አዲስ ሪፖርተር – ፋኖ ወደ አንድ አመራር በመጣት ራሱን አጥርቶ በሳምንታት ውስጥ እጅ በአፍ የሚያስጭን ድል እንደሚያስመዘገብ እያስታወቀ ባለበት በአሁኑ ሰዐት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፋኖ ታጣቂዎችና ከፍተኛ አመራሮች የሰላም ጥሪ እየይተቀበሉ በመግባት ላይ ናቸው።
ዛሬ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር በይፋዊ የማህበራዊ ገጹ እንዳመለከተው ሰፊ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው መግባታቸውን አመልክቷል።
እንደ ዜናው በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቡድን አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ሲገቡ፣ የ10ኛ ዕዝ ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አሰጋ አከለና የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ቢሮ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መንበረ ክፈተው የሀይማኖት አባቶችና የወረዳው አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ይህ በደቡብ ጎንደር ዞን ሲንቀሳቀስ የቆየውና ራሱን “የገብርየ ክፍለ ጦር” ብሎ የሚጠራው የታጠቀ ቡድን፣ የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል በሰላማዊ መንገድ እጁን መስጠቱን ተከትሎ በውጭ የሚኖሩ የፋኖ ደጋፊዎች፣ የትህነግና የሻዕቢያ ወኪሎች ትችት ሰንዝረዋል።
የክፍለ ጦሩ መሪ አዲሱ ደባልቄ እና ታጣቂዎቻቸውን አስከትለው ሲገቡ፣ ቡድኑ ይህንን ውሳኔ ሊያስተላልፍ የቻሉት፣ በቅርቡ ተመሰረተ የተባለው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ዓላማና አካሄድ የአማራን ህዝብ ጥቅም የማይወክል ሆኖ በማግኘቱ እንደሆነ ገልጿል።
በቅርቡ ፋኖ አንድ አመራር ሰየመ በማለት የተቋቋመው የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ከሻዕቢያና ትህነግ ጋር ኝባር መፍጠሩና ወልቃይትን ለትህነግ ለመስጠት ስምምነት ማድረጉ ከሌሎች ጋር ለተፈጠረው ልዩነት ዋና ምክኛት መሆኑ ሲገለጽ እንደነበር ይታወቃል። አፋብን በድርጅትም ሆነ በአመራሮቹ በይፋ ወልቃይትን አስመልክቶ የአማራ ክልል አካል መሆኑን ወይም ለትህነግ እንዲሰጥ ፋላጎት እንደሌላቸው በግልጽ ለሕዝብ ይህ እስከተጻፈ ድረስ አስታውቀው አያውቁም።
የክፍለ ጦሩ መሪ አዲሱ ደባልቄ “አፋብን የተባለው ስብስብ ከውጭ ኃይሎችና ከጥፋት ቡድኖች ጋር በማበር የሚሰራ መሆኑን ደርሰንበታል” ብለዋል። አክለውም ዝርዝር አሳቦችን አክለዋል።
ቡድኑ በቀጥታ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ እና ከህወሓት ትዕዛዝ በመቀበል እንደሚንቀሳቀስ ያመለከቱት መሪው፣ “የአማራን ክልል የትርምስ ማዕከል በማድረግ የቆየ የፖለቲካ ሒሳብ ለማወራረድ እቅድ ተይዟል” በማለት በዚህ መሰሉ የክህደት ተግባር መሳተፍ ፍጽሞውንም አግባብ ባለምሆኑና የታሪክ ተጠያቂ ስለሚያደርግ የሰላም ጥሪውን መቀበላቸውን አስታውቀዋል።
“ከዚህ የጥፋት መንገድ በመውጣት ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለማስቀጠል የመንግስትን ጥሪ መቀበል የተሻለ አማራጭ ሆኖ መገኘቱ በስለማ ግብተናል” በማለት የክፍለ ጦሩ አባላት ትናንት በይፋ እጃቸውን እንደሰጡ አመልክተዋል። አሁን ላይ ከመንግስት የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ወደ ተረጋጋ የሰላም መንገድ መግባታቸው አውስተዋል።

እርምጃ ቀደም ሲል በሰላም ከገቡት ጋር ተዳምሮ በዞኑ ለሚታየው አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረው ተመልክቷል። በይፋ አይገለጽ እንጂ በተመሳሳይ ሌሎች የሚገቡ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
በስፋት ወደ ሰላማዊ መንገድ እየፈለሰ ያለው የፋኖ አደረጃጀት ሻዕቢያና ትህነግ ለመሰረቱት ጥምረት እንቅፋት በመሆኑ አቶ ነዓምን ዘለቀ የሚባሉት የኤርትራ መልዕክተኛ ከአስመራ በZangi የተላከ መሆኑን ገልጸው መንግስት ወልቃይትን ለትህነግ ለመስጠት መስማማቱን እንደታወቀና ባስቸኳይ ሼር እንዲደረግ ጠይቀዋል።
በግል የኤክስ ገጻቸው አቶ ነዓምን እንዳሉት መንግስት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የፋኖ አንድ መሆን ስላሳሰበው እንደሆነ አስታውቀዋል።እሳቸው ይህን ባሉ በሰዓታት ወስጥ ከደቡብ ጎንደር በዚህ ደረጃ የፋኖ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መግባታቸውና ሌሎችም እንደሚገቡ የሚጠበቅ መሆኑ፣ ከወልቃይትም ለአቶ ነዓምን “ይህንን መረጃ አጋሩልኝ” ጥያቄ “እኛም አውቀናል” ዓይነት ምላሽ መስጠቱ በሻዕቢያ በኩል የታሰበው ዘመቻ መክሸፉን አመልካች እንደሆነ ተወስዷል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የ2018 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን በገመገመበት መድረክ፤ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚንቀሳቀሱ የስጋት ኃይሎችን እንቅስቃሴ የሚቀለብሱ ስምሪቶች በስኬት መከናወናወናቸውን ትናት ማስታወቁ፣ ከብሄራዊ መረጃና ደኅንነት እንደተገኘ ተጠቅሶ በሆርን ሪቪው በኩል ይፋ የሆነ ዜና እንዳመለከተው የኤርትራው የስለላ መዋቅር እየፈረሰ መሆኑ ቀጣዩን የኤርትራ መሪ መጻኢ እድል ከወዲሁ አጓጊ አድርጎታል። የአሜሪካ ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢሳያስን እንዲነቀሉ ወይም አገር ጥለው እንዲወጡ እንዲያደርጉ መጠየቁን ከዚሁ ጋር ያያዙም አሉ።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393






