለራሳቸውን አጀንዳ እንዲመች ሲሉ የሳቸውን ጥረት ለማጣጣል ሲሞክሩ የአሁኑ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ጠቅሰው ምክር ለግሰዋል።

አቶ አማኑኤል በትግራይ ቲቪ ቀርበው ሽምግልናው የከሸፈበትን ዋና ምክንያት ይፋ አድርገዋል። እሳቸው እንዳሉት የፕሪቶሪያው ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ኦባሳንጆ ወደ ትግራይ መመላለሳቸው ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ፋኖ፣ ኦላ፣ እና እዚህ ግባ የሚባል ተዋጊ የሌላቸው አንዳንድ የነጻ አውጪ ወዘተ አሰባስቦ የተቋቋመውን “ጽምዶ” የተሰኘ ጥምረት ጥርጣሬ ውስጥ ካቷል።

ተቀማጭነታቸው አሜሪካ የሆኑ የህወሃት ወኪሎች ሽምግልናውን ተከትሎ ሻዕቢያ የከረረ ተቃውሞና ማሳሰቢያ በመስጠቱ አቶ አማኑኤል አሰፋን በቲቪ በይፋ የተጀመረውን ንግግር በመቃወም መግለጫ እንዲሰጡ ተደርጓል። የዋሽንግቶን የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ እንዳለው አቶ አማኑኤል “የኦባሳንጆ ምልልስ በትብብር ውስጥ ያሉ አካላትን ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ ለማድረግ የታሰበ የፖለቲካ ሴራ ነው” ያሉትም በዚሁ መነሻ ነው።

“ሽምግልናውን በጽምዶ ውስጥ የተካተቱትን እርስ በርስ ጥርጥር ውስጥ እንዲገቡ ለማድረግ ነው” በማለት አቶ አማኑኤል ያስታወቁት፣ “ትብብር ፈጥረዋል የተባሉት ቡድኖችና አገራት ህወሃት ሳያውቅ የፌደራል መንግስቱ ሆን ብሎ ለሴራ ያደረገው እንጂ እኔ የለሁበትም” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነ የተባባሪያችን መረጃ ያመልክታል።

ይህወሃት መግለጫ የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በሽምግልና ሂደቱ ውስጥ ለፌዴራል መንግሥት የወገኑ እና ገለልተኛ መሆናቸውን ጥያቄ ውስጥ እንደከተተ አመልክቷል። ገለልተኛ አደራዳሪ እንዲመደብ፣ ይህ ሲሆን ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ያመለከተው ህወሃት ኦባሳንጆ በተደጋጋሚ የናይጄሪያ የቢያፍራ ጦርነት ልምድን እንደምሳሌ ማቅረባቸውን ተቃውሟል።

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በኃይል ያፈረሰው ቡድን፣ ባወጣው በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሃት መካከል ያለው የሰላም ሂደት እንዲታደስ ከተፈለገ ገለልተኛና ነፃ አደራዳሪ እንዲሰየም መግለጫውን ያሰራጨላቸው ዓለም ዓቀፍም ሆነ አህጉር አቀፍ ተቋማት ይህ እስከተጻፈ ድረስ ምላሽ አልሰጡም።

ኦባሳንጆ የህወሓት አመራሮች ለራሳቸውን አጀንዳ እንዲመች ሲሉ የሳቸውን ጥረት ለማጣጣል ሲሞክሩ የአሁኑ የመጀመሪያው እንዳልሆነ በመጥቀስ በፕሪቶሪያው ድርድር ወቅትም ተመሳሳይ ሙከራ አድርገው ሳይሳካላቸው እንደቀረ በማመልከት ምክር ለግሰዋል።

“በአንድ ግጭት ውስጥ የቀረቡ ፍላጎቶች ተቀባይነት ካላገኙ ወይም አንድ ወገን የሚጠብቀውን ካልተሳካ መፍትሄው አደራዳሪውን ማጥቃት ወይም አቋሙን ጥያቄ ውስጥ መክተት ሳይሆን፣ አስማሚ ነጥብ ላይ እስኪደረስ ንግግርን መቀጠል ነው” ያሉት ኦባሳንጆ፣ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የሰላም ጥረት ቁርጠኛ አቋም እንዳቸው እንዲሁም ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በአፍሪካ ኅብረት የሚመራው የሰላም ጥረት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ሌላ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ የሁሉንም ወገኖች እርምጃ በቅርበት እንዲከታትል ጥሪ አቅርበዋል።

ኦባሳንጆ በጽህፈት ቤታቸው በኩል ይፋ ባደረጉት መግለጫ “ትኩረትን ለማግኘት ጥንቃቄ የሚፈልጉ እና ምሥጢራዊ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ኃላፊነት የጎደለው ነው” ብለዋል። አክለውም በማሸማገል ሂደታቸው ከፌደራል መንግሥቱ ትዕዛዝ እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። 

ህወሃትም ሆነ ኦባሳንጆ ለሰነዘሩት አስተያየት ከመንግስት ወገን ምንም ዓይነት ምላሽ አልተሰጠም። መንግስት ህወሃት ለሚያወታቸው በርካታ መግለጫዎች ምንም ዓይነት ምላሽ የማይሰጥበት ምክንያት ምን እንደሆነም በየትኛውም መድረክ በይፋ አይገለጽም።

“ጽምዶ” በሚል የትግርኛ ምህጻረ ቃል የተሰየመው እና የውጭ አገራት ሳይቀሩ የተካተቱበት ህብረት በዓላማ፣ በትግል መርህ፣ በርዕዮትና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተለያየ አቋም ያላቸው ቡድኖች የተካተቱበት፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚመሩትና የሚደግፉት አገር የሚበታትን ህብረት መሆኑ እየተገለጸ በስፋት እየተተቸ እንደሆነ ይታወቃል።

መንግስትን በመቃወም የሚቃወሙ፣ በራሱ ጥምረቱ ውስጥ ባሉ ድርጅቶች ውስጥ በስፋት ተቃውሞ እየተነሳበት ያለው ጥምረት ባዘጋጀው ይፋዊ ድርገጹ ላይ የሻዕቢያ የፕሮፓጋንዳ ክፍል እንደሚመራው መገለጹን፣ ለዚሁም ኤርትራዊ ዜኘት ያለው የቀድሞ ተቃዋሚ እንደተሾመለት መዘገባችን ይታወሳል። በዚሁ ዌብሳይት ላይ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ ወዘተ በጥምረቱ ውስጥ መካከተታቸው ተመልክቷል።

ራሱን ነጻና ሃቀኛ ተደራዳሪ አድርጎ ያቀረበው የህወሃት መግለጫው በትግራይ ያለውን የፖለቲካና ወታደራዊ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ስለሚነሳበት ክስ ምንም አላለም።

የፕሪቶሪያ ስምምነት በትግራይ ክልል እስከ ምርጫ ድረስ የሚቆይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ያስገድዳል። በዚሁ አገባብ የክልሉ የሽግግር አስተዳደር በ2023 ተቋቁሞ አቶ ጌታቸው ረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሰይመው እንደነበር ይታወሳል።

የህወሃት ውስጣዊ ክፍፍል ወደ ትጥቅ ግጭቶች ተሸጋግሮ፣ አዲግራትን ጨምሮ በርካታ ከተሞች የታጠቁ ቡድኖች ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተዘግቧል። ከዚያም አቶ ጌታቸው ረዳ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ኃላፊ ተደርገው ነበር።

ከዚያ በኋላ የትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት እንደገና ተመስርቶ የህወሃት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡ ተዘግቧል። ይህም በአንድ ወቅት በፕሪቶሪያ ስምምነት የተቋቋመውን የሽግግር ሥርዓት በተግባር ዳግም የሚፈታተን የፖለቲካ ለውጥ እንደሆነ አልጃዜራ ሲዘግብ “ስምምነቱ በመሳሪያ ኃይል በተደረገ የስልጣን ሽግግር የሰላም ስምምነቱ አደጋ ገጥሞታል” በማለት ነበር።

የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ ክስ

ከዚህ በተጨማሪ በ2018 ዓ.ም በትግራይ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እየተካሄደ መሆኑን የሚገልጹ ክሶች በተለያዩ ምንጮች ቀርበዋል። የሰብዓዊ መብት ተቋም Human Rights Watch በሐምሌ 2018 ባወጣው ሪፖርት በትግራይ ከሚያዚያ ጀምሮ አፈሳ መጠናከሩን፣ ከእነሱም መካከል እድሜያቸው እስከ 15 ዓመት የሚደርሱ ህጻናት፣ በግዳጅ ለውትድርና እየተመለመሉ መሆኑን ገልጿል። ኦባሳንጆ በትግራይ ምልልሳቸው ይህንን በማንሳት ዕድሚያቸው ለጦርነት ያልደረሱ ህጻናትን እንዳያስጨርሱ መምከራቸው ተሰምቷል።

የጀርመኑ Stiftung Wissenschaft und Politik በበኩሉ በሰኔ ወር የትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት ወታደራዊ አፈሳን የሚያጸና ሕግ ማጽደቁንና፣ አፈርሳው በዶክተር ደብረጽዮን መሪነት የሚመራና ማዕከል እንደተቋቋመለት ዘግቧል። ዘገባው ይህ ሁሉ የሚደረገው ለጦርነት ዝግጅት እንደሆነ አመልክቷል።

የህወሃት አመራሮች በተደጋጋሚ በተለያዩ መድረኮች ካድሬዎቻቸውን በመሰብሰብ፣ “የብልጽግና መቃብር ተቃርቧል” በማለት በቅርቡ “በብልጽግና መቃብር ላይ የትግራይ ህልውና ተግባራዊ ይደረጋል” በማለት መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ኦባሳንጆ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ወድ ትግራይ ማምራታቸውን የሚገልጹ ወገኖች፣ የህወሃት መግለጫ “የፌዴራል መንግሥት ለጦርነት እየተዘጋጀ ነው” በሚል መክሰሱ አስገርሟቸዋል።

ቀደም ሲል አማራና አፋር ክልልን የወረረው ህወሃት “ጄኒሳይድ ተፈጸመብኝ” በማለት ግራ የሚያጋባ መግለጫ ሲሰጥ እንደነበር የሚገልጹ፣ “ህወሃት ደብረ ሲና ድረስ ሲመጣ፣ ከዚያም አልፎ አዲስ አበባ መንግስት እስኪገለብጥ መንግስት እጁን አጣጥፎ እንዲጠብቀው ነበር ፍላጎቱ” በማለት ዛሬም ድረስ ግራ መጋባታቸውን ያመለክታሉ። እነዚህ ወገኖች ህወሃት ያወጣው መግለጫ ከግብጽ በሱዳንና በኤርትራ መሳሪያ እየተጋዘለት፣ ወታደር በገፍ እየመለመለ፣ መሳሪያ ወደተለያዩ ግንባሮች እያጋጋዘ “ዝም በሉኝ፣ ዳግም ልውረር፣ ዳግም አማራና አፋርን ላፈራርስ” የሚል ማመልከቻ ብለውታል።

የኤርትራና የሱዳን ጉዳይ

የህወሃት ከኤርትራና ከሱዳን ጋር የወታደራዊ ትብብር ወይም ጥምረት የፈጠረው ህወሃት፣ አካሄዱና ህብረቱ ለኢትዮጵያ ስጋት ከሆኑ ኃይሎች ጋር በመሆኑ፣ ስብስቡ ያሰበውን ተግባራዊ ለማድረግ ሲነቅሳቀስ ወይም ልወመንቀሳቀስ የሚኦከረ መሆኑ ሲረጋገጥ የአገር መከላከያ ይመጥናል የሚለውን ርምጃ እንደሚወስድ በተደጋጋሚ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።

በህወሃት፣ በኤርትራና በሱዳን መካከል ስለፈጠረው ጥምረት እና ትስስር አስመልክቶ የሚውጡ ሪፖርቶች ከሩቅ ሳይሆን መነሻቸው ከራሱ ከህወሃት አንድበትና ተባባሪዎች በመሆኑ አሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረት በተደጋጋሚ ምክር መለገሳቸውን ጠቅሰው በትፋ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርም በሐምሌ ወር በኤርትራ፣ በህወሃትና በሱዳን መካከል እየተፈጠረ ስላለ የተባለ ጥምረት አስመልክተው በይፋ  መናገራቸውም አይዘነጋም።

በሕገመንግሥቱ መሠረት የኢትዮጵያን የውጭ ፖሊሲ መቅረጽና የውጭ ስምምነቶችን መፈጸም፣ ማጽደቅ ወዘተ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ሲሆን፣ ብሔራዊ መከላከያንም ማቋቋምና ማስተዳደር በፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ሥር ብቻ የሚከናወን በመሆኑ ክልሎች በዚህ ተግባር ተሳትፈው ሲገኙ የእርምት ርምጃ እንደሚወሰድ ያመለከቱ እንደሚሉት መንግስት ህወሃትን ከልክ በላይ ታግሷል።

በዚህ የተወሳሰበ ሁኔታ ውስጥ የሚገኘው ህወሃት ያነሳው ዋነኛ ጥያቄ አደራዳሪው ከሁለቱም ወገኖች ነፃ መሆን እንዳለበት ነው።  የፕሪቶሪያ ስምምነት እስከ ምርጫ ድረስ የሚቆይ የሽግግር አስተዳደርን እንዲቋቋምና በኋላም በሕጋዊ ምርጫ የክልሉ አስተዳደር እንዲቋቋም ያስቀመጠና የቀደመው ምርጫ ውድቅ እንደሚሆን ስምምነት የተደረሰበት ነው።

ስለዚህ የአሁኑ ችግር በአደራዳሪ ስም የፖለቲካ ወገንተኝነትን ማጠናከር ሳይሆን፣ ሁለቱንም ወገኖች በእኩል የሚጠይቅ፣ የፕሪቶሪያ ስምምነትን እና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓትን መነሻ የሚያደርግ የሰላም ሂደት መፍጠር መሆኑን ተንታኞች ያስገነዝባሉ። ህወሃት መቀበል የማይችለው ይህንን ሃቅ እንደሆነም ይታቻሉ።

በአሁኑ ወቅት የትግራይ ጉዳይ በሰላምና በጦርነት መካከል ባለ አደገኛ የግራጫ ዞን ውስጥ መግባቱን የሚያስጠነቅቁ የውጭ ተመራማሪዎችና አገራት ጥቂት አይደሉም። በተለይም የግዳጅ ምልመላ፣ የታጠቁ ኃይሎች እንቅስቃሴና በሁለቱም ወገኖች የሚሰማው የጦርነት ዝግጅት ክስ አደጋውን እያሳደገ መሆኑ ተጠቁሟል (SWP) በተደጋጋሚ ከወተወቱ ጥናት ተኮር ሚዲያዎች መካከል ይጠቀሳል።

በመሆኑም የህወሃት መግለጫ የፌዴራል መንግሥትን ክስ በመቃወም ገለልተኛ አደራዳሪ እንዲመደብ ቢጠይቅም፣ በተመሳሳይ ጊዜ በራሱ ላይ የሚቀርቡትን የጊዜያዊ አስተዳደር መፍረስ፣ የፖለቲካ ሥርዓትን መቀየርና የወታደራዊ ምልመላ ክሶች መነሳታቸው የማይቀር ነው። ህወሃትን በመቃወም ወደ ሃራ መሬት የከተሙ፣ ወታደራዊ ኃይል የሚያደራጁ፣ በተቃውሞ ጎራ ተሰባስበው ምክር ቤት ያቋቋሙ በሙሉ ህወሃት አሁን በያዘው መንገድ የትግራይን ህዝብ ከማስጨረስና የተረፈውም የትግራይ ሃብትና ንብረት ከማውደም የዘለለ ምን ውጤት እንደማያስገኝ ደጋግመው እየወተወቱ ነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የቻይናና ግብፅ ባለ21 ነጥብ ስምምነት…የናይል ውኃና የቀይ ባሕር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ምን መልዕክት አለው?

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ —  የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ...

ኤፍሬም ማዴቦ “ጽምዶ ኢትዮጵያን መንግሥት አልባ ያደርጋል” ያሉበት ሚስጢር ታወቀ፤

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ —  ኤፍሬም ማዴቦ “ሀገሬ እንደ...

“ጦርነት መፍትሄ እንደማያስገኝ በህይወቴ በተግባር አይቻለሁ፣ ይህን እመሰክራለሁ” ሜ.ጄ ተክለብርሃን

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ —  “በህይወቴ በተግባር ያየሁትና...

ልደቱ በድብቅ ሲሰራበት የነበረውን ግብጽ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ … ያሉበትን ጽምዶ “የኢትዮጵያ ትንሳዔ” አለው

አሁን አሁን ፈርሰናል። የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ / ህወሃት፣...