ኢትዮጵያን ሶስት አገር የሚያደርግ አማራጭ በጽምዶ አጀንዳ ውስጥ መካተቱ ይፋ ሆነ፤ “ዩጎዝላቪያን የበተኗት እንደዚህ ነው” አቶ አባይ ግደይ

Date:

“ሻዕቢያን የሚያክል ጠላት ከጀርባችን አስቀምጠን፣ አማራ የሚያክል ህዝብ በጠላትነት ፈርጀን፣ ከኦነግ ጋር ፖለቲካዊ ስምምነት ሳናደርግ ወደ ጦርነት መግባታችን ስህተት ነበር። ሻዕቢያን ወዳጅ፣ ፋኖን የስልጣን ተጋሪ በማድረግ በአዲስ መልኩ መንቀሳቀስ አለብን” በማለት ወደ ኤርትራ ያመራው ህወሃት፣ በሻዕቢያ ሸምጋይነት ከእነ ዘመነ ጋር ስምምነት ፈጥሮ ዛሬ ላይ “ዩጎዝላቪያን ያፈረሷት እንደዚህ ነው” በማለት አደባባይ መግለጫ ለመስጠት ደርሷል።

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — የብልጽግና መንግስት ከወደቀ በኋላ ኢትዮጵያን ሶስት አገር የማድረግ አማራጭ መያዙ ይፋ ሆነ። ቀዳሚው ተግባር ግን የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ማፍረስ እንደሆነ ታውቋል። በውጭ አገር ያሉ የመንግስት ተቃዋሚዎችን ጎራ ከፍሎ እያነታረከ ያለው ቁልፍ ጉዳይም ይህ መሆኑ ታውቋል።

የሻዕቢያና የህወሃት የጋራ ጥምር ግብረኃይል ውስጥ ህወሃትን ወክለው የሚሰበሰቡት አቶ አባይ ግደይ ናቸው ከብልጽግና መውደቅ በኋላ ኢትዮጵያን ሶስት አገር የሚያደርግ ዕቅድ በጽምዶ አደረጃጀት ውስጥ መካተቱን ያመለከቱት። ከቀናት በፊት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አሁን ላይ የተመሠረተው አዲሱ ጥምረት የራሱ መዋቅር፣ አመራር፣ ዕቅድ እና የተፈረመ ስምምነት ያለው ወደ ኋላ የማይመለስ የትብብር ማዕቀፍ እንደሆነ ተናግረዋል።

አቶ አባይ በተፈጠረው “ጽምዶ” በተሰኘው ህብረት ውስጥ ድርጅታቸው ህወሃት፣ እሳቸው በጥቅሉ ፋኖ ያሉት ታጣቂ ኃይል፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ ሌሎች የነጻ አውጪ ታጣቂዎች እንዳሉበት ተናግረዋል። አክለውም የውጭ ኃይሎች እንዳሉበት አመላክተው ስማቸውን ዘርዝረዋል። ኤርትራና ሱዳንን በስም ጠቅሰው ሌሎች አገራት እንዳሉበት አስታውቀዋል። የጥምረቱ መሪም ህወሃት እንደሆነ ይፋ አድርገዋል።

“ኢትዮጵያን አንድ ብሄር ከአሁን በኋላ አያስተዳድራትም” ሲሉ የተደመጡት አቶ አባይ፣ “ስልጣን አንሶኛል፣ ስልጣን እፈልጋለሁ፣ ህገመንግስቱ አልተመቸኝም” ለሚሉ ሁሉ አማራጭ መቀመጡን በለሆሳስ ጠቁመዋል። አክለውም ኢትዮጵያ እንደምትፈርስ “ዩጎዝላቪያን ያፈረሷት እንደዚህ ነው” በማለት ግልጽ መረጃ ሰጥተዋል። አቶ አባይ ድብቁን አጀንዳ ሲያፈርጡ “አሁን ላይ ደግሞ የሀገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ፣ መዋቅርና ውሳኔ በጥምረቱ ሳይሆን በውይይት እና በሕዝብ ተሳትፎ የሚወሰን ይሆናል” በማለት ሊያስተባብሉ ሞክረዋል።

እነ አቶ ልደቱ አያሌው ከህወሃት ጋር ምስጥረው እንዳመከኑት በስፋት መረጃ በወጣበት በምርጫ 97 ወቅት “ድምጼን አላሰርቅም” በማለት ህዝቡ አድማ ሲመታና የውጭ አገራት የህዝብ ድምጽ እንዲከበር ሲጠይቁ አቶ መለስ “እኛ ከለቀቅን ኢትዮጵያ እንደ ሶማሊያ ትበታተናለች” ማለታቸው አይዘነጋም።

“ሻዕቢያ በግብጽ ውክልናና ድጋፍ ይመራዋል” የሚባለው “ጽምዶ” የሚል ህብረት የፈጠሩት ድርጅቶች ወደ ኦፕሬሽን ሲገቡ፣ የሚመራቸው ህወሃት መሆኑን፣ ህወሃት ልምድ ያለውና አሁን የአገር መከላከያ ውስጥ ያሉትን ሁሉ ያሰለጠነና ያበቃ በመሆኑ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ አቶ አባይ አመልክተዋል።

“መንግስትን የገጠመው አሁን ተራ ሽፍታ አይደለም” በማለት የህወሃት የጦር አመራሮች የሚመሩት ጥምረት የኢትዮጵያ መከላከያን እንደሚያፈርስ በተዘዋዋሪ አረጋግጠዋል። “…. ጥምረት የፈጠሩት ተጋግዘው ወደ ኦፕሬሽን ሲገቡ” አሉ አቶ አባይ፣ ልምዱና ብቃቱ ያላቸው የህወሃት አዋጊዎች የሚፈርሰውን መከላከያ እንደሚተኩ ፍንጭ ሰጥተዋል።

የአንድ ዘር ወይም ዲክታተሮች ኢትዮጵያን የሚመሩበት ዘመን እንደሚያከትም ያመለከቱት አቶ አባይ፣ የመንግስት ለውጥ ሲደረግ የተለያዩ መዋቅሮች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። ክልሎች ባሉበት ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ጠቆም አድርገው፣ ይህ ካልሆነ የተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች እንደሚቋቋሙ ተናግረዋል። አክለውም ይህ አካሄድ ሶስት አገራት እንዲፈጠሩ ሊያደርግ እንደሚችል ይፋ አድርገዋል። ኢትዮጵያ ተቆራርጣ የሚፈጠሩት ሶስቱ አገራት እነማን እንደሆኑ አላስታወቁም። ጠያቂዋም አላነሳችም።

“ስልጣን አንሶናል፣ አገር መሆን እፈልጋለሁ፣ ህገመንግስቱ አይመቸኝም የሚሉ ስላሉ” በማለት ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ ሶስት አገራት ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ካስታወቁ በኋላ፣ “ዩጎዝላቪያን እንደዚህ አድርገው ነው ያፈረሷት” በማለት የዕቅዱን የመጨረሻ ግብ በይፋ ተናግረዋል።

አቶ አባይ በጋራ ጥምረቱ ላይ ሱዳን እንደሚመላለሱ፣ በሱዳን እና በሸረሪና ያለውን ኃይል ዝግጅት፣ እንዲሁም በቅርቡ ህወሃት የድሮን ጥቃት በመስጋት መሳሪያዎችና ሎጂስቲክ በጋማ ከብቶች ወደ ተመረጡ አካባቢዎች በማመላለስ ላይ እንዳለና በቅርቡ ጦርነት እንደሚጀመር ይፋ ያደረጉ የህወሃት ቁልፍ አመራር ናቸው።

ይህ እሳቸው ይፋ ያደረጉት ዕቅድ ሻዕቢያ በሚመራው ጥምረት ከወር በፊት በአስመራ የፋኖ መሪ ዘመነ ካሴና ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባሉበት የጸደቀ መሆኑን መዘገባችን አይዘነጋም። ይህንኑ ዕቅድ የሚያውቁ አደባባይ በመውጣት “መንግስትን መቃወምና አገር ስትፈርስ መስማማት የተለያዩ ናቸው” በማለት ሻዕቢያ በሚመራቸው ሚዲያዎች ሳይቀር መቃወማቸው አይዘነጋም።

የፕሬዚዳንት ኢሳይያስ “አፍ” የሚባሉት ፕሮፌሰር መሀመድ “ፋኖን ያደራጀው፣ ያስታጠቀውና ያሰለጠነው የኤርትራ መንግስት ነው” በማለት አውቀውም ይሁን አምልጧቸው መናገራቸውን ተከትሎ እንደ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ዶክተር ዮናስ የመሳሰሉ የመንግስት ተቃዋሚዎች “ይህ አገር አፍራሽ ስብስብ ነው” በማለት ህዝብ በንቃት እንዲከታተል በይፋ ጥሪ ማቅረባቸው አይዘነጋም።

ጃዋር መሐመድም እስከ ጽምዶ ምስረታ አብሮ ከሄደ በኋላ በግልጽ ጽምዶን ተቃውሞ በተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቱ አንድ ላይ ተዳምሮ የፈጠረው የመፈረካከስ ስሜት በገነነበት ሰዓት፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አሁን ላይ የተመሠረተው አዲሱ ጥምረት የራሱ መዋቅር፣ አመራር፣ ዕቅድ እና የተፈረመ ስምምነት ያለው ወደ ኋላ የማይመለስ የትብብር ማዕቀፍ እንደሆነ አመልክተዋል።

ሻዕቢያ የቀድሞ ተቃዋሚ የነበረውን የሚዲያ ሰው በአስተባባሪነት በመምራት ለጽምዶ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በስፋት በጀት መድቦ እየሰራ “ብልጽግና ስሜን እያጠፋ ነው” በማለት በተደጋጋሚ መግለጫ በሚያወጣበት በዚህ ወቅት፣ ይፋ የሆነው ኢትዮጵያን ሶስት ቦታ የመቆራረጥ ዕቅድ ከየአቅጣጫው ቁጣ እየፈጠረ ነው።

“ዶ/ር ደብረጽዮንና ድርጅታቸው ለበርካታ ዓመታት የአማራ ፖለቲከኞችንና ምሁራንን የፌዴራል ሥርዓቱን ለማፍረስና የድሮውን ሥርዓት ለመመለስ የሚሠሩ የትምክህት ኃይሎች እና የድሮ ሥርዓት ናፋቂዎች” በማለት ሲፈርጁ እንደቆዩ ይታወቃል።

ይህን ሲሉ የኖሩት የህወሃት መሪ በአዲሱ ጥምረት ዙሪያ ሲናገሩ “ፍላጎታችን አንድ ዓይነት አይደለም፤ የየራሳችን ፍላጎት አለን፤ ነገር ግን ቢያንስ የሚያገናኘን አንድ ማዕከላዊ ነገር አለን” በማለት ቀደም ሲል የማይታገሱትን የፖለቲካ ልዩነት አሁን ላይ አቀራራቢና አብሮ የሚያሠራ አድርገው አቅርበዋል።

በጦርነቱ ወቅት የአማራ ክልል የጸጥታ መዋቅርንና ፖለቲከኞችን ወራሪ ኃይሎች በማለት ይፈርጁ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን በአማራ ምሁራንና ፖለቲከኞች ለምሳሌ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች መካከል ጽምዶ በሚል መሪ ቃል የተጀመረውንና በጋራ ሰላማዊ አብሮ መኖርን ለመፍጠር የሚደረገውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ጥረት አዲሱ ጥምረት እንደሚቀበለውና ይልቁንም ተጨማሪ ኃይሎች ሊቀላቀሉት እንደሚችሉ ገልጸዋል። የዶክተር ደብረጽዮን መግለጫ ከላይ አቶ አባይ ኢትዮጵያ ሶስት ቦታ እንደምትቆራረጥ በገሃድ በአንደበታቸው ካስታወቁት እውነት የሚጋጭ እንደሆነ ተመልክቷል።

አቶ ልደቱ “ለኢትዮጵያ ትንሳዔ” ያሉትን ህብረት ለማሞካሸት እንዲያመቻቸው “በሕዝብ ደረጃ የአማራ ሕዝብ ጠላታችን አይደለም” በማለት የተናገሩት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ ህወሃት አማራ ክልልን ወሮ ለምን እንደዘረፈ፣ በጅምላ እንደጨፈጨፈ፣ መሰረተ ልማት እንዳወደመ፣ ባልደረባቸው ሞንጆሪኖ “ብልጽግናን ካስወገድን በኋላ ከአማራው ጋር የምናወራርደው ሂሳብ አለን” ያሉበትን ምክንያት አላስረዱም። ስለ ወልቃይትና ራያ ህዝብ ግልጽ ፍላጎትና ጥያቄም ያነሱት ነገር የለም።

“አሁን ላይ ደግሞ የሀገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ፣ መዋቅርና ውሳኔ በጥምረቱ ሳይሆን በውይይት እና በሕዝብ ተሳትፎ የሚወሰን ይሆናል” ያሉት የህወሃት ሊቀመንበር፣ ባልደረባቸው ኢትዮጵያ ሶስት ቦታ እንደምትቆራረጥ ይፋ ማድረጋቸውን በዚህ መልኩ አስተባብለዋል።

ጥምረቱ አደባባይ በመውጣት ዕቅዱን መናገር እንዳለበት በሚወተወትበት በዚህ ወቅት መግለጫ የሰጡት ደብረጽዮን፣ የጽምዶ የተጻፈ ደንብና የተፈረመ ስምምነት አለ ቢሉም ይህ እስከተጻፈ ድረስ ይፋ አልሆነም። ይሁን እንጂ አባሎቻቸውና የውጭ አገር ክንፎቻቸው በፊናቸው በሚያደርጉት ስብሰባ፣ እንዲሁም ለማስተባበያ በሚል በሚሰሩት ፕሮፓጋንዳ ይፋ እያደረጉት ይገኛሉ።

“ሻዕቢያን የሚያክል ጠላት ከጀርባችን አስቀምጠን፣ አማራ የሚያክል ህዝብ በጠላትነት ፈርጀን፣ ከኦነግ ጋር ፖለቲካዊ ስምምነት ሳናደርግ ወደ ጦርነት መግባታችን ስህተት ነበር። ሻዕቢያን ወዳጅ፣ ፋኖን የስልጣን ተጋሪ በማድረግ በአዲስ መልኩ መንቀሳቀስ አለብን” በማለት ወደ ኤርትራ ያመራው ህወሃት፣ በሻዕቢያ ሸምጋይነት ከእነ ዘመነ ጋር ስምምነት ፈጥሮ ዛሬ ላይ “ዩጎዝላቪያን ያፈረሷት እንደዚህ ነው” በማለት አደባባይ መግለጫ ለመስጠት ደርሷል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ፋኖን ፍርሃቻ የአማራ እናቶች እንጀራ በሌሊት ይጋግራሉ” ፋኖ ሻዕቢያ በላካችው አስራ አንድ አመራሮችን ይመራል

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ — አማራ ክልል የትጥቅ እንቅስቃሴ...

“የኦባሳንጆ የትግራይ ምልልስ በጽምዶ ውስጥ ያሉትን ቡድኖች ጥርጥር ውስጥ ከቷል”

ህወሃት አሁን ላይ በራሱ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም። በቅርቡ...

የቻይናና ግብፅ ባለ21 ነጥብ ስምምነት…የናይል ውኃና የቀይ ባሕር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ምን መልዕክት አለው?

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ —  የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ...