ወልቃይትን ለመቆጣጠር ህወሃት ሰፊ ኃይል አሰልፎ ጦርነት ከፈተ፤ 140 ቁስለኛና ምርኮኛ ተመዝግቧል፤ “ሞክረዋል አልተሳካላቸውም፤ አይሆንምም” አዋጊ መኮንን

Date:

አዲስ ሪፖርተር ወልቃይት —ህወሃት በዛሬው ቀን ሌሊት ላይ በአዲ ጎሽም አቅጣጫ ጦርነት መክፈቱን ግንባር የሚገኙ ለአዲስ ሪፖርተር አስታወቁ። ለሶስት ሰዓታት በተካሄደውና በተጠናቀቀው ጦርነት ክህወሃት ወገን ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተመልክቷል።

በዚሁ ሊነጋጋ ሲል በተጀመረው ጦርነት፣ የህወሃት እቅድ ወደ ወልቃይት ዘልቆ መግባት ነበር። ዜናውን ያቀበሉት ክፍሎች እንዳሉት የአገር መከላከያና የአካባቢው የጸጥታ መዋቅር አስቀድሞ ሙሉ መረጃ ስለነበራቸው ህወሃት የከፈተውን የተቀናጀ የማጥቃት ጦርነት ቀልብሰዋል።

የሃ ሚዲያ ያነጋገራቸው ከፈተኛ መኮንን ” …. አዎ ሞክረዋል። አይሆንም። አልተሳካላቸውም። ያለ የሌለ ኃይል አሰልፈው በሌሊት ማጥቃት ሰንዝረው ነበር። በተወሰደው መልሶ ማጥቃት 144 የሚሆኑ ታጣቂዎቹ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነዋል፤ የቆሰሉትን መከላከያ እርዳታ እያደረገላቸው ነው” ብለዋል። አክለውም ጦርነቱ አሁን ላይ መቆሙን አመልክተዋል።

ለአዲስ ሪፖርተር መረጃ የሰጡ እንዳሉት የህወሃት ተዋጊዎች ምንም እንኳን በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ቢሰነዝሩም፣ የአጻፋውን ርምጃ መቋቋም ስላቃታቸው አፈግፍገዋል። በማፈገፈ ላይ እያሉ ተቆርጠው ለከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ መዳረጋቸውን አመልክተዋል።

በጦርነቱ ህይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ አንድ መቶ አርባ አራት በላይ ምርኮኛ መመዘገቡን ያመለከቱት ወገኖች እንዳሉት ያፈገፈገው የህወሃት ጦር ለጊዜው እንደተበታተነ አመልክተዋል።

“የፌዴራል መንግሥቱ እያደረገ ያለውን የጦርነት ትንኮሳና የድሮን ድብደባ በትግስት ይዘን ስራችን እያከናውን የምንገኘው” በማለት ሰሞኑን መግለጫ የሰጡት የህወሓት ወታደራዊ መሪ ጄ.ፍስሃ ማንጁስ ቴክኖሎጂ/ድሮን/ጦርነት እንደማያስቆምና ባለ ድል እንደማያደርግ አስታውቀው ነበር። በዚሁ መግለጫቸው “ለህልውናችን ብለን የምናካሄደውን ትግል አሸንፈን ለመውጣት ሁሉንም ነገር በማስተካከል እየተዘጋጀን ነው ያለነው፤ ሁሉም ነገር አንዳለቀ ደግሞ ያኔ የሚሆነው ይሆናል። አንደምናሸንፍም ኧርግጠኞች ነን” በማለት ቀኑን መናገር ባይችሉም በቅርቡ ወልቃይትን እንደሚያስመልሱ አስታውቀው ነበር።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related