“የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሚቀጥለው ሳምንት ኤርትራን ይወራል በውስጥ ያለው አመጽ ይፍጠን” የሻዕቢያ መረጃ ያስተላለፈው መመሪያ

Date:

“አስችኳይ ነው። ሩጫው ከጊዜ ጋር ነው” በማለት ደጋግመው ገለጹ። ይህን የሚናገሩት አቶ ነዓምን ዘለቀ ናቸው። አቶ ነዓምን ይህን የሚናገሩት ለአቶ ልደቱና በቅርባቸው ላሉ የአመጽ አመቻች የቴክኒክ ኮሚቴ የተመረጡ አባላት ነው። እሳቸው ይህን ያሉት በውክልና እያገለገሉት ያለው ሻዕቢያ ዋሽንግቶን ባለው ሴሉ አማካይነት በሰጣቸው መመሪያ መነሻ ነው። “የአገር መከላከያ በአስበ ብኩል በሚቀጥለው ሳምንት ቃታ ሊስብ መመሪያ እየጠበቀ ነው። የውስጥ አመጽ ይጣደፍ” ሲል ሻዕቢያ መመሪያ አስተላልፏል። የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ዘወትር ዝግጁ ሆኖ እንደሚጠብቅ በተደጋጋሚ ማስታውቁ አይዘነጋም።

የአዲስ ሪፖርተር የዲሲ ተባባሪ የተለመዱ የመረጃ አቀባዮቹን ጠቅሶ እንዳለው አቶ ልደቱ ከአቶ ነዓምን የተቀበሉትን መረጃ ለሌላ የኮሚቴው አባል በመግለጽ አመጹ በቶሎ እንዲቀሰቀስና የመንግስት ትኩረት ወደ ውስጥ ግጭት እንዲያተኩር ማድረግ ግድ እንደሆነ አመልክተዋል።

አቶ ነዓምን የቀይ ባህር አፋሮች የሰሞኑ መግለጫ፣ከሦስት ቀን በፊት ወደ አስመራ በማቅናት ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ውይይት ያደረጉት የቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ሁ ቻንግቹን እና ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ አዲስ አበባ ደርሰው ከተመለሱ በኋላ በትህነግ አመራሮች መካከል ድጋሚ ይሀተነሳውን ውጥረት፣ ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን የሰጡትን ወቅታዊ መረጃና ሌሎች ኩነቶችን በማያያዝ “ኢትዮጵያ ወረራ ለመፈጸም ተዘጋጅታለች” በማለት ለአቶ ልደቱ ትንታኔ እንደሰጡ መረጃውን ያጋሩት አመልክተዋል።

ከትናንት በስቲያ በኢትዮጵያ አመጽ ለማነሳሳት የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። በስብሰባው ላይ ይህ ጉዳይ ሳይነሳ መግለጫ በማውጣት መበተኑን አዲስ ሪፖርተር ሰምታለች። በተከታታይ በተደረገ ስብሰባ ተደርጎ በነበረው የሰማይ ላይ ህየተቃውሞ ሰልፍ የሚፈለገውን ያህል ሰው አለመሳተፉ፣ ከአገር ቤትም ሆነ ከውጭ አገር ሕዝብ እንዲያምጽ እንዲቀሰቅሱ የተጋበዙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው፣ በአገር ቤት ተነሳሽነት እንደሌለ፣ ኢህአፓ ድጋፍ ቢደረግለትም ተሰሚነት ሊኖረው አለመቻሉ፣ አብረውት ያሉትም ፓርቲዎች ተጽዕንኖ የማሳደር አቅማቸው ደካማ መሆኑ፣ የተለመዱና የተሰለቹ ፊቶች ለውጥ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸው በደካማ ጎን ተገምግሞ ሲያበቃ “ዝግጅቱ የተሳካ ነበር” በማለት መግለጫ ያዘጋጀው ይህ ኮሚቴ “ኤርትራ ልትወረር ነው፣ እንፍጠን” የሚለው ጉዳይ አልቀርበለትም።

መረጃውን ያገኘው የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ እንዳለው፣ አንድ የቴክኒክ ኮሜቴው አባል አቶ ልደቱ በስልክ አቶ ነዓምንን በመጥቀስ ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል። በዚሁ መረጃ መሰረት ሻዕቢያ በሚቀጥለው ሳምንት የኢትዮጵያ ጦር አሰብን እንደሚይዝ መረጃ ደርሶታል።

“የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ዓለምን ወጥሮ ስለያዘ፣ የብልጽኛ መንግስት አጋጣሚውን ተጠቅሞ አሰብን ለመቆጣጠርና ከዛም አልፎ የኤርትራንና የኢትዮጵያን አፋሮች ከፊት አስልፎ በኤርትራ የስርዓት ለውጥ ለማድረግ ዝግጅቱን ጨርሷል” በማለት አቶ ነዓምን የሰጧቸውን መረጃ አቶ ልደቱ በስልክ የገለጹላቸው የመረጃው ምንጭ፣”አቶ ልደቱ በሰሙት ጉዳይ ተደናግጠዋል። በዚህ ቅጽበት እንዴት አመጽ ማስነሳት ይቻላል” ሲሉ ጠይቀዋል።

አቶ ነዓምን የትጥቅ ትግል የሚያደርጉት ክንፎች በተጠበቀው ደረጃ እየሰሩ አለመሆኑ አንስተው “አሁን ያለውን አማራጭ ሁሉ በመጠቀም አመጽ እንዲነሳ ሁሉንም አማራጭ መጠቀም አስፈላጊ ነው።” ብለዋል። ስም ሳይጠሩ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ የሚሰሙ የአዲስ ዘፈን አለመግባብቶችን፣ እንዲሁም የዘፈኖቹን ትርጉም በሚፈለገው መልኩ ለመቀስቀሻ መጠቀም እንዲቻል ዝግጅት እንዳለም ለአቶ ልደቱ መንገራቸውም ታውቋል።

የቴዲ አፍሮን ዘፈን ለአመጽ ማነሳሻ ለመጠቀም 888 የሚሉትን ቁጥሮች ከመንግስት ስምንት ዓመት ዕድሜ ጋር በማያያዝ “የማብቂያው ማብሰሪያ ነው ‘ድንኳን ጣል አፍርስ’ ይህን ያረጋግጣል” በሚል የተረጎሙ አሉ። የአመጽ አመቻቹ የቴክኒክ ቡድን የሚዲያ ክንፎችም “እየጠበቅንህ ነው” የሚል ካኔቴራ በመልበስ የፕሮፓጋንዳ ስራ ጀመረው ታይተዋል።

በአልበሙ ላይ ኢትዮሪካ በሚሉት ፊደሎች ላይ የአክሱምና የአንበሳ ምልክት መኖሩን በማመላከት “አክሱም የትግራይ፣ አንበሳው የአማራ ምልክት ነው አንድ ላይ ገጥመው በስምንት ዓመቱ የገዳውን ስርዓት ይጠርጉታል” በማለት አስተያየት የሰጡ ጥቂት አይደሉም። “ታዋቂ ነን” የሚሉ፣ ሌሎች “ታዋቂ ናቸው” ያሏቸው ከዘፈኑ ይፋ መሆን በፊት ስለቴዲ ምስክርነት በመስጠት በተጠመዱበት በአሁኑ ወቅት “ኢትዮጵያ ኤርትራን ልትወር ነው፣ እንፍጠን፣ አጋጣሚውን ሁሉ እንጠቀም” የሚለው ጥሪ ይፋ መሆኑ መረጃውን ላካፈሉ ወገኖች አስገራሚ ሆኖባቸዋል።

ቴድሮስ አፍሮ ዘፈኑን በስምንትወኛው ወር፣ በወሩ ስምንተኛ ቀን፣ በቀኑ ስምንተኛው ሰዓት “888” ላይ ይፋ እንደሚያደርግ ከማስታወቁ ውጪ ዝርዝር ያለው ነገር የለም። አጋጣሚ በመጠበቅ፣ ሁኔታዎችን በመንተራስ ዘፈን በመልቀቅ የሚታውቀው ቴዲ “ኤርትራዊ ነች” የምትባለው ሚስቱም ስለ “888” ይህ እስከተጻፈ ድረስ ያለችው ነገር የለም።

ከመንግስት ወገን መረጃ ለማግኘት ያደረኘው ጥረት ባይሳካም፣ የአገር መከላከያ ከፍተኛ መክንኖችና ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “አገር መከላከያ ሁሌም ዝግጁ ነው” በማለት አሰብን የማስመለሱ ጉዳይ የቀን ጉዳይ ካልሆነ ጥርጥር እንደሌለው በተደጋጋሚ ማስታውቃቸው የሚታወስ ነው። አሁንም በየመድረኩ ይህንኑ እያንጸባረቁ ነው። አሰብ እንዴት እደተሰረቀ በውቅቱ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ከፍተኛ መኮንኖችና የፖለቲካ አመራሮችም ያለማቋረጥ ምስክርነታቸውን እየሰጡ ነው።

ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗ በከፍተኛ ደረጃ ለውጪና ለድህንነት ስጋት መጋለጧ አሁን አሁን ይፋ በሆነበት በዚህ ወቅት “ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉና “በኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍኑኝ” የሚሉ ይህንኑ የኢትዮጵያን የባህር በር የማስመለስ አጀንዳ ለማሰናከል በየአቅጣጫው ዘመቻ ላይ መሆናቸው እንደሚያሳዝናቸው የሚናገሩ ኢትዮጵያዊያን “ታሪክ ይህንን አይዘነጋውም፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ በዚህ ደረጃ በግልጽና በገሃድ ክህደት ገጥሟት አያውቅም” እያሉ ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሜካናይዝድ ኃይል በተጠቀሰው አቅጣጫ በስፋት መስፈሩን፣ የቀይ ባህር አፋር ወኪልም “ዝግጁ ነን” በማለት ለአዲስ ሪፖርተር መናገራቸውን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት ተበተነ

አዲስ ሪፓርተር— በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን አስተናጋጅነት...

ሻዕቢያ ያደራጀው የአመጽ ቀስቃሽ ኮሚቴ ዲያስፖራው ስለፈራ አገር ቤት አመጽ ማስነሳት ቅድሚያው አደረገ

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ፤ ኢህአፓን ማገዝና ብረት ያንሱ ድርጅቶችን...

ኢህአፓ ሌላው የ “ሞዐ ተዋሕዶ” ክንፍ? “ከፈጣሪ የለም” ወደ የብሉይ ምሁር አመራር ሽግግር ሚስጢር

ሰራተኛ ሰፈር ዛሬ ፈርሷል እንጂ ምክር ነው። በየአንዳንዱ ቤት...

ፕሮፌሰር መሐመድ “ቀጣፊ ነው፤ የሚልኩብን እነሱ [ሻዕቢያዎቹ] ናቸው” ነዓምን

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ...