በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ግድያና ፍንዳታ ሊፈጽሙ የነበሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ፤ “የተመሳሰሉ የትህነግና ሻዕቢያ ሴሎች ላይ ቁጥጥሩ ይጥበቅ”

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና – ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለውን “የወጣቶች አፈሳ” የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ሊካሄድ በተሰላፊዎችና ስለፉን ባስተባበሩ ቁልፍ አመራሮች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት አድርገው የነበሩ ከነመሳሪያቸው መያዛቸው ተሰማ።

“አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ ቃል ለፌዴራል መንግሥትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪ ለማቅረብ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ተስታፊዎች እና አስተባባሪዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ የተላኩት በሻዕቢያና በትህነግ እንደሆነ በተለይ መረጃውን ለአዲስ ሪፖርተር ያስታወቁ አመልክተዋል። የተለያዩ ፈንጅዎች እና የነብስ ወከፍ መሳሪያዎች፣ እንዲሁም ግንኙነት ያደረጉበት መረጃ ተይዞባቸዋል።

አዲስ አበባ ሰላማዊ መስለው የሚንቀሳቀሱ የሻዕቢያና የትህነግ ሴሎች ሊፈጽሙት የነበረውን አደጋ ቀድሞ ያከሸፉት የወታደራዊ፣ የመንግስት የሲቪል የስለላ አካላት በቅንጅ ናቸው። መረጃውን ያስታወቁት አካላት እንዳሉት፣ ዜናው ይፋ ያልሆነው ዕቅዱ በቁጥጥር ስር በመዋሉ ስጋት ባለመኖሩና ድንጋጤን ለማስወገድ እንደሆነ አመልክተዋል። የተያዙትም በሽብር ክስ እንደሚከሰሱ ጠቁመዋል። መረጃ ለማጠናቀርና መረባቸውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ሲባል ዜናው ይፋ እንዳልሆነ አመልክተዋል። የተያዙትን ተጠርጣሪዎች ስምና ብዛት እንዲሁም ልዩ መለያ ለመግለጽ አሁንም ጊዜው ገና እንደሆነ አመልክተዋል።

በዋናነት በፕሪቶሪያው ስምምነት አፈፃፀም መዘገየት ላይ ትኩረት በማድረግ የመንግስትን እና የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ተመሳሳይ ሰልፍ መደረጉ አይዘነጋም።

ሰላማዊ ሰልፉ የተጠራው በትግራይ ለውጥ መምጣት አለበት የሚል የጋራ አላማን ባነገቡ መሰረታቸውን ትግራይ ክልል ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪል ተቋማት እና ስለትግራይ ጉዳይ ይመለከተናል ባሉ ሰዎች በተዋቀረው የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት ነው። የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሓለፎም ምርኤይ የዚህ ምክር ቤት አላማ በክልሉ ጊዜያዊ መንግስት እንዲመሰረት ማገዝም እንደሆነ ገልጸው ነበር። “በትግራይ ያለው ሁኔታ የየራሳችን ፖለቲካ ይዘን የየራሳችን የፖለቲካ ድርጅቶች ከምናራምደው ሰብሰብ ብሎ የፖለቲካ አጀንዳን ለጊዜው አቆይቶ የህልውና ጉዳይ የገጠማትን ትግራይ ወደ ሌላ ጦርነት ሊያስገባት የፈለገ ኃይል ስላለ አገር ውስጥና ውጪም ያሉ የትግራይ ተወላጆች ይሄን አጀንዳ አድርገው በትግራይ ለውጥ የሚመጣበትና አቃፊ የሆነ ጊዜያዊ መንግስት ተመስርቶ የሰላምና መረጋጋት መስራት፤ ከዚያም ፖለቲካ ድርጅቶች እራሳቸውን ለህብረተሰቡ በማሳወቅ ቋሚ መንግስት እስኪመሰረት ምክር ቤቱ እንዲመራው ነው” ሲሉም ምክር ቤቱን ረጅም ውጥን ለተለያዩ ሚዲያዎች ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት እና በትግራይ ውስጥ ያለውን የትህነግ ሽራፊ አካላ በማጋለጥ ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ እንዲነሳ ለፌደራልና ለዓለም ዓቀፉ ማህበርሰብ ድጋፍ የጠየቁት ሰልፈኞች ከምን በላይ ጦርነትን ማውቀዛቸው ይታወሳል። ይህንኑ ሰልፍ መክሸፉን፣ ሰዎች ሲሰባሰቡ ደግሞ የትግራይ ተወላጆች ሳይሆኑ ሌሎች ናቸው፣ ቆይቶም የተከፈላቸውና በኃይል እንዲሰለፉ የተደረጉ ናቸው በማለት ትህነግ ከመቀለ መረጃ ሲያሰራጭ ነበር። ቆይቶም ሰላማዊ ስለፉ ላይ የሚሳተፉ “ከሃጂዎች ናቸው” በማለት ፈርጇቸው ነበውር።

ሰላማዊ ሰልፈኞችና ቁልፍ አመራሮች ላይ ጥቃት ለመሰነዘር ተዘጋጅተው ሳለ አስቀድሞ በቁጥጥር ስር የዋሉት የሻዕቢያና የትህነግ ሴል አባላት በቁጥጥር መዋላቸውን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው እንዳሉት “አዲስ አበባ ጥንቃቄና ልዩ ክትትል የሚያሻቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ” ብለዋል።

ከአብዛኛ የተገፉና ግፍ ሸሽተው ወደ ወገኖቻቸው የመጡ እህትና ወንድሞቻችን መካከል ጥቂት ስውር ዓላማ ያላቸው በመኖራቸው መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ እንደሚገባ የጠቆሙ፣ በአዲስ አበባ በተለይም ኤርትራዊያን ከዜጎች በላይ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ተሰግስገው እየፈጸሙ ያሉት ዘረፋና ህገወጥ ድርጊት መላ ሊባል እንደሚገባ አመልክተዋል።

የበታች አስተዳደር መዋቅር በተራ ሳንቲም በየመንደሩ የተሰገስጉትን እያወቃቸው በዝምታ እንደሚያልፍ የሚጠቁሙ፣ “በሌብነትና በተራ መልከስከስ አገርን ዋጋ ሊያስከፍሉ የሚችሉ የበታች አመራሮች ላይ መንግስት ጠብቅ ያለ እርምጃና ክትትል እንዲያደርግ፣ ከምንም በላይ አከራዮች ለተራ ሳንቲም ሲሉ በህገወጥ የሚፈጽሙት ስምምነት ላይ ጥብቅ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል። ዋናውና ትልቁ ጉዳይ ግን የበታች መዋቅሩ በየመንደሩ እየተርመጠመጠ ለወንጀለኞች የሚፈጥረው ምቹ ሁኔታ ለነገ የሚባል አይደልም” ብለዋል። ሕዝቡም አካባቢውን በመጠብቅ፣ በመከታተልና የሚመለከተውን አዲስ ጉዳይ ለሚመለከተው አካል የሚያደርገውን ጥቆማ አጠናክሮ ሊሰራበት እንደሚገባ አመልክተዋል።

በተካሄደው ሰልፍ ላይ የትግራይ ተወላጆች በመሪዎቻቸው አማካይነት

ለፌዴራል መንግስት እና ዓለማቀፉ ማህበረሰብ የቀረበ ጥሪ

የስምረት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሩ አቶ ሓለፎም፤ በትግራይ የሰላምና ለውጥ ምክር ቤት የተጠራው ሰላማዊ ሰልፉ በትግራይ ክልል እየታየ ነው ያሉትን ቀውስ ለማስቆም የፌዴራል መንገስት እና ዓለማቀፉ ማህበረሰብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማሳሰብም ነው ብለዋል። “አሁን የፌዴራል መንግስት ተፈናቃዮች ወደ ቀዬያቸው እንዳይመለሱ እንቅፋት የሆነብኝ ኃይል አለ ብልም ይሄ ኃይል ከህዝቡ ስለማበልት መፍትሄ እንዲሰጥ የሚለው አንዱ ጥያቄያችን ነው” በማለት፤ ሌላው ጥያቄችን ጦርነትን በመሸሽ ከትግራይ ሚወጣውን ወጣት አጠቃላይ ኢትዮጵያ ህዝብ እና ፌዴራል መንግስት ድጋፍ ከላላ እንዲሆኑላቸው ማሳሰብ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ “ድንበር ተሻጋሪ” ያሏቸው “ጽምዶ” የተባለውን የውጊያ ጥምረት በኢ-ህገመንግስታዊነት ፈርጀውም፤ ለምስራቅ አፍሪካን ቀውስ ሊተርፍ የሚችል በመሆኑ እንዲገታ ተቃውሞ ማሰማትም ሌላው የእንቅስቃሴው አላማ ነው ተብሏል፡፡

ህገመንግስታዊ መፍትሄ የሚሻው’ “የምዕራብ ጉዳይ..”

በአዲስ አበባ ቅዳሜ ይካሄዳል የተባለዉን ሰላማዊ ሰልፍ ህወሓት “የብልፅግና መንግሥት ያቀደዉ ጥቃት ነዉ” ሲል ተቃውሞታል። በቅርቡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ሚካኤል አስገዶም፤ “የህልውናችንን አደጋ ለመከላከል እየተዘጋጀን መሆኑን እየገለጽን ነው” ብለዋል፡፡ በትግራይ ጦርነት ወቅት የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ተፈናቃዮች ወደ ቀዬያቸው አለመመለሳቸውን ህወሓት የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በፌዴራል መንግስት ሳይተገበር የቀረ ትልቁ ሽንቁር አድርጎም በተደጋጋሚ ያነሳል፡፡

ፎቶ በኤአይ የተሰራ

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related