አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — ”ከሁሉም በላይ ትግላችን አጠናክረን አሸናፊ ሆነን እንወጣለን፣ ይህንን ጠብቀን ከቀጠልን የተሻለ አቅምና ጥንካሬ በመያዝ የተሻለ ተፅዕኖ ፈጣሪነት እና ተደማጭ የምንሆንበት አጋጣሚ ይፈጠራል” ይላል ህወሃት ያዘጋጀው እና ለተዋጊዎቹ ያሰራጨው ቀልብ መሰብሰቢያና የሞራል ማነቃቂያ ሰነድ።
“የአገር መከላከያን ‘የብልጽግና፣ የአብይ ሰራዊት በማለት ደጋግማቹህ በመጥራት ከህዝብ ለዩት’ የተባሉት ሚዲያዎች በስፋት ጽምዶን “የሰላም ዋስትና” አድርገው እንዲያቀርቡ መመሪያ ከተላለፈ ሰነባብቷል። በዚህ መመሪያ መሰረት ሰፊ የቅሰቀሳ ስራ እንዲሰራ መመሪያ የተሰጣቸው ተናበው ምክንያት በመፍጠር ጭምር አሁን ከሚሰሩት በላይ ተመዳድበው በፕሮፓጋንዳ እንዲረባረቡ መታዘዙን የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ አመልክቷል።
በዘፈን፣ በተቃውሞ አስመስለው “ጽምዶ ራሱን ለህዝብ ይግለጥ” በሚል ጫና በማሳደር ተናበው የሚሰሩት ሻዕቢያ ባደራጀው የጽምዶ የፕሮፓጋንዳ ክፍል የሚዘጋጅላቸውን መርሃ ግብር እያከናወኑ ነው።
“በኦሮሚያ ክልል የሚደረግ አንዳችም እንቅስቃሴ የለም። ኦሮሚያ ክልል የገባቹህ ዕለት ጉዳይ ሌላ ይሆናል” በማለት በገሃድ ዘመቻ የጀመሩትን የኦነግ ደጋፊና አባላት ጨምሮ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ሚዲያዎችና ፖለቲከኞች “ጽምዶ አገር አፍራሽ” መሆኑን በይፋ እየገለጹ ነው።
አገራቸውን የሚወዱ ፊት ለፊት ወጥተው “ዳግም አንታለልም” በማለት ህወሃትና ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በምን ደረጃ ተስማምተው እንደገደሏት በማስታወቅ ላይ ናቸው። ይህ በንዲህ እንዳለ ነው ጽምዶ ገበያ መሆኑ ከወደ ትግራይ የተሰማው።
“ፅምዶ ገበያ ነው፤ ሻጭና ገዢ የተገናኙበት ገበያ” እንደሆነ ብ.ጄ ፍስሃ ማንጁስ ናቸው የተናገሩት። ወልቃይት ጠገዴንና ጠለምት ነጻ እንደሚወጡ ማረጋገጫም ሰጥተዋል። የዘመነ ካሴ ፋኖ ግን ምንም አላለም። የገበያውን ተረት የሰሙ እነ ዝመነ የሚመሩትን ቡድን ” ገበያውን ተገበያይተዋል። ወልቃይት ጠገዴን ነው የተገበያዩት። ታሪክ የማይረሳው ክህደት ፈጽመዋል” ብለዋቸዋል።
“ወልቃይት ጠገዴንና ጠለምትን ነፃ እናወጣቸዋለን ብዬ ቀን ቆርጬ አሁን አልነግርህም። ጊዜው ሲደርስና እውን ሲሆን ማየቱ ነው የሚሻለው” ሲሉ ብ.ጄ ፍስሃ ማንጁስ መናገራቸው በፋኖ መካከል ያለውን ስንጥቅ አስፍቶታል።
“ፅምዶ ገበያ ነው፤ ሻጭና ገዢ የተገናኙበት ገበያ” እንደሆነም ይፋ አድርገዋል። ገበያተኞቹ ስለተሻሻጡት ጉዳይ ዝርዝር አልተናገሩም። ያደመጧቸው “ድሮም ይታወቃል” ብለዋል።
ብ.ጄ ፍስሃ ማንጁስ “ኦነግ ሸኔ ላለፉት ስምንት ዓመታት ከእኛ ጋር ነበር” ብለው፣ ሙሉ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሚለው የታጣቂ ቡድን ቃል አቀባይ ግን በይፋ አስተባብለዋል።
“የፌዴራል መንግሥቱ እያደረገ ያለውን የጦርነት ትንኮሳና የድሮን ድብደባ በትግስት ይዘን ስራችን እያከናውን የምንገኘው” ሲሉ የተደመጡት የህወሓት መሪ ጄ/ ፍስሃ ማንጁስ ቴክኖሎጂ ወይም ድሮን ጦርነት ሊያስቆም እንደማይችል አመልክተዋል። ይህን የተናገሩት ሰራዊቱ እየፈረሰና ጦርነት ቢነሳ እጁን እንደሚሰጥ መረጃ ስላለ ተስፋ ለመስጠት እንደሆነ ከትግራይ የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
ጄኔራሉ “ለህልውናችን ብለን የምናካሄደውን ትግል አሸንፈን ለመውጣት ሁሉንም ነገር በማስተካከል እየተዘጋጀን ነው፣ ሁሉም ነገር አንዳለቀ ያኔ የሚሆነው ይሆናል። አንደምናሸንፍም እርግጠኞች ነን” ብለዋል።
መቀለ ሆነው በሰጡት መግለጫ “ኦነግ ሸኔ ስምንት ዓመት ሙሉ ከመንግስት ጋር ሲዋጋ ከእኛ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ነበረው።አሁንም ግንኙነታችን እንደቀጠለ ይገኛል፤ አልተቋረጠም” ሲሉ ተደምጠዋል። ይህንን መግለጫ የሰሙና መረጃ እንዳላቸው የሚናገሩ ኦላ “የለሁበትም። ጽምዶን አላውቀውም” ማለቱን “ውሸታም” ሲሉ ተቃውመዋል።
ብ/ጄኔራል ፍስሃ ኪዳኑ “ፅምዶ ገበያ ነው፤ ሻጭና ገዢ የተገናኙበት ገበያ” በማለት ተጀመረ የተባለውን ጥምረት በገበያ ህግ አስደግፈው አስረድተዋል። አክለውም “ወልቃይት ጠገዴንና ጠለምትን ነፃ እናወጣቸዋለን ብዬ ቀን ቆርጬ አሁን አልነግርህም። ጊዜው ሲደርስና እውን ሲሆን ማየቱ ነው የሚሻለው” ብለዋል።
ይህ “በገበያ፣ ገዢና ሻጭ” ተመስሎ የቀረበው የጄኔራሉ አገላለጽ፣ አሁን በአማራ ስም ከህወሃት ጋር እየሰራ ያለው በዘመነ ካሴ የሚመራው ኃይል “በስውር ተስማምቷል” በሚል የሚቀርበበትን ክስ የሚያረጋግጥ ተደርጎ ተወስዷል።
ዘመነ ካሴ የሚመራው እና እየተከፋፈለ ያለው አፋብን የህዝብ ግንኙነት ሆኖ እያገለገለ ያለው አስረስ ማረ “ወልቃይት ሰላሳ ዓመት ደምና አጥንት የፈሰሰበት የትግል ውጤት ነው” በማለት መናገሩን ተከትሎ የህወሃት ሚዲያዎች በይፋ ማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ ሲሰጡት እንደነበር ይታወሳል።
የአስረስ ማረ ንግግር “ታክቲካል እና ጎንደር ተሸጠ” ለሚለው ከፍተኛ ተቃውሞ ማስተንፈሻ እንዲሆን ታስቦ የተደረገ መሆኑን በጎንደር የሚንቀሳቀሱ የድርጅቱ የተለያዩ አመራሮች አስታወቀው ነበር።
ለህወሃት ተዋጊዎች ለውይይት የተዘጋጀ ነው የተባለ ሰነድ ውስጥ እንደተጠቆመው ህወሃት በፈጠረው ጽምዶ ውስጥ ጥቅሙን ያሰላል። “ሉአላዊ” የሚለውን የትግራይን ድንበር እንደሚያስከብር በግልጽ አስቀምጧል።
ህወሃት የትግራይ ሕዝብን ክፉኛ ጎድተዋል ከሚባሉት ፋኖና ሻዕቢያ ጋር የፈጠረው ጥምረት ላስነሳበት ተቃውሞ ማብረጃ በሚል ለወታደራዊ ክንፉ በትግርኛ ቋንቋ ባዘጋጀው የመወያያ ሰነድ፣ “በአሁኑ ወቅት የጋራ ህልውና ስጋት ካለ፣ የቀድሞ ግጭቶች እና ልዩነቶች በጊዜያዊነት ተወግደው በጋራ መሥራት ይቻላል” ሲል ተዋጊዎቹን ለማሳመን ይጥራል። የሰነዱን ትርጉም እዚህ ላይ ተጭነው ሙሉውን ያንብቡ።
ሳይጀመር እንደፈረሰ የሚነገርለት “ጽምዶ” ኢትዮጵያን ሶስት ቦታ የሚቆራርጥ መሆኑን አቶ አባይ ግደይ የተባሉ የቀድሞ ታጋይ የተናገሩት የቪዲዮ መረጃ በማያያዝ መዘገባችን አይዘነጋም።
በሌላ ተመሳሳይ ዜና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጽምዶ በሚል ስያሜ ስለተመሠረተው ጥምረት የሚያውቀው ነገር እንደሌለና ድርጅቱም የጥምረቱ አካል እንዳልሆነ የድርጅቱ ቃል አቀባይ አስታውቀዋል። አዲስ ሪፖርተር በዚህ ጉዳይ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ ሌላ ዘገባ እንደሚያዘጋጅ ከወዲሁ ያስታውቃል።
ከዲያስፖራው ማኅበረሰብ ጋር በተካሄደ ውይይት ላይ የተገኙት የድርጅቱ ቃል አቀባይ አቶ ቀጄላ ሲራጅ እንደገለጹት፤ በድርጅታቸው ስም በጽምዶ ዙሪያ በሶሻል ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎች ይፋዊ አቋማቸውን እንደማይወክሉ ተናግረዋል።
አክለውም ይፋዊ መግለጫ ባልወጣበት ጉዳይ ላይ በግለሰቦች የሚሰራጩ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ተከትሎ መሄድ ተገቢ አለመሆኑን አሳስበዋል።
ቃል አቀባዩ የWBO መሪ ጃል መሮን ከሌሎች የፖለቲካና ድርጅት አመራሮች ጋር በማያያዝ የሚናፈሱ ወሬዎችን አስተባብለዋል። እሳቸው ይህን ቢሉም “መረጃ አለን” የሚሉ ጃል መሮ በይፋ ከህወሃት ጋር እንደሚሰራ ያረጋግጣሉ። ዝርዝር መረጃ በማቅረብ ጃል መሮ ለህወሃት እንጂ ለኦሮሞ እንደማይታገል ይናገራሉ። ከዚያም በላይ አልፈው “ኦሮሞ አለምሆኑንም ያስታውቃሉ። ጃልመሮ በተዘጋው የአሜሪካ ድምጽና በቢቢሲ እየቀረበ ማስተባበያ ይዘጋጅለት እንደነበርም አይዘነጋም።
“ጃል መሮ የትግል ሜዳ ላይ ይገኛል፤ ከየት መጥቶ ነው የዘመነ ምክትል ተደርጓል የተባለው?” ሲሉ የተሰራጩትን ዘገባዎች ተቃውመዋል።
ጽምዶ በሚል መጠሪያ በሚንቀሳቀሰው በዚህ ስብስብ ዙሪያ የሚነሱ ውዝግቦች እየተጋጋሉ የመጡ ሲሆን፣ ተቃዋሚ ወገኖች ጥምረቱ በኦሮሞና በሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ፖለቲካዊ ጥቅም ላይ ስጋት ሊፈጥር ይችላል የሚል ትችት በማቅረብ ላይ ናቸው። በየጊዜው ለኦሮሞ ጥቅም እንደሚታገሉ የሚገልጹ እንደሚሉት ከሆነ ጽምዶ የሚባለው ስብስብ የኦሮሞ መሬትን ረግጦ እንዲገባ አይፈቀድለትም።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






