ኢትዮጵያና አሜሪካ ወዴት? በሻዕቢያ ደጅ ያለው የመጨረሻው የግብጽ ሽምግልና፣ የቀይ ባህር ጉዞና የባብ ኤልመንደብ ስምምነት አዋጆች

Date:

አዲስ ሪፖርተር – “ጉዞ ወደ ባብ ኤልማንደብ” እና “የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መመለስ” የሚሉት ነጥቦች በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ ስትራቴጂካዊ ውይይት፣ እንዲሁም በቅርቡ በዋሽንግተን በተፈረመው ስምምነት ውስጥ ቁልፍ ቦታ የያዙ ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ናቸው። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በተደጋጋሚ የተጎበኙትም በዚሁ ቁልፍ ጉዳይ ትግበራ ላይ ወደው እንዲስማሙ ለማድረግ እንደነበር ዲፕሎማቲክ ምንጮች በተደጋጋሚ የሚያንሱት ጉዳይ ነው።

የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ ለኢትዮጵያ አየር ኃይል እና ለመከላከያ ኃይሉ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱ፣ ኢትዮጵያ በቀጠናው ማለትም በቀይ ባሕር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ አካባቢ ለሚደረጉ የሰላም ማስከበር እና የጸጥታ ጥበቃ ስራዎች ዝግጁ እንድትሆን ያግዛታል። እርምጃው በዲፕሎማሲ ቋንቋ የተጠቀለለ የኢትዮጵያን ወደ ቀይ ባህር የመመልስ ጥያቄ የሚመለስ እንደሆነ የሚገልጹ፣ በባብ ኤልማንደብ አካባቢ ያሉ የደኅንነት ስጋቶችን ለመከላከል ሁለቱ ሀገራት የደኅንነትና የስለላ መረጃዎችን በፍጥነት ለመለዋወጥ ከመስማማታቸው ጋር አንድ ላይ ሲታይ የጉዳዩን አይቀሬነት አመላካች ነው።

በዚሁ ወር ከኤርትራ ባለሥልጣናት ጋር በግብፅ ካይሮ የተወያዩት ከፍተኛው የአሜሪካ መካከለኛው ምሥራቅ እና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ አማካሪ ማሳድ ቦሎውስ። ውይይቱ የተሳካ እንደሆነ ቢገልጹም ኤርትራ ከአሜሪካ የቀረበላትን የመርህና የፖሊሲ ጉዳይ አልተቀበለችም። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንዳሉት ግብጽ ኢሳያስን እንድታግባባ የመጨረሻዋ ሽማግሌ ሆናለች። እንደ መረጃ ምንጮቹ ከሆነ የየመን ሃውቲ ቡድን በሳኡዲ አረቢያ ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ኢትዮጵያን በቀይባህር ላይ መሾመ የሳኡዲም አቋም በመሆኑ የግብጽ የመጨረሻ ሙከራ ካለተሳካ አሜሪካ በግልጽ አቋሟን ታሳውቃልውች።

ከወራት ብፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የተመራው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ ዋሽንግተን ዲሲ በመሄድ “ባለሁለት ወገን የተዋቀረ የስትራቴጂክ ውይይት ማዕቀፍ” ወይም BSD Framework የተፈረመው ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በተደረገው የሁለትዮሽ ምክክር ወቅት ሲሆን ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ መግለጫ አድርጎ ሲያሰራጨው ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። 

ስምምነቱ የተፈረመው እና ይፋ የሆነው ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና ከሌሎች ከፍተኛ የደህንነት ተቋማት መሪዎች ጋር በሽብርተኝነትና ቀጠናዊ ደህንነት ዙሪያ ሰፊ ውይይቶች ከተካሄዱ በኋላ ሲሆን፣ ስምምነቱን ተከትሎ በአሜሪካ የትጥቅ ትግል የሚመሩና ሰላማዊ ትግል በሚል የተሰባሰቡ “ብልጽግናን አላወቅነውም፣ ከማን ጋር እየታገልን እንደሆነ አልተረዳንም” በማለት የስምምነቱ አካሄድ ስጋት የገባቸው ጥያቄ ማንሳታቸውና በልዩነት መለያየታቸው አይዘነጋም። 

የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግሥታት “ባለሁለት ወገን የተዋቀረ የስትራቴጂክ ውይይት ማዕቀፍ” ሁሉን አቀፍ፣ ተቋማዊ እና በእኩልነት አጋርነት ላይ የተመሠረተ ስምምነት ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረና ከሌሎች ጊዜያት ውሎች የተለየ መሆኑ በተለያዩ ወገኖች የተለያዩ ትነተና እየቀረበበት ቆየ። ይህ ማዕቀፍ የመከላከያ፣ የፀረ-ሽብር፣ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ አጋርነትን በማቀናጀት ከጊዜያዊ ስምምነቶች ወጥቶ ዘላቂና ስልታዊ መሠረት ያለው አጋርነት ስለሚፈጥር አሜሪካ ባሉ የትጥቅ ትግል አራማጅ ቡድኖችና አመራሮች ዘንዳ የተፈጠረው ስጋት አየለ። 

ይህ ልዩ ማዕቀፍ ቋሚ የጋራ የሥራ ቡድኖችን (Joint Working Groups) በማቋቋም በየስድስት ወሩ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ግምገማ የሚያደርግ ሲሆን፣ ለሚፈረሙ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ስምምነቶች እንደ መሪ የሕግ ጥላ ሆኖ ያገለግላል። በሁለቱ ሀገራት መካከል የጋራ የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያና ከፍተኛ የፖለቲካ መተማመን ማሳያ የሆነው ይህ ስምምነት፣ ቀጣይ ውይይቱን በአዲስ አበባ ለማካሄድ ቀጠሮ ይዟል። 

በውይይትቱ ወቅት ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ የተነሳው ልዑኩ በነጩ ቤተ መንግሥት ከሚገኙ ከፍተኛ የደህንነት አማካሪዎች ጋር በተለየ ሁኔታ ተገናኝቶ፤ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የጂኦፖለቲካዊ ሽኩቻ ለመቀነስ እና የባብኤልመንደብ ቀይ ባሕር ቀጠና የደህንነት ስጋቶችን በጋራ መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተደረገ ስምምነት ነበር። 

ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻና  የአፍሪኮም ዋና አዛዥ ጀነራል ዳግቪን አንደርሰን ከአየር ኃይል 90ኛ ዓመት በዓል ጎን ለጎን ባደረጉት ስምምነት አሜሪካ ለኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል አሜሪካ ለኢትዮጵያ አየር ኃይል የቴክኒክ፣ የጥገና እና የፓይለቶች ሥልጠና ድጋፍ የምታደርግበትን ዕድል ማመቻቸት። በአፍሪካ ቀንድ እየታዩ ያሉትን አዳዲስ የጸጥታ ስጋቶች ለመከላከል፣ ሁለቱ ሀገራት ወቅታዊ የደህንነት መረጃዎችን በፍጥነት ለመለዋወጥ ከመስማማታቸው ባለፈ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኅብረት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ የምታደርገውን ተሳትፎ አሜሪካ በወታደራዊ ቁሳቁስና በሎጂስቲክስ ለመደገፍ ያላትን ዝግጁነት ማረጋገጧን ይፋ ማደረጓ ይታወሳል። 

ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ በዲፕሎማሲ እና በወታደራዊ ትብብር መስክ ያለው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ወደ ላቀ ስትራቴጂያዊ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን ይበልጥ አጉልቶ የሚያሳየው የአፍሪካ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየም (ALCS26) በአዲስ አበባ መካሄዱ ነው። 

የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ባለው ግንኙነት ላይ ጥገኝነትን በማስቀረት፣ በጋራ መተማመን ላይ የተመሠረተ የእኩልነት አጋርነት Equal Partnership መገንባት እንደሚፈልግ ግልጽ አድርጓል። ይህ የአሜሪካን የቀድሞ አካሄድ የተቀየርበትን አግባብ የሚያመለከተው ንግግር ከ40 በላይ ተሳታፊ አገሮች ለተሳተፉበት ሲምፖዜም ግልጽ መልዕክት ተደርጎ ተወስዷል።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) ጋር በመተባበር ያዘጋጀችውና የከፍተኛ ጦር መኮንኖች ስብስብ የሆነው የአፍሪካ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየም ሲጀመር 

በመድረኩ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን፣ የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናንት ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤልን ጨምሮ በርካታ የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖችና የአፍሪካ ሀገራት የጦር መሪዎች ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የአህጉሪቱን የፀጥታና ደኅንነት ስጋቶች ለመመከት በአፍሪካና በዓለም አቀፍ አጋሮች መካከል ጠንካራ ትብብር መገንባት ወሳኝ ነው። ሲምፖዚየሙም በአሜሪካና በአፍሪካ መካከል ዘላቂ አጋርነትን በመፍጠር ተቋማትን ለማጠናከር፣ ወታደራዊ ትምህርትን ለማስፋፋትና ዘላቂ የመከላከያ ኢኮኖሚን ለማበረታታት ያግዛል ብለዋል።

አምባሳደሩ አክለውም፤ አሜሪካ ለአፍሪካ ሀገራት የምታደርገውን የመከላከያ ድጋፍ በማጠናከር ዘላቂ ወታደራዊ ዝግጁነትን ለማጎልበት ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።የአፍሪካ ወታደራዊ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን መጎልበት የዜጎችን ሁለንተናዊ ደኅንነት ከመጠበቁ ባሻገር አህጉራዊ ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።

በዚህም መሰረት ሽብርተኝነትን፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የሳይበር ጥቃትንና ግጭቶችን በጋራ መመከት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ይህ የሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየም በመንግሥትና ወታደራዊ ተቋማት እንዲሁም በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር እንደሚያጠናክር የገለጹት አምባሳደሩ፤ ተሳታፊዎች ውይይቶችን ወደ ተጨባጭ አቅም የሚያሸጋግሩ ምክክሮችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related