ዳውድ ኢብሳና መረራ ጉዲና አለመታሰራቸውን አረጋገጡ፤ “በምርጫው ዋዜማ ታስረዋል ተብሎ መረጃ እንዲሰራጭ ዝግጅት ተደርጓል”

Date:

“አቶ ዳውድ ኢብሳና ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን ጨምሮ የሚታውቁ ፖለቲከኞች ታስረዋል” የሚል መረጃ በስፋት ለማሰራጨት በውጭ አገር ሕዝባዊ አመጽ ዝግጅት ማደረጉን እንቅስቃሴውን ውስጥ ህፕነው የሚከታተሉ አመለከቱ። ፓርቲዎቻቸው ስለመታሰራቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ፣ ይህን በሚናገሩበት ሰዓት ቢሮ አብረው እንዳሉ አመልክተዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ ለአዲስ ሪፖርተር የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳሉት አቶ ዳውድ ኢብሳ ቢሯቸው ናቸው። ስራቸውን እየሰሩ ነው። ፓርቲያቸውም የምርጫውን የመጀመሪያ ምዕራፍ እያከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ አመራር የህፖኑት አቶ ኦልባና ሌሊሳ በበኩላቸው፣” አብረን ቢሮ ውለናል። ለምሳ ወጥተው ነበር። አሁን በመስኮት እያየኋቸው ነው። ከምሳ ተመልሰው ወደ ቢሮ እየገቡ ነው” ሲሉ ተመሳሳይ ምላሽ ሰጥተዋል።

“አቶ ዳውድ ኢብሳና ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን ጨምሮ የሚታውቁ ፖለቲከኞች ታስረዋል” በሚል በስፋት እንዲሰራጭ ዝግጅት የተደረገው “በሚቻለው ሁሉ ምርጫውን ማስተጓጎል” የሚል አቋም የየዛው ግብረኃይል አመራር ነው።

የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ዲሲ ተባባሪ ዕቅዱ ኦሮሚያ ላይ ሁከት ለማስነሳት የተያዘውን ዕቅድ ለማቀጣጠል ተጨማሪ ግብአት እንዲሆን ታስቦ መሆኑን የዘወትር የመረጃ ምንጮቹን ጠቅሶ አመልክቷል።የተለያዩ ከግብረኃይሉ ጋር የሚሰሩ ሚዲያዎችና የማህበራዊ አውድ ክንፎቻቸው በቅብብል እንዲያሰራጩት ታስቦ የተያዘርው ዕቅድ ትናንት እንደተነገራቸው ያመለቱ ወገኖች፣ ይህን ዕቅድ ሁሉም የግብረኃይሉ አባላት እንዲሰሙት አለመደረጉን አመልክተዋል።

“በሰላማዊ ትግል ስም እስከ ሱዳን ዘልቀው ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር አብረው እየሰሩ ያሉ የግብረኃይሉ አመራሮች መኖራቸው ሲታወቀ መከፋፈል በመከሰቱ መደበኛ ስብሰባ ተቋርጧል” ያሉት እነዚህ ወገኖች፣ ሰብሰባው ቢቀርም ራሳቸውን አመራር ያደረጉት ቡድኖች ይህን ዕቅድ መያዛቸውን ገልጸዋል። በስም የሚታወቁትና ኦሮሚያ ላይ ግርግር ለመፍጠር ታስቦ የሁለቱ ስም ግንባር ሆነ እነጂ፣ምርጫውን አስመልክቶ ከተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች የሁከት ዜናና ምርጫው እየተጨናገፈ እንደሆነ የሚያውጁ መረጃዎችን ለማሰራጨት ዝግጅት ተደርጓል። በድምጽ እየገቡ ምስክር እንዲሆኑ የተዘጋጁም አሉ። እነዚህ የተዘጋጁት ሰዎች በየጫካው ያሉና ከዚህ ግብረኃይል ጋር አብረው የሚሰሩ እንደሆኑ የሚገለጸባቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጭምር እንደሆነ የመረጃው ባለቤቶች አመልክተዋል።

“ምርጫውን በሁከትና በአመጽ ማስተጓጎል ባለመቻሉ፣ የድህረ ምርጫ አመጽ በሸዋ ኦሮሚያ ላይ ለማስጀመር የኃይማኖት ክንፉን ለመጠቀም አሜሪካ አገር ባለው የኤርትራ ኤምባሲ ከአዲስ አበባ የሄዱ ዕቅድ አቅርበዋል” በማለት አስቀድመው ለአዲስ ሪፖርተር የገለጹትን ያስታወሱት ወገኖች፣ አቶ ነዓምንና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በሻዕቢያ ድግስ ላይ ታዳሚ በመሆናቸው ሳይካሄድ የቀረው ጋዜጣዊ መግለጫ ለረቡዕ መተላለፉን አመልክተዋል። በድግሱ ላይ ሁለቱም ኢትዮጵያን ወራሪ አድርገው ኤርትራን በማወደስ ማብራሪያ መስጠታቸውንም እነዚሁ ወገኖች አመልክተዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኤፍሬም ማዴቦና ነዓምን በሻዕቢያ በዓል ላይ ታዳሚ በመሆናቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ለኢድ ቀን ተላለፈ፤

አዲስ ረፖርተር ዜና - አባላቶቹ በመበተናቸው መደበኛ ስብሰባውንና ሊያካሂዳቸው...

“የፈርዖን ቀንበር ተሸካሚዎችን” ጽምዶን አስመልክቶ ዓለም ዓቀፍ ማህበርሰብ መረጃ ተሰጠ

አዲስ ሪፖርተር ዜና - “አባቱም አያቱም ይታወቃሉ” በማለት የገለጹት...

በሻዕቢያ የሚመራው የእነ ነዓምን ዘለቀ ግብረ ኃይል ተበተነ፤ ስብሰባ፣ ቅስቀሳ፣ ሰላማዊ ስለፍ በይፋ ቆመ፤

አዲስ ሪፖርተር ዜና - በኢትዮጵያ ምርጫ እንዳይካሄድ ለማደናቀፍ ተደራጅቶ...

[ሞዐ ተዋህዶ] አዲስ የድህረ ምርጫ ህዝባዊ አመጽ ዕቅድ በኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ ቀረበ

አዲስ ሪፖርተር ዜና - ምርጫ መካሄድ እንደሌለበት በተቀመጠው አግባብ...