“ኢህአፓ የትግራይ ሕዝብ ከማን ጋር አብሮ እንዲቆም ነው እየጠየቀ ያለው? ይህ አዲስ አበባ ያለው የጽምዶ ክንፍ መግለጫ ነው” የትግራይ ሰላም ኃይሎች

Date:

አዲስ ሪፖርተር –“መግለጫው በውጭ አገር የተመሰረተው ጽምዶ መግለጫ ነው” ሲሉ ኢህአፓ ያወጣውን መግለጫ ይዘትና የመግለጫውን ባለቤት የገለጹ እንዳሉት “የትግራይ ሕዝብ በፊትም ሆነ አሁን አንድ ነው። የሚነቅለውንም ያውቃል” ኢህአፓ መግለጫውን በየትኛው አቋሙና አሰላለፉ መሰረት እንዳወጣ ተጠይቆ ምላሽ ለመስጠት አልፈለገም።

ኢህአፓ አዲስ አበባ ተቀምጦ በይፋ የ“ጽምዶ” አባል መሆኑን ያረጋገጠ ያህል እንደሚሰማቸው ተስፋዬ ንጉስ ራያ የሃራ መሬት አመራር፣ የሕዝብና ሰራዊት ግንኙነት ኃላፊ ናቸው የተናገሩት። የባይቶና ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ በርኸም በተመሳሳይ መግለጫው በውጭ አገር የተፈጠረው ጥምረት እንዳለ አመልክተው መግለጫውን የዚያ ጥምረት ክንፍ አውጥቶታል ብለው እንደሚያምኑ አመልክተዋል።

የኢህአፓ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ወልዳይ “ስለምታወሩት ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም” በማለት መግለጫውን ተከትሎ ስለተነሳባቸው የመርህና የአሰላለፍ ጥያቄ ምላሽ ከምስጠት ተቆጥበዋል። ለፓርቲው ቢሮ ስልክ በመደውል ተመሳሳይ ጥያቄ ቢቀርብም ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም። ሚስጥረ ለሚባሉት የፓርቲው ከፍተኛ አመራር በተደጋጋሚ ቢደወልም ምላሽ አልሰጡም። ፓርቲው በተደጋጋሚ ለሚቀርበለት ጥያቄ ምላሽ አይሰጥም። ሆኖም ግን “አዲስ ሪፖርተርን ገለልተኛ አይደልም” በማለት ይከሳል።

“…. ሕግ ማስከበር እና ተመሳሳይ መፈክሮች ሽፋን በመጠቀም ትግራይን እንደገና ወደ አውዳሚ ጦርነት ለመክተት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ከፍተኛ ስጋት እየተከታተልን ያላነው ጉዳይ ነው” በማለት ኢህአፓ ብልጽግናን ከሶ ላውጣው መግለጫ ሲመልስ፣ “እኔ እስከማውቀው ድረስ ብልጽግና ጦርነት አይፈልግም። ቢፈልግ ኖሮ ጽምዶ እስኪፈጥሩ ድረስ አይታገሳቸውም ነበር”  ብሏል።

“ኢህአፓን ጨምሮ በሩቅና ቅርብ ያሉ ወንጀለኞች ስብስብ የትግራይ ህዝብ እንዴት አንድ መሆን እንዳለበት ሊነግሩት አይችሉም። የትግራይ ህዝብ ድሮም አንድ ነበር። አሁንም አንድ ነው” ያለው ተስፋዬ፣ ይህ ሕዝብ ማንን እንደሚነቅል ጠንቅቆ የሚያውቅ እንደሆነ አመልክቷል። አክሎም የትግራይ ሕዝብ ጦርነትን ፈልጎ እንደማያውቅ አመልክቷል።

“ሕዝቡ ጫካ አድርገው የሚጠቀሙ ሽፍቶች አሉ” በማለት ህገወጡን ትህነግ ለትግራይ ሕዝብ ስቃይና መከራ ተጠያቂ ያደረገው ተስፋዬ፣ ኢህአፓ ይህን ሰላማዊ ሕዝብ አንድ ሆኖ እንዲቆም ጥሪ ሲያቀርብ “ከማን ጋር ቁም እያለ ነው” ሲል ይህን ሊያብራራ እንደሚገባው አመልክቷል።

ኢህአፓ በመግለጫው “የፕሪቶሪያ ስምምነት በተለያዩ አካላት ከሚጠቀሱበት የአካታችነት መሰል ጉድለቶች፣ የውሉ ዋና መንፈስ ጦርነቱን በቋሚነት ማቆም፣ ፖለቲካዊ መፍትሔን ማስቀደምና ተፈናቃዮችን ወደየቦታቸው መመለስ፤ ሰብዓዊ እርዳታ ማሰራጨት እና የተፈረሙትን ግዴታዎች መፈጸም ነበረበት። ዛሬ ግን መንግሥት በራሱ የገባውን ቃል በመጣስ ክልሉን እንደገና ወደ ውጥረት ለመመለስ ተግቶ እየሰራ ነው” በማለት መንግስትን ከሷል።

መከላከያ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም መቀለ ከተማን መቆጣጠሩ በይፋ ሲነገር ኢህአፓ “ጁንታው ተደምስሷል እንኳን ደስ አለን” በማለት መግለጫ አውጥቶ ነበር። የአገራዊ የመከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሉአላዊነትና አንድነት ለማስከበር ያደረገውን ተጋድሎ አድንቆ የነበረ ፓርቲ ዛሬ “የገዢው ፓርቲ ዋና ዓላማ በትግራይ ሕዝብ ላይ እንደገና ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድና ጦርነት መክፈት እንጂ ሰላምን ማስፈን አይደለም። ለዚህም ያለፈውን ጦርነት መመከት እና ከአሁናዊ ሁነቶች ጋር ማዛመድ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያን ህወሓት ማዶ በሚል ሽፋን በትግራይ ሕዝብ ላይ የታወጀው እልቂት ቁስል ሳይደርቅ ዛሬ ደግሞ የትግራይ ሕዝብን ከህወሓት ማዶ የሚለው መፈክር ሌላ ዙር ጦርነት የፖለቲካ ሽፋን እየሆነ ነው” በማለት መግለጫ ማሰራጨቱ በበርካቶች ጥርስ ውስጥ አስገብቶታል።

የህገወጡ ትህነግ ሊቀመንበርና የጊዜያው አስተዳደሩን አፍርሰው መሪ የሆኑት ዶክተር ደብረጽዮን “ከአሁን በኋላ ሰላማዊ ንግግር የለም። በኃይል ነው ሁሉንም የምናደርገው” በማለት አብረዋቸው የሚሰሩ አካላትን በመጠቀስ “ሃሳብ አይገባቹህ እናሸንፋለን” በማለት በገሃድ ተናግረዋል። አክለውም የትግራይ ህዝብ ሰላም የሚረጋገጠው በብልጽግና መቃብር ላይ ነው” በማለት ጦርነቱን ከገጋሮቻቸው ጋር ሆነው ለመክፈት መዘጋጀታቸውን ይፋ አድርገዋል።

“እኛ በተቻለን አቅም ድሮንን በፀረ ድሮን ተዋጊ አውሮፕላኖችን በፀረ አውሮፕላን ለመከላከል እንሞክራለን።ሁሉንም ግን ተከላክለን አንዘልቀውም።ከሰሞኑ እንዳየነው እንኳን እኛ እስራኤልም ብትሆን ሁሉንም የኢራንን ድሮንና አውሮፕላን መከላከል አልቻለችም።በመሆኑም እናንተ የራሳችሁን መከላከል ማድረግ አለባችሁ” በማለት ሞንጆሪኖ ስለጦርነት ዝግጅት ዝርዝር ተናግረዋል።

ይህ ሁሉ በሆነበት አግባብ ብልጽግና የትግራይ ህዝብን ሊያጠፋ መነሳቱን ገልጾ የትግራይ ሕዝብ ከትህነግ ጋር አንድ ሆኖ እንዲቆም ኢህአፓ ጥሪ ማቅረቡን፣ ተስፋዬ “የትግራይ ልጆችን እየነጠቀ ወደማይታወቅ ስፋር የሚልከው፣ ለጦርነት እየተዘጋጀ ያለው ማን እንደሆነ እየታወቀ ኢህአፓ ይህን ማለቱ የሌሎችን አቋም አዲስ አበባ ሆኖ ለማራመድ ተብሎ እንጂ ሌላ ምንም ምክኛት አይቀርብለትም” ሲል ጉዳዩ ሌላ ይዘት እንዳለው አመልክቷል።

“አብረን ከምንሰራቸው ጋር ልዩነቶች አሉን። አሁን የተስማማነው ተባብረን ብልጽግናን በመጣል ልዩነታችንን ከዚያ በኋላ ለመመለከት ነው” በማለት ዶክተር ደብረጽዮን መናገራቸውን ያስታውቀው አቶ ዮሴፍ “እውነታውን በዚህ መልኩ ዶክተር ደብረጽዮን እየነገሩን፣ ኢህአፓ ለትግራይ ህዝብ በውጭ ያሉትን የጥምረቱ ኃይሎች አሳብ እንዲተገብር የትግራይ ህዝብ ጥሪ በማቅረብ አጋርነቱን ወይም የጽምዶው አባል መሆኑን አረጋግጧል” ብለዋል።

“አሁን የተሰባሰቡት ሱዳን፣ ትህነግ፣ ፋኖ፣ ኦላ፣ ወዘተ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ የትግራይ ህዝብ አግዘህ አዲስ አበባ አድርሳቸው” የሚል መግለጫ በኢህአፓ በኩል ውጭ ያለው ኃይል ያሰራጨው መግለጫ የትግራይ ህዝብ ያለውን የሰላም ፍላጎት መዘነጋቱ አስገራሚ ነው” ብሏል።

 “ትምህርት ከድል በኋላ በማለት በአክሳሪ አካሄዱ የሚታወቀው ኢህአፓ፣ከእግዚአብሔር የለም መሰረታዊ ዕምነቱ ተስፈንጥሮ የብሉይ ኪዳን መመህር መሪ አድርጎ ሲሾም ድግሱ ምን እንደሆነ ይታወቃል” በማለት አስተያየት የሚሰጡ “ኢህአፓ ለትግራይ ሕዝብ የጦርነት ትብብር ጥሪ በማቅረብ ከትህነግ ጋር እንዲቆሙ ጥሪ አቀረበ” ሲሉ ጉዳዩን ከመነሻው መመልከት እንደሚበጅ ይገልጻሉ።

በውጭ አገር ያለው የፓርቲው ሽማግሌ አመራሮች “ለምን ወደ ምርጫ ገባቹህ” በሚል አዲስ አበባ ያለውን ክንፍ በወቀስ ተጣልተው እንደነበር የሚናገሩ የፓርቲው የቅርብ ሰዎች፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በተደረገ የዙም ስብሰባ እርቅ ማውረዳቸውን ይናገራሉ።

ዕርቅ መደረጉን ለአዲስ ሪፖርተር የአሜሪካ ተባባሪ የገለጹት ክፍሎች እንዳሉት ከሆነ እነዚሁ አንጋፋ አመራሮች አሁን ላይ ትህነግ ያለበት የተለያዩ ታታቂዎች የመሰረቱትን ጥምረት ስለሚደግፉ አገር ቤት ያለው ክንፍ ይህንኑ በመረዳት ስልታዊ ደጋፍ እንዲሰጥ ወስነው ተስማምተዋል።

የሳት ራት መንገድ መርጦ እናቶችን ጠዋሪና ቀባሪ በማሳጣት የትግል ገድሉን በኪሳራ የደመደመውና የከሰመው ኢህአፓ አሜሪካ ባሉ ያረጁና አስር የማይሞሉ ጡረተኞች መመሪያና መሰረት የወጣው ትህነግን የሚደግፍ መግለጫ ሊጠና እንደሚገባው በርካቶች አሳስበዋል።

በአዲስ አበባ የተለያዩ ተልዕኮ ያላቸው እንዳሉ የገለጸው ተስፋዬ መንግስት በጥንቃቄ ጥናት ሊያካሂድባቸው እንደሚገባ አመልክቷል። አክሎም፣ “የፋኖ፣ የሻዕቢያ፣ የሱዳን፣ የኦነግ ወዘተ ትብብርን እደግፋለሁ ያለው ኢህአፓ፣ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል ብሏል” አቶ ዮሴፍም “ጉዳዩ ኢትዮጵያን የማጥፋት እንደሆነ እየታወቀ ኢህአፓ አዲስ አበባ ሆኖ እንዲህ ዓይነቱን መግለጫ ያወጣበትን ምክኛቱን እንዲያስረዳ ይጠበቃል” ብሏል። ማንም ፓርቲ አቋሙን በግልጽ ማራመድ እንዳለበት አመልክቶ፣ ኢህአፓም አሰላለፉን ግልጽ አድርጎ እንዲያሳውቅ ጠይቋል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related