ቴድሮስ ካሳሁን ለሰዋሰው መልቲሚዲያ 33 ሚሊዮን ብር ከፍሎ በሰላም ፍቺ ማደረጉ ይፋ ሆነ

Date:

“ቴድሮስ በማህበራዊ ገጹ እውነቱን ለምን አይናገርም? በስማ በለው በማህበራዊ ሚዲያ የሚቀርበውን ውዝግብ መነሻው ፖለቲካ እንዲሆን ለምን ይፈቅዳል? ፍላጎቱ ከሆነም በተዘዋዋሪ ከሚሆን ለምን በገሃድ አያደርገውም? ሁልጊዜ ቀንና አጋጣሚን እየጠበቁ ማጩጯህ ለምን ልምድ ይሆንበታል? ስሙንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ስለምን ስራውን በሰላም ለአድናቂዎቹ አያደርስም? ከሙዚቃው በላይ ውዝግቡና የጅምላ ጩኸቱ አስልቺ ሆነ”

አዲስ ሪፖርተር – ቴድሮስ ካሳሁን አስቀድሞ ወስዶት የነበረውን ሃያ አምስት ሚሊዮን ብር ከአራት አመት የባንክ ወለድ ጋር ታሳቢ ተደርጎ በድምሩ ሰላሳ ሶስት ሚሊዮን ብር ለሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ከፍሎ በስምምነት ውል ማፈርሱንና በውል ማፈረሱ አግባብ ምንም ችግር እናልነበረ ተገለጸ። በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨውን መላምትና ሁከት የተሞላበት መረጃ አርቲስቱ ለምን እንደማያስተባብል በርካቶች ጥያቄ እያነሱ ነው።

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከ9 ዓመታት በኋላ  አዲስ አልበም በነገው ዕለት ለማቅረብ ቀጠሮ ከመያዙ ውጪ በግል የማህበራዊ ገጹ ተጭማሪ መረጃ አልሰጠም። ይሁን እንጂ ማኔጅመንቱን ጠቅሶ ኢትዮፒካሊንክ እንደዘገበው ውል በማፍረሱ ሂደት የተፈጠረ አለመግባባት አልነበረም።

አርቲስቱ ” ኢትዮጵያ ” የተሰኘውን አልበሙን የዛሬ 9 ዓመት ለአድማጩ ካደረሰ በኋላ ነገ ” ኢትዮሪካ ” የተሰኝ አልበሙን በራሱ የዩትዩብ ቻናል ላይ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ማዳመጫ ድረገጾች ላይ እንደሚለቅ ለመልቀቅ ዝግጅቱን መጨረሱን ያመለክተው ዘገባው፣ የስምንት ቁጥሮችን ስብስብ ለመጠቀም ራሱ ዘፋኙ ባለው ፍላጎት ምክንያት ቀደም ሲል ከታሰበው ቀን ቀድሞ ዘፈኑ እንዲለቀቅ መወሰኑ ታውቋል።

አልበሙ ምንም እንኳን ” ሰዋሰው መልቲሚዲያ ” በተሰኘው የዘፈን አቅራቢ ድርጅት በኩል ለህዝብ ይደርሳል ተብሎ ቢነገርም በመካከል የቆየው ውል ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ከሁለቱም ወገን ለቀረበ ጥያቄ ስምምነት ባለመኖሩ ወደ ውል ማፍረስ ለማምራት ተገደዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህን አለመግባባት አጀንዳ ያደረጉና ያራገቡ የተለያዩ ገጾች ጉዳዩን ቀጥታ ከፖለቲካ ጋር እንደሚያያዝ ሲገልጹና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ሲያሰራጩ አርቲስቱ ወይም ማናጅመንቱ እውነታውን ለሕዝብ ለማሳውቀ ተነሳሽነት አለመውሰዱ፣ በደል እንደተፈጸመ አድርገው የሚናገሩ ሚዲያዎችም ጠይቀው እውነቱን ለመዘገብ አለመፈለጋቸው ጉዳዩን ወደ ሌላ እንዲያመራ አድርጎታል።

እንደ “ኢትዮፒካሊንክ” የመዝናኛና መረጃ የሬድዮ ፕሮግራም ከሆነ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር የነበረውን ውል በስምምነት እንደፈረሰ ከሁሉም ወገን በተገኘ መረጃ ተረጋግጧል። ስምምነቱ የፈረሰው በአሳታሚውና በአርቲስቱ በኩል ውሉ ውስጥ የተካተቱት አዳዲስ ጉዳዮች ላይ ልዩነት በመፈጠሩ ነው።

ሁለቱ አካላት ከአራት ዓመት በፊት ነበር ስምምነት የተፈራረሙት። ውሉን ለማደስ በነበረ ሂደት ግን አዳዲስ ሃሳቦች በመግባታቸው አለመስማማት ተፈጠረ። ሰዋሰው ፣እልቲ ሚዲያ በአዲሱ ውል ላይ ቀደም ያሉ የቴዴ አፍሮ ዘፈኖችን በሰዋሰው መተግበሪያ ላይ እንዲጫኑና ለዚህም በየዓመቱ የሚከፈል ገንዘብ በቅድመ ክፍያ ለመክፈል ፍላጎቱን ገልጿል። በቴዲ ሃሳቡን ውድቅ በማድረጉ ስምምነት ላይ አልተደረሰም።

በተጨማሪ ከአራት ዓመት በፊት በተፈረመው ውል ላይ ከስልክ ድምጽ ማሳመሪካ CRBT የሚገኝ ገቢ ለሰዋሰው እንዲሰጥ የሚፈቅደውን ስምምነት ማሻሻያ እንዲደረግበት በቴዲ በኩል ጥያቄ ቢቀርብም ከሰዋሰው በኩል ይሁንታ ሊያገኝ አልቻለም። ሁሉንም ወገን ጠይቆ መረጃውን ያሰራጨው ኢትዮፒካሊንክ፣ ከሁለቱም ወገን የተነሱ ልዩነቶቹ ሊጠቡ ባለመቻላቸውና የአልበሙ መውጫ በመድረሱ ሁለቱም ወገኖች ውሉን በስምምነት ለማቋረጥ ከስምምነት ደርሰዋል።

ውሉ ሲፈረም ሰዋሰው ለቴዲ አጠቃላይ 50 ሚሊዮን ብር ለመክፈል ተስማምቶ ነበር። የዚህንም ግማሽ 25 ሚሊዮን ብር በወቅቱ ተከፍሎት ነበር። አልበሙ እንዲወጣ ስምምነት ላይ ተደርሶ የነበረው ከአራት አመት በፊት የነበረ ቢሆንም በተለያዩ አለመግባባቶች ምክንያት ውሉ ሊታደስ አልቻለም። በመጨረሻም ውሉ በሰላማዊ መንገድ መግባባት ፈርሷል።

ከሁለት ሳምንት በፊት ቴዲና አሳታሚው ድርጅት ውይይት አድርገው ውሉን ለማደስ ባለመግባባታችው ቴዲ ቀደም ሲል ወስዶት የነበረውን 25 ሚሊዮን ብር ከአራት አመት የባንክ ወለድ ጋር ታሳቢ ተደርጎ 33 ሚሊዮን ብር ለሰዋሰው መመለሱን የአርቲስቱ የማናጅመንት አባል ናቸው የተባሉ ለኢትዮፒካሊንክ አረጋግጠዋል። ሰዋሰው መልቲሚዲያም አርቲስቱ የወሰደውን ግማሽ ክፍያ 25 ሚሊዮን ብር ከአራት አመት የባንክ ወለድ ጋር ጨምሮ መመለሱን ይፋ አድርጓል። አሳታሚው ” በስራ ሂደት በሚያጋጥሙ ሃሳቦች ምክንያት ውሉ በስምምነት ነው የተፈረሰው ” ብሏል።

ቴዲ አፍሮ ” ኢትዮሪካ ” የተሰኘው አልበሙን ነገ ሀሙስ ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በራሱ ዩትዩብ ቻናል እንዲሁም በተለያዩ የማዳመጫ አማራጮች ለህዝብ ያደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

አልበሙ ቅዳሜ ይወጣል ቢባልም ቀደም ብሎ እንዲወጣ የተወሰነው በቴዲ አፍሮ መሆኑን እንዲሁም የወር ፣ የቀን እና ሰዓቱ ቁጥር 888 ግጥምጥሞሽ አርቲስቱ በምክንያት ያደረገው መሆኑን የማናጅመንት ክፍሉ ለኢትዮፒካሊንክ የመዝናኛና መረጃ ፕሮግራም አአብራርቷል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት ተበተነ

አዲስ ሪፓርተር— በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን አስተናጋጅነት...

ሻዕቢያ ያደራጀው የአመጽ ቀስቃሽ ኮሚቴ ዲያስፖራው ስለፈራ አገር ቤት አመጽ ማስነሳት ቅድሚያው አደረገ

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ፤ ኢህአፓን ማገዝና ብረት ያንሱ ድርጅቶችን...

ኢህአፓ ሌላው የ “ሞዐ ተዋሕዶ” ክንፍ? “ከፈጣሪ የለም” ወደ የብሉይ ምሁር አመራር ሽግግር ሚስጢር

ሰራተኛ ሰፈር ዛሬ ፈርሷል እንጂ ምክር ነው። በየአንዳንዱ ቤት...