በህወሓት የፖለቲካዊ ጉዳዮች ማዕከል ተዘጋጅቶ ለውይይት የቀረበው “ጽምዶ/ጥምረት” የተሰኘ የትግርኛ ሰነድ፣ የጋራ ትግል ለማድረግ በትግራይ ሠራዊት ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችንና ተቃውሞዎችን ለመመለስ የቀረበ የማሳመኛ ሰነድ መሆኑን የይዘቱ መግቢያ ያሳያል።
ሰነዱ የሚያስተላልፈው ዋና መልዕክት በጽምዶ መስራት የትግራይን ህልውናና ጥቅም ለማስጠበቅ የሚረዳ ተጨማሪ አቅም ነው። የጽምዶ ሰነዱ በተለይ በሠራዊቱ ውስጥ የሚነሱትን ጥያቄዎች በመመለስ የጋራ ትብብርን ለማሳመን የተዘጋጀ መሆኑ በሰነዱ ተደጋግሞ ተመልክቷል።
ቀደም ሲል በነበረው ውጊያ የትግራይ ሕዝብ ላይ ጉዳት አድረሰዋል የሚላቸውን ወገኖች “ከድል በኋላ” ለፍርድ እንደሚያቀርብ ለተዋጊዎቹ መወያያ በቀረበው ሰነድ ላይ በገሃድ ተቀምጧል። ይሁን እንጂ አንድም ቦታ በስም አልጠቀሳቸውም። ከዚህ ቀደም በህወሃት መካከል ክፍፍል ሳይፈጠር በመቀለ ዩኒቨርስቲ በተሰራ ጥናት ሻዕቢያና ወያኔ በከፍተኛ ደረጃ ስብእናን የሚፈታተን ጥፋት መፈጸማቸው፣ ጥፋት ተብሎ የቀረበው ደግሞ በዓለም ዓቀፍ ህግ እንደሚያስከስስ መገለጹ አይዘነጋም።
ህወሃት “ጦርነት ሰሪ ነን፤ ውጊያ ባህላችን ነው” በሚል ወደ አፋርና አማራ ክልል ዘልቆ የፈጸመውን ጥፋት፣ እንዲሁም መንግስት ለመገልበጥ ደብረብርሃን እስኪደርስ ያደረሰውን ሰባዊና ቁሳዊ ጥፋት እንደ ፍትሃዊ ጉዳይ መውሰዱን በደሉን በመዘርዘር የሚቃወሙ “ህወሃት በስልታን ላይ በነበረበት ወቅት በተለይም በወልቃይት ጠገዴ፣ በሶማሌ ክልል እና በኦሮሚያ ላደረሰው ግፍ፣ ለሰወራቸው ንጽሁሃን፣ እንዲሁም በጅምላ ለገደላቸው ሁሉ ለፍርድ ሊቀርብ ይገባዋል” በሚል አሁን ድረስ እየገለጹ ነው። ህወሃት የፈጸመው በደል ከፍተኛ በመሆኑ፣ አብረውት ጠብመንጃ ለመተኮስ እየሰሩ ያሉትንና አስቀድመው ጀመረው አብረው እየሰሩ ያሉትን በባንዳነት ይፋርጃሉ። ከህወሃት ጋር ብቻ ሳይሆን ከሱዳን፣ ኤርትራና ሌሎች የውጭ ኃይሎች ጋር በማበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ በግልጽ አቋም ለያዝ ጥምረት አገልጋይ መሆናቸውን ይከሳሉ።
ከሁለቱም ወገን ቅሬታና የከፋ ተቃውሞ እያስተናገደ ያለው ጽምዶ፣ ከተቃዋሚዎችም ዘንዳ ተቀባይነት አላገኘም። የተከፈለው ህወሃት አንድ ወገን በከፍተኛ ደረጃ ጥስምዶን በመቃወም፣ የታጠቁ ኃይሎች በማደራጀትና ህዝቡን በማንቃት ያደረሱት ጫና ከፍተኛ መሆኑን ያልሸሸገው ሰነድ ሙሉ ትርጉም ከስር ያንብቡ።
I.መግቢያ
ስለ ፅምድ/ጥምረት አጀንዳ ሆኖ ከተነሳ ጀምሮ ይህንን በተመለከተ በሰራዊታችን ውስጥም ውይይት መደረጉ ይታወሳል። ሆኖም አሁንም ስለ ጥምረቱ አስፈላጊነት እና ምንነቱን የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎች የውይይት አጀንዳ ሆነው ቀጥለዋል።
እነዚህ የሚነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች መነሻቸው ከተለያየ ክፍሎች የሚነሱ ላይሆኑ ይችላል። ከእነዚህም አንዱ፣ በጥምረቱ/በጽምዶ ውስጥ ያሉ ኃይሎች ባለፉት ሁለት ዓመታት በትግራይ ሕዝብ ላይ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት እጃቸው ያስገቡ ወይም ተሳታፊ የነበሩ መሆናቸው ነው። አሁን ደግሞ ከእኛ ጋር በመሆን የብልፅግናን ሥርዓት ለመታገል መግባታቸው፣ በቀድሞ ወንጀላቸው ላይ በመመስረት ብዙ ጥርጣሬና ስጋት እንዲነሳ ሊያደርግ የሚችል መሆኑ የሚታወቅ ነገር ነው።
ይህ እንዲህ እንዳለ ሆኖ ጥምረት አድርገን የብልፅግናን ሥርዓት ካስወገድን በኋላ ቀጥሎ የሚመጣ አደጋ እነዚህስ መልሰው ወደ ሌላ ጦርነት እንዳይገቡ እና በተወሰነ መሰረታዊ ጥያቄዎች ለማስመለስ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ የሚል የብልጽግና ውድቀት በኋላ የሚመጣ ስጋት መነሻ በማድረግ ሊነሳ የሚችል ጥያቄ እና ሀሳብ መሆኑ በጥምረቱ/በጽምዶ እስካሁን አጀንዳ እየሆነ መቀጠሉ ግልጽ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም የክህደት ኃይሎች ከራሳቸው የሆዳምነት ፖለቲካ እየተነሱ የሚያሰራጩት ፕሮፓጋንዳ፣ በጉዳዩ ላይ የራሱ ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል።
ስለዚህ የዚህ ጽሑፍ መነሻ በጥምረት ጉዳይ ላይ የሚነሱትን ጥያቄዎችና ሀሳቦች፣ የብልፅግናን ሥርዓት ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ውስጥ ያለውን አስፈላጊነትና ጥቅም ግልጽ ለማድረግ የተዘጋጀ አጭር ጽሑፍ ነው።
II. የዚህ ጽሑፍ ዓላማ
በአመራሮቻችን እና በአባላቶቻችን ዘንድ የጥምረት/ጽምዶ መፍጠር ሕልውናችንና ጥቅሞቻችን ለማረጋገጥ <<ዳግም የዘር ማጥፋት ጦርነት አይደገምም>> ብለን እያደረግነው ያለነው ትግል የሚኖረው ጥቅም እና ዓለማ በአስፈላጊነቱ ላይ ተጨማሪ ዓቅም በሚደረገው የሚጨበጥ የጋራ እንቅስቃሴ የሚኖረው ሚና ግልጽ ለማድረግ ነው።
III, የጽምዶ ምንነት፣ ለምን ወደ ጥምረት/ጽምዶ ገባን በዚህ ጉዳይ የሚነሱ ሀሳቦች እና ጥያቄዎችን በተመለከተ
1. የጽምዶ/ጥምረት ምንነት
ከዚህ በፊትም በዚህ አጀንዳ ዙሪያ ውይይት መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፣ ጥምረት/Alliance የሚባለው ነገር በታሪክ ከጦርነት መጀመር አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ያለነው እየተደረጉ ባሉ ጦርነቶች ከጥምረት ውጭ አይደሉም።
ጽምዶ/ጥምረት/Alliance ማለት የህልውና አደጋ ወይም ስጋት ያለባቸው፣ ወይም እንዳለባቸው የሚያምኑ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሀገራት ወይም የተለያዩ ኃይሎች፣ የጋራ የህልውና አደጋ ወይም ስጋት ብለው የሚያስቡትን ነገር ለማስወገድና ለመከላከል የሚፈጥሩት ወታደራዊ ወይም ፖለቲካዊ ስምምነት ነው።
በዚህ ላይ ግልጽ መሆን ያለባቸው ጉዳዮች አሉ። በሀገራት ወይም በተለያዩ ኃይሎች መካከል የጋራ የህልውና አደጋን ለመከላከልና ለመመከት የሚፈጠረው ጥምረት (Alliance)፣ በሁሉም በመካከላቸው ቀደም ሲል በነበረ ግንኙነት፣ ወይም የወደፊት ባላቸው የጋራ ጥቅምና ዓላማ፣ ወይም በርዕዮተ ዓለም አንድነት ላይ የሚያደርጉት ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ዓለማና ጥቅም ያላቸው አካላት አሁን ለገጠማቸው የጋራ የህልውና አደጋ የሆነ ሃይል ለማስወገድ ብቻ ሊተባበሩ የሚችሉ መሆናቸው ነው።
ትናንት እርስ በርሳቸው ሲዋጉ የነበሩ ኃይሎች ለጊዜው ጉዳያቸውን ገታ አድርገው የጋራ ጠላት ወይም አደጋ በመኖሩ ሊተባበሩ ይችላሉ። እንዲሁም የተለያየ የሥርዓት አመለካከት ያላቸው ኃይሎች፣ ለሁላችንም አደጋ ነው ብለው የሚያምኑትን ኃይል ለመከላከል የራሳቸውን የሥርዓት አመለካከት ለጊዜው ትተው ጥምረት (Alliance) ሊፈጥሩ ይችላሉ።
ለዚህም አንድ ምሳሌ አሜሪካና ሩሲያ ናቸው። አሜሪካ ካፒታሊዝምን ስትከተል፣ ሩሲያ ደግሞ ሶሻሊዝምን ትከተል ነበር። ሆኖም የጀርመን ኃይል ለሁለቱም የጋራ አደጋ በመሆኑ ጥምረት/ Alliance ፈጥረው ጀርመንን ተዋግተው አሸንፈዋል።
ጥምረት ከጀመርክ በኋላም ሁልጊዜ እንደተጀመረበት ሁኔታ የመቀጠል ዕድል ላይኖረው ይችላል። በጥምረቱ ውስጥ የገቡ አንዳንድ ኃይሎች በመንገድ ላይ ሌላ ጥምረት ሊፈጥሩ ይችላሉ።
ለምሳሌ፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀርመንና ሩሲያ ሆላንድን ለመውጋት ጥምረት ፈጥረው ነበር፣ ከ10 ቀናት በኋላ ግን ጀርመን ይህንን ጥምረት አፍርሳ ሩሲያን በራሷ ለመውረር ጀመረች።
ሌላዉ ፅሞዶ/Alliance በመፍጠር የህልውና አደጋ ነው ተብሎ የተጠራዉ ኃይል ካሸነፍክ በኋላ እንኳን በመከፋፈል ወደ መለያየት እና ወደ ጦርነት እስከመግባት ሊያጋጥም ይችላል።
ሩሲያ እና አሜሪካ ጀርመንን ካሸነፉ በኋላ እንደሚከተሉት ስርዓት በነበራቸው ልዩነት መነሻ በድሉ ላይ ተለያይተዋል። በአገሮች ክፍፍል (ሩሲያ እጀርመን የነበሩ መሬቶቿን ወሰደች) ከዚህ በኋላ ለ40 ዓመታት በነበራቸዉ የስርዓት አመለካከት ቀዝቃዛ ጦርነት ተብሎ የሚጠራውን የመፋጠጥና እና አንዱ ሌላውን የመጠበቅ ጊዜ አሳለፋቸው ይታወቃል።
ሌላዉ የእኛን ጄኖሳይዳዊ ጦርነት ስንመለከት የብልፅግና ጆኖሳይዳዊ ስርዓት የተለያዩ ኃይሎች የውጭ አገር ኃይሎች ያከተተ ፅምዶ/ጥምረት በመፍጠር በእኛ ላይ ከባድ አደጋ ፈጥረዋል። ከፕሪቶርያ ስምምነት በኋላ ግን አብይ አሕመድ ገንዘብ ከፍሎ ያስገባቸዉ ኃይሎች በተቃራኒው የብልፅግና ስርዓት በመቃወም ጦርነት ገብተዉ እየተዋጉ ይገኛሉ፤ሌሎቻቸዉ ደግሞ በጦርነት መንፈስ ላይ ይገኛሉ።
በ17 ዓመት የትጥቅ ትግላችን በወቅቱ የነበረዉ የሻዕብያ ኃይል ፅምዶ በመፍጠር ከፍተኛ ውድመት ከደረሰ በኋላ ተለያይተዋል።
ከዚህ የምንማረዉ ጉዳይ ቢኖር ዓላማህ እና ህልውናህን ለመከላከል የሚያግዝ ፅምዶ አሰላለፍን በማስተካከል፣ ወዳጅነት መፍጠር እና አብሮ መስራት ያለ እና የነበረ ስለመሆኑ፤ ከዚህ ቀደም የበደለህ ኃይል የተዋጋህ ቢሆንም አሁን የጋራ የህልውና አደጋ ባለበበት፣ ይህንን የህልውና አደጋ የሆነዉን ጠላት ለማስወገድ ፅምዶ/ጥምረት መፍጠር በእኛ ያልተጀመረ አሁንም ያለ እና የነበረ ነው።
ትናንት የወጋን፣ የበደለን፣ የጄኖሳይድ ወንጀል የፈፀመብን ኃይል ከራሱ የህልውና አደጋ በመነሳት “አሁን እንተባበር” ሲል መግፋት አይቻል። ከዚህ ቀደም እነዚህን ኃይሎች ያስተባበረዉና አሁንም የትግራይ ህዝብ የህልውና አደጋ የሆነዉ የብልፅግና ስርዓት እንዲደመሰስ “ከአንተ ጋር አብራለሁ” የሚል ጥሪ ሲያቀርብ “ትናንት በድልኸኛል አታስፈልገኝም” በማለት ለብቻ መቆም እና ጥግ ይዞ መጠበቅ ሞኝነት እና አቅም ማባከን ይሆናል።
የትናንት ወንጀሎች በይደር ይዞ በሕግ እና በፍትሕ እንዲረጋገጥ፤ አሁን ስላለዉ የህልውና አደጋ በመከላከል ከእኛ ጋር የብልፅግና ስርዓት ወደ መቃብሩ አስገባለሁ ብሎ የወሰነ ኃይል እስከሚሄደዉ መንገድ ይሂድ መጠቀም ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። ይህ የህልውና ጉዳይ ቀዳሚነት በማድረግ የነገ አደጋዎች በመቀነስ ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ዕድሎች በአግባቡ አንድ በአንድ ለመጠቀም ትክክለኛ አቅጣጫ ስለመሆኑ ይህን ተቀበሎ በትኩረት በመስራት አጥጋቢ ዉጤት ማስመዝገብ ይገባል።
2. አሁን ወደ ፅምዶ ለምን ገባን? ያለዉ ጥቅም ምንድን ነው?
በዚህ ጉዳይ ላይ የ 2013-2014 ዓ/ም ጄኖሳይድ ጦርነት በብልፅግና ጄኖሳይዳዊ ስርዓት የተሰበሰቡ የተለያየ ዓላማ ያላቸዉ፤ ሆኖም በትግራይ ህዝብ ጄኖሳይድ ዘመቻ የትግራይ ህዝብ የህልውናችን አደጋ ነው በማለት ፅምዶ ፈጥረዉ የፈፀሙት ጄኖሳይድ፤ ለዚህም ያለምንም ፅምዶ ብቻችን በመሆን ከብዙ የተፃመዱ ኃይሎች በመግጠም በመጨረሻ በትግራይ ህዝብ እና ሰራዊት ጀግንነት፣ ፅናት፣ በመከላከል ህልውናችን እንዳይጠፋ ፍላጎቶቻቸውን በመስበር ብናመክነውም ብቻችን በመሆናችን የደረሰብን ኪሳራ ትላቅ ነው።
አሁንም የብልፅግና ስርዓት የትግራይን ህዝብ ከምድረገፅ የማጥፋት ግቡ ባለማሳካቱ ሁለተኛ ዙር የጄኖሳይድ ጦርነት ለመፈፀም እየተዘጋጀ ይገኛል። ይህ ሲያደርግ ግን እነዚያ በመጀመርያ ዙር የጄኖሳይድ ጦርነት ተጣማጅ የነበሩ ኃይሎች ፈርሰዉ ራሱ ብልፅግና የህልውናችን አደጋ ነው በማለት ከብልፅግና ጋር ወደፊት ጦርነት የገቡበት ሁኔታ ነው ያለዉ።
በአማራ እየተካሄደ ያለዉ ጦርነት የፋኖ ኃይል የብልፅግና ስርዓት ለመደምሰስ በሚታገሉበት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትም እንዲሁ በተመሳሳይ ዓላማ ጦርነት ላይ በሚገኝበት፣ የአፋር፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል፣ አገዉ ኃይሎች እንደየአቅሞቻቸዉ ስርዓቱን ለማፍረስ በሚታገሉበት ወቅት፤ ብልፅግና የህልውናችን አደጋ ነው ሊደመመስ ይገባል ብለው ባመኑበት ወቅት በአንድ ላይ ፅምዶ ፈጥረዉ አቅሞቻቸዉ አቀናጅተዉ በጊዜ እና በቦታ በሚገጥሙበት ጊዜ የሚፈጠረዉ አቅም፣ በብልፅግና ስርዓት ላይ የሚደርሰዉ ምት፣ የጠላት ዕድሜ ለማሳጠር በሚገባ ይጠቅማል። እኛ ደግሞ ብቻችን ከመሆን ከእነዚህ ኃይሎች ጋር በመጣመድ አቅማችን እንዲቀናጅ በማድረግ የብልፅግና ስርዓት ሁሉም አቅሙን አሰባስቦ ወደ እኛ እንዳይመጣ ወደ ሌሎቹም በተመሳሳይ በየተራ እንዳያጠቃ አቅሙን ከፋፍሎ ለመደምሰስ ትልቅ ጥቅም አለዉ።
3. በፅምዶ/ጥምረት ውስጥ የሚነሱ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች፦
እንደሚታወቀው በፅምዶ ውስጥ የገቡ ኃይሎች፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት የዘር ማጥፋት ጦርነት ውስጥ የብልጽግና ስርዓት አካል እና ተጣማጅ ኃይል በመሆን በህዝባችን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተሳትፎ ያላቸዉ መሆኑ ሁለት ስጋቶችን/ጥያቄዎችን ያስነሳል።
ከባለፈው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አጋር ከነበሩ ኃይሎች ጋር እንዴት ጥምረት እንፈጥራለን? የሚለዉ አንዱ ጥያቄ ሲሆን ሁለተኛዉ ነጥብ አሁንም ከፅምዶ ኃይል ጋር የብልጽግና ስርዓት ብንደመስስም እነዚያ ጥያቄዎቻችን ማለትም የሉዓላዊ መሬቶቻችን እና የተፈናቃዮቻችን መመለስ …. ወዘተ ጥያቄዎች በተቃራኒው ወደ ሌላ ጦርነት እንደማያስገባን ምን ማረጋገጫ አለን የሚሉ ኃሳቦች የሚንጸባረቁበት ነው።
እዚህ ላይ ግልፅ ሊሆን የሚገባዉ እነዚህን የሚቀርቡ ሀሳቦች እና ስጋቶች መነሳታቸዉ ተፈጥሯዊ እና ትክክለኛ ጥያቄ መሆኑ ነው። እዚህ ጉዳይ ላይ ሊፈጠር የሚገባው ግልጽነት ከዚህ መሠረታዊ ኃሳብ የሚነሳ እና ምላሽ የሚሰጥ ሊሆን ስለሚገባ በእነዚህ ሁለት አስተሳሰቦች እና አመለካከቶች አንድ በአንድ መመልከት አስፈላጊ ነው።
3.1. ጠላቶቻችን የነበሩትን አንዳንድ ኃይሎች እንዴት በመተማመን እንጣመዳቸዋለን?
በትግራይ ህዝብ ጄኖሳይድ ጣልቃ የገቡ አንደአንድ የብልጽግና ስርዓት ተጣማጆች የነበሩ አሁን እነሱን በማመን መጣመድ አደጋ ነዉ የሚል ካለፈዉ ቁስል የሚነሳ ኃሳብ ሲታይ መነሳት የማይገባዉ ጥያቄ ነው ሊባል አይችልም። በትግራይ ህዝብ ላይ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተሳትፈዋል እንዲሁም ከባድ በደል በእኛ ላይ ፈጽመዋል፤ ልክ ነው። አሁን ግን ያ የነበረዉ ፅምዶ ፈርሶ ለራሳቸዉ የህልውና አደጋ ላይ ወድቀናል በማለት ከብልፅግና ጋር ጦርነት ላይ ገብተዉ ይገኛሉ። የነበረዉ አሰላለፉም ተቀይሯል።
የብልፅግና ስርዓት አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ ሁለተኛ ዙር የጄኖሳይድ ጦርነት ለመክፈት በሚዘጋጅበት በአሁኑ ወቅት፣ በተመሳሳይ መልኩ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ አገው በተደራጀ መንገድ ስርዓቱን በመቃወም የሚዋጉ ኃይሎች በጦርነት ላይ ናቸው።
እነዚህ ለየብቻቸዉ ጸረ ብልፅግና ትግል ከሚያካሂዱ ፅምዶ/ጥምረት በመፍጠር ከታገሉ በሚፈጠረው አቅም በመጠቀም “አብረን እንስራ” ካሉ እነሱም ተጠቃሚ የሚሆኑበት እኛም የምንጠቀምበት ሲሆን በጠላት ላይ የተቀናጀ አቅም በማሳረፍ ሥርዓቱ ሊደመሰስ የሚችልበትን ሁኔታ ከመገንባት ውጭ ሌላ አማራጭ የለም።
አሁን እዚያው በትግራይ ጄኖሳይድ ላይ እጅ የነበራቸዉና በደል የፈጸሙትን፣ አሁን ወደ ፅምዶ መግባታቸዉ፣ በሕግ ተጠያቂነትና ፍትህ ሳይሰፍን የምሕረት ሰርቲፊኬት መስጠት ማለት አይደለም። መጀመሪያ አሁን የገጠመንን የህልውና አደጋ የሆነውን በጥምረት እና አብሮ በማፍረስ ቅድሚያ ሰጥተን፣ ከዚያ በኋላ የደረሱብንን በደሎች፣ ጅኖሳይድ ታሪካዊ ክሶችን የሚገባቸውን በሕግ ዓይን እንዲታዩና ፍትህ እንዲያገኙ ማድረግ፣ እንዲሁም ህልውናች እና አቅማችንን ይዞ ለመውጣት፤ የመጀመሪያው ሥራ ይህንን ሥርዓት ማፍረስና ለዚህ የሚሆን አቅም መሰብሰብ ስለሆነ ይህንን ዕድል መጠቀም ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።
አንዳንዶቹ በዚያ ፅምዶ/ጥምረት ውስጥ ያሉ ጠላቶቻችንና ጄኖሳይድ የፈፀሙብን ነበሩ በማለት ለብቻችን ነው የምንሆነዉ ካልን ለብቻ የምንጠቃበት እና የጠላት አቅም የበላይነት አግኝቶ ትግላችን እንዲራዘም የሚያደረግ ሁኔታ እንዲፈጠር ዕድል መስጠት ነው። በሌላ በኩል ስናየው፣ በተናጠልና በየቦታዉ በመግጠም በጠላት ከመዳከም ይልቅ፣ አንድ ላይ በመጣመር እና አቅም በመሰብሰብ ሥርዓቱን ወደ መቃብሩ ለማውረድ የተሻለው አማራጭ በመሆኑ ይህ ዕድል ያለፈውን ጉድለቶችና ልዩነቶቾ በማየት ለየብቻ መሄድ የጠላታችን ዕድል ማሳደግ እንደሆነ አድርገን ልናየው ይገባል።
በዚህ ግልፅ ልናደርገው የሚገባን ፅምዶ/ጥምረት ማለት፣ አንዱ ለአንዱ ነፃ/ሐራ ለማውጣት የሚጠጋ ሳይሆን፤ በመደጋገፍ እና ራስህን በመቻል፣ ራስህ የምትወስነውና በራስህ አቅም ተማምነህ በምትሠራው መቆም (ጽናት) የሚመሠረትበት ነው። አቅምህን በገነባህ ቁጥር በፅምዶዉ ተመራጭ እና ተደማጭ ትሆናለህ። በዚህ ፅምዶ ውስጥ የሚኖረውን የአንዳንዶቹን መቀነስ እና መፍረስ የራስህን አቅም በማሳደግ ነው ጉድለቱን የምትሞላው። ስለዚህ እነዚያ ተጣማጆች እኛ ነፃ እንድናወጣቸዉ የሚያስቡ፤ በተመሳሳይ እኛም ነፃ እንዲያወጡን የምናደርገዉ ጥምረት የለም። ስለሆነም ራሳችን የህልውና አደጋ እስከሚወገድ፣ አንዱ ሌላውን ተጨማሪ አቅም እንዲሆን መሳብ ትክክል ስለሆነ ነው።
3.2. ከብልፅግና መፍረስ በኋላ ያለው የአጋሮቻችን የሚፈጠር ስጋት
እየፈጠርን ያለነዉ ፅምዶ በሁሉም መስኮች እኩል (ተመሳሳይ) ዓላማ፣ አረዳድ እና ተመሳሳይ እምነት ይኖረናል ብሎ መደምደም አይቻልም። ነገር ግን የጋራ ጠላት የሆነው የብልፅግና ሥርዓት ከተወገደ በኋላ፣ እርስ በርሳችን እንዴት ነው የምንኖርዉ የሚል ስጋት እንዳለ ማሰብ የማይቀር ነው።
ከብልፅግና በፊት ወይም ደግሞ ከብልፅግና ሥርዓት መውደቅ በኋላ የትግራይ ሕዝብ የህልውና የስጋት አደጋ ሙሉ በሙሉ እንደሚረጋገጥ ማሰብ የሚል አስተሳሰብ እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም።
ከብልፅግና ሥርዓት መፍረስ በኋላም ቢሆን ሌላ ዓይነት አሰላለፍ ሊመጣ እንደሚችል፣ በዚህም አዲስ አሰላለፍም ሌላ ተጣማጅ ማግኘት እንደሚቻል መገንዘብ ያስፈልጋል።
አሁን በምናደርገዉ ፅምዶ ብዙ የሕዝብ ለሕዝብ መደጋገፍና ተፅዕኖ ዕድል እንደሚሰጥ ሁሉ፤ ከፕሮፓጋንዳ እና መጠላላት ስሜት የያዘዉ ሊፈታ እንደሚችል ዕድል እንዳለዉ ማየት ይቻላል። ይህም በቀጣዩ ትግል ውስጥ የራሱ የሆነ አቅም እንደሚሆን መረዳት ያስፈልጋል።
ከሁሉም በላይ ደግሞ ትግላችን አጠናክረን አሸናፊ ሆነን መውጣታችን፣ ይህንን ጠብቀን ከቀጠልን የተሻለ አቅምና ጥንካሬ በመያዝ የተሻለ ተፅዕኖ ፈጣሪነት እና ተደማጭነት አግኝተን የምንወጣበትን ሁኔታ መፍጠር ይቻላል። ይህም ሊፈጠር ከሚችል ማንኛውም ዓይነት ስጋት ጠንክረን እንድንቆይ እንደሚያግዘን ማየት ይቻላል።
በዚህ ልንገነዘበው የሚገባ ጉዳይ፣ ቀደም ሲል እንዳልነው የጄኖሳይድ አካላት ነበሩ ብለን ስናስብ የነበርነውን ያህል፣ ከብልፅግና ሥርዓት መፍረስ በኋላስ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ብለን እንጠራጠራለን፤ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ ይነስም ይብዛም ጥርጣሬ ይሁን ስጋት ሊኖራቸዉ ይችላል። አሁን የምንጣመዳቸው አሁን ባለዉ የጋራ የህልውና አደጋና ዋና ጠላት የጋራ ነው በማለት፣ በጋራ መተባበር ያለዉ አቅም (ትርጉም) ለሁላችንም ስለሚጠቅም ነው። ለጥቅማችን ስንል ጥምረት ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለን የምናምን ቢሆንም፣ እኛ ብቻ ስጋትና ጥርጣሬ ይዘን፤ እነሱ ግን በሙሉ ልብ እና ንስኃ አምነዉን ሊሆን እንደማይች መረዳት ያስፈልጋል።
በዚህ የጋራ ፅምዶ ጉዳይ የትግራይን ህዝብ ከድቶ ከጆኖሳዳዊ ስርዓት ጋር በመወገን ለሆዱ እየሰራ ያለዉ ይህ የክህደት ሀይል ይህንን ፅምዶ/ጥምረት ለማፍረስ ጥላሸት የመቀባት ስራ እየሰራ ይገኛል።
እኛ ጄኖሳይድ ከፈፀሙብን መካከል ፍቅር እና ጥቅም ካገኘንበት መርጠን እንደገባን፣ በአንዳንዶች ደግሞ “የሻዕቢያ አጋሮች ሆነዋል” እያሉ፣ ከዚያም “ሻዕቢያ ለትግራይ ህዝብ የበለጠ ጄኖሳይደር የፈፀመ ነው” በማለት የብልጽግና ስርዓት ጄኖሳይድ ተጠያቂነት ነፃ ለማውጣት፣ የአብይ አሕመድን ወንጀል ለማጠብ፣ ከዚያም በላይ የብልጽግና ስርዓት እንዳይፈርስ ሆዳቸውና ሀብታቸዉ በእሱ ላይ ስለተመሰረተ የተለያዩ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን እያካሄዱ ይገኛሉ። ከዚህም በላይ፣ ለሆዳቸው የሚኖርለት ስርዓት በትግራይ ህዝብ ላይ ሁለተኛ የጄኖሳይድ ጦርነት እንዲጀምር የሚለምኑበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
በእኛ በኩል በመመዘኛችን ፋኖ ትንሽ ወንጀል ፈጽሟል። ሻዕቢያም በተመሳሳይ የፈጸመውን ወንጀል አሳንሰን ከጄኖሳንደሮች መርጠን የገባንበት ጉዳይ የለም። የብልጽግና ስርዓት የእነዚያ ሁሉ የጄኔሳይድ ኃይሎች አደራጅቶ፣ ደመወዝ ከፍሎ እና ጥይት ሰጥቶ አስተባብሮ ጄኖሳይድ እንዲፈጸም የመራ ወንጀለኛ ስርዓት ነው።
በአሁኑ ወቅት መደመሰስ አለበት ስንል፣ አሁንም የመጀመሪያ ግቡ ስላልተሳካለት ሁለተኛ የጄኖሳይድ ጦርነት ለመክፈት የሚፈልግ፣ ሉዓላዊ መሬቶቻችንንና የተፈናቀለውን ህዝባችንን ለመመለስ የማይፈልግ፣ የደረሰብንን የኢኮኖሚዊ ውድመት ሰርተን እንዳናገግም፣ ድህነት እንዲቀጥል፣ እንድንራብና እንድንሞት የሚሰራ ኃይል ነው። ከዚህም በላይ አሁንም ሁለተኛ ጊዜ ጄኖሳይድን ለመፈፀም እየተሽቀዳደመ የሚገኘዉ፣ ሌሎቹ ወደ እኛ ከመተኮስ ይልቅ ብልጽግናን ላይ የሚታገሉ ናቸው።
ይህ ቢሆንም፣ የክህደት ኃይል የብልፅግና ወንጀል ለማፅዳት ከብልጽግና ጋር እንደሚተባበረዉ፣ በጄኖሳይድ የተካፈሉት ሌሎችም አሁን ተጣማጅ የሆኑ ኃይሎች የፈጸሙትን ወንጀል አንምርም፣ ምሕረትም አንሰጥም። አሁን በብልጽግና ስርዓት የደረሰብንን የህልውና አደጋ ለመከላከል፣ የተፈጸመብንን ጄኖሳይድ በህግ ፍትሕ እንዲያገኝ በቦታው በማስቀመጥ፣ አሁን የደረሰብንን የህልውና አደጋ ለማስወገድ ፅምዶ እየፈጠርን ያለነዉ።
የእነዚህ የክህደት ኃይሎች የስም ማጥፋት ዘመቻ፤ እንደነሱ የብልጽግና ስርዓት ጥፋት አላደረሰም፤ ከፍተኛውን የፈጸሙት ሌሎቹ ናቸው፤ አሁን “የትግራይን ጥቅም የሚረጋገጠዉ ከብልጽግና ጋር መሆን ነው” እያሉ፣ በቁም ነገር ግን ሆዳቸውንና ስልጣናቸውን ማዕከል አድርገው ህዝባቸውን የካዱ፣ ወደእነሱ መንገድ አንሄድም። የብልጽግና ስርዓት ህዝባችን ከማጥፋት ሌላ ተፈጥሮ የለውም።
4. ይህ ፅምዶ ለእኛ ጥቅም እንዴት ይውላል? በተግባራዊ እንቅስቃሴዎቻችን ያለን ሚና
የብልፅግና ስርዓት ለመደምሰስ ከሌሎች ፀረ ብልፅግና ኃይሎች የሚሰሩ ኃይሎች ፅምዶ/ጥምረት ስንል ከሁሉም በፊት እምነታችን እና መነሻችን በራሳችን አቅም ጥንካሬ የተመሰረተ እንዲህን ማመን ያስፈልጋል። ያ የምናደርገውን ፅምዶ አሁን ባለን አቅም የሚጨምር እንጂ የእኛን አቅም የሚተካ ሊሆን አይችልም። በራሳችን ውስጣዊ አቅም እና ጥንካሬ መሰረት ስናደርግ ፅምዶው/ጥምረቱ ላይ ያለን ተፅዕኖ እና ተደማጭነት ያድጋል። በሂደት የፅምዶ ስራ ይሁን የብልፅግና ስርዓት ከደመሰስን በኋላ ሙሉ አቅም ይዞ ለመውጣትእና ሚናችን ሊያድግ የሚችለዉ በራሳችን መተማመን ውሳጣችን እያጠናከርን ስንሄድ እንደሆነ ግልፅ ሊሆን ይገባል።
ይህንን እንደ መነሻ በመውሰድ ፅምዶ/ጥምረት ላይ በመግባታችን የምንፈጥረዉ አቅም በመገንዘብ ከፅምዶ ኃይሎች ሊኖረን ስለሚገባው መደጋገፍ በአግባቡ በመረዳት ይህንን በሚጠቅም አካሄድ እና እምነት ልንሰራ ይገባል።
የብልፅግና ስርዓት እንዲደመሰስ ከእኛ ጋር የሚተባበሩ የፅምዶ ኃይሎች በሁሉም ግንኙነቶቻችን የመደጋገፍ ፍላጎት እና ተግባር ልናሳያቸዉ ይገባል። መቀናጆዎቻችን ይነስ ይብዛ የሚወክሉት ህዝብ አለ፤ የህዝቡ ባህል ማክበር ከማንኛውም ጫና እና ክብረ ነክ የሆነ ተግባር ከመስራት ልንቆጠብ ይገባል። ይህ በይሉኝታ ሳይሆን ከማንኛውም ህዝብ ጥላቻ ሆነ ቅሬታ የለንም። ከህዝባዊ ባህርያቶቻችንም ልንነሳ ይገባል።
በሰራዊቶቻቸዊ ሆነ በግለሰብ አባላቶቻቸው ከሚታይ ችግር ማጋለጥ ይሁን ማንኳሰስ ላይ መድረስ የለብንም። አንድአንድ ችግሮች በእኛ ላይ የሚታዩ ናቸዉ። ችግሮች ሲፈጠሩ በመፍትሔዎቻቸዉ ላይ መምከር እንጂ በማጥላላት ላይ የተመሰረተ መሆን አይገባም።
በአንድ ላይ ተልዕኮ ወስደን በምንሰራበት ወቅት ይህ ወሰዱ፣ ይህ የኛ ነው በማለት ወደ ግጭት እንዳንገባ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው። ከወሰዱት ወይንም አግኝተውታል የምንለዉ ማቴሪያል ባሻገር ዋና አቅማቸው በማሳረፍ ከእኛ ጋር በመደጋገፍ የሚሰሩት ስራ ይበልጣል፣ ይጠቅማል።
በግለሰብ ደረጃ ተራ ግጭት እና እልኽ እንዳይፈጠር አስቀድመን ራሳችንን እናስተዳድር። ከማንኛውም ዓንነት የግል ግጭት እንራቅ። በመግባባት እና ትዕግስት በማድረግ እንዲፈታ ማድረግ።
መደጋገፍ እና መተሳሰብ በሚያስፈልገበት አጋጣሚ ሲፈጠር ሙሉ ሰላምታ እና ወገናዊነት የሚያንጸባርቁ አካሄዶችን መከተል። ለምሳሌ ቁስለኞቻቸው መደገፍ እና ማሳከም ወዘተ… ጥንቃቄ በሚያስፈልግበት ወቅት እንዲጠነቀቁ ማድረግ በአውደ ውጊያ መደጋገፍ እንዲኖር ማድረግ።
የትግራይ ህዝብ ህልዉና እና ብሔራዊ ጥቅም በብልፅግና መቃብር ላይ ይረጋገጣል‼
ከትግራይ መከላከያ ኃይሎች የፖለቲካ ጉዳዮች ማዕከል
ነሐሴ/2018 ዓ/ም ከ(ዶ/ር ገሰሰው ወንድም ፌስቡክ) ትርጉም የተወሰደ
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






