የአርሚ 11 አዛዥ ሌ/ጄኔራል ፍስሃ በየነ እጅ ለመስጠት ከመከላከያ ጋር ንግግር መጀመራቸው ተሰማ፤ ሕዝብ ውጊያ እየተቃወመ ነው

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በጠለምት ግንባር የአርሚ አስራ አንድ አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄኔራል ፍስሃ በየነ በሰላም እጅ ለመስጠት ከአገር መከላከያ ጋር እየተነጋገሩ መሆኑ ተሰማ። ከተለያዩ አርሚዎች የሚከዱ ታጣቂዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተጠቅሶ ያለማቋረጥ ሪፖርት እየቀረበ መሆኑ ታውቋል።

በቀደመው አደረጃጀት እስከ አርባ ሺህ፣ በአሁኑ ደግሞ እስከ አስራ አምስት ሺህ ኃይል የሚያካትተውን አርሚ የሚመሩት ሌ/ጄኔራል ፍስሃ በየነ እጅ ለመስጠት ንግግር መጀመራቸውን ያስታወቁት ለመኮንኑ ቅርብ የሆኑ አብረዋቸው ያሉ የመካከለኛ አመራሮች ናቸው።

በምዕራብ ጠለምት ግንባር ጥቃት ከሰነዘሩት የአርሚ አስራ አንድ ኮሮች መካከል ሁለቱ ኮሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመበተናቸው ሌ/ጄኔራል ፍስሃ በየነ ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ምክንያት እንደሆናቸው መረጃውን ካካፈሉን ወገኖች ለመረዳት ተችሏል። መኮንኑ ወደ ሰላማዊ መንገድ ሲመጡ ከትግራይ ሰላም ኃይሎች ጋር ስለመቀላቀላቸው ለጊዜው የተባለ ነገር የለም። የአገር መከላከያም በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ለማኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። መከላከያ በተደጋጋሚ የሰላም መንገድ ለሚመርጡ አቀባበል እንደሚያደርግ ኃላፊዎቹ በተደጋጋሚ ሲናገሩ መስማት  የተለመደ ነው።

በሌላ ዜና ከአርሚ 35 እየከዱ ያሉ ታጣቂዎች ቁጠራቸው መጨመሩ ተሰምቷል። የሚከዱት ታጣቂዎች መበራከት ያሳሰባቸው የአርሚው አመራሮች የታጣቂዎቹን የመኖሪያ መታወቃያ ካርድ በመንጠቅ እንቅስቃሴያቸውን  ማገድ ጀምረዋል። መታወቂያ የተነጠቁት በግዳጅ ካምፕ እንዲቀመጡ በማድረግ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።

ጸለምት ወረዳ ከሚንቀሳቀሱት የትህነግ ታጣቂ ኃይሎች መካከል አርሚ 11 እና 13 እየፈረሰ መሆኑን በስፍራው የሚገኙ የሰላም ኃይሎች በትናንትናው ዕለት መናገራቸው አይዘነጋም።

የትግራይ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ህዝብ፣ በተለይም ወጣቶች ጦርነት በትግራይ ምድር እንዳይደገም በከፍተኛ ሁኔታ ጥሪ ሲያስተላልፉ በመቆየታቸው፣ ያለፍርው ጦርነት ጠባሳ የከፋ መሆኑና በቀላሉ ሊረሳ ስለማይችል፣ በተለይም የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት ባለ በሌለ ኃይሉ ሲንቀሳቀስ ከነበረው የሻዕቢያ ኃይል ጋር በመሆን ትግራይን የጦርነት አውድማ ለማድረግ የተያዘው ዕቅድ በትግራይ ባስነሳው ተቃውሞ ሳቢያ ትህነግ ድጋፍ እንዳጣ እየተገለጸ ነው። ይህንኑ ተከትሎ ከፋኖ፣ ሻዕቢያና ግብጽ ጋር የገጠመው ትህነግ ባደራጀው ሰራዊት ዘንዳ ዕምነት በማጣቱ ሳቢያ የገነባው ተዋጊ እየከዳው እንደሆነ ተከታታይ መረጃዎች እየወጡ ነው።

ከበአዲግራት የተሰማውም ዜና በተመሳሳይ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሆኗል። የአርሚ 15 አራት የሻለቃ አመራሮችን ጨምሮ ከ200 በላይ ታጣቂዎች ጥቃት እንዳይደርስባቸው ራሳቸውን በአነስተኛ አሃድ ከፋፍለው  መጥፋታቸው ተገልጿል። ይህ እስከታተመ ድረስ መጥፋታቸው እንጂ የት እንደደረሱ ይፋ አልሆነም። መጥፋታቸው ከተገለጸ በሁዋላ ፍለጋ እየተደረገና የአሰሳ ፍትሻ እንደተጀመረ ዜናውን ያካፈሉን ተናግረዋል።

በሚከዱት የሰራዊቱ አባላት ብዛት የተነሳ መሳሪያ እስከመጠቀም የደረሰ አስገዳጅ እርምጃ እየወሰደ ያለው ትህነግ፣ በአፈሳ መልክ አንዋጋም ያሉትን አስገድዶ ወደ ግጭት ቀጠና ለማስጋበት ጥረት እያደረገ መሁኑን የመቀለ ነዋሪዎች አመልክተዋል።

“በስጋት ላይ ነን” በማለት የተናገሩት የመቀለ ወጣቶች አሁን ላይ ከትግራይ መውጣት አስቸጋሪ እንደሆነ፣ ነገሩ ሁሉ ኤርትራን ወደመምሰል መቃረቡን አመልክተዋል።

በተመሳሳይ ዜና በትግራይ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ መጀመሩ ተሰምቷል። የህወሓት ታጣቂ ቡድን በትግራይ የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን በሃይል እያፈሰ ወደ ግንባር እየወሰደ እንደሚገኝ የዘገበው መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 ነው።

በአዲግራት፣ በአድዋ እና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች የተጀመረው ይህ የወጣቶች አፈሳ፤ በዋናነት በትጥቅ ትግል ስም ወጣቱን ወደ ወልቃይት አቅጣጫ ለመውሰድ የታለመ መሆኑ በዘገባው ተመልክቷል።

ቡድኑ በጠለምት በኩል በከፈተው ጦርነት ከፍተኛ የሰው ሃይል እና የቁሳቁስ ኪሳራ እንደደረሰበት መረጃዎች ይጠቁማሉ። በአካባቢው ከሚገኙ የሚሊሻ ሃይሎች ጋር በነበረው ፍልሚያ በርካታ ታጣቂዎቹ ሙት እና ቁስለኛ ከመሆናቸውም በላይ፣ ወሳኝ የተባሉ የጦር መሳሪያዎቹ መማረካቸው ተነግሯል።  ይህንን የተመናመነ የሰው ሃይል ለማካካስም ነው በአሁኑ ሰዓት በከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን የማፈስ ስራ ላይ የተሰማራው ተብሏል። መረጃዎች እንዳመለክቱት፣ የታፈሱ ወጣቶች በመኪና ተጭነው ወደ ወልቃይት አቅጣጫ እየተወሰዱ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የትግራይ ወጣት ዳግም ለማያባራ ጦርነት እና ለቡድኑ ፍላጎት ሲል ህይወቱን አሳልፎ መስጠት የለበትም የሚሉ ድምፆች እየተሰሙ ነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ባርነትና ባንድነት” ዕርቃናቸው ታዩ፤ የሻዕቢያ መሪዎችና መንጋችው ለምን ተነኩ ጩኸትና “ተኮፊልና” ላሉት ኢሳያስ ጥብቅና መቆም!

“ጄኖሳይድ የምትሉትን ክስ አቁሙ፣ ሴቶች ተደፈሩ የሚባል ነገር እንዳታነሱ”...

ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዴት ተቋረጡ? እንዴትስ እንዲጀምሩ ተወሰነ?

አዲስ ሪፖርተር - ላለፉት አምስት ቀናት የተቋረጠው የአየር ትራንስፖርት...