“ከመብረቃዊ ጥቃት” መግለጫ በኋላ የሴኮ ቱሬ የመጨረሻ ሳምንታት፤ “አማራ ስለሆንክ አጋለጥከን” የድምጸ ወያኔ ምስክርነት

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በአብዮታዊ ዴሞክራሲ መጽሄትና ጋዜጣ ዝግጅት መሪነት በፕሮፓ ጋንዳ ስራ የተሞረዱት ሴኮ ቱሬ በማህበራዊ ህይወታቸው ባላቸው መስተጋብር በክፉ እንደማይነሱ የሰማችው ዕውነት መሆኑን ማረጋገጧን ትናገራለች። በሚኒስትርነት ማዕረግ እና በጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪነት ያገለገሉት አቶ ሴኮ ለውጡን ተከትሎ ከህወሃት አመራሮች ጋር በመሆን ወደ ትግራይ አቀኑ።

በትግራይ ክልላዊ መንግሥት በጦርነቱ ወቅትና ከዚያ በፊት በትግራይ ክልል የኮሙኒኬሽንና የፖለቲካ ሥራዎችን በማስተናበር ረገድ ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው አቶ ሴኮ ቱሬ፣

ጥቅምት 24 ቀን በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውንና መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ያስቆጣውን የክህደት እርምጃ “መብረቃዊ ጥቃት” የሚለውን ቃል ተጠቅመው ዝርዝር ማብራሪያ ሲሰጡ ሰይፍ እንደተመዘዘባቸው “እኔ ልንገራችሁ” የሚለው የድምጸ ወያኔ ዝግጅት ክፍል አባል ነው።

የሰሜን ዕዝ ላይ የተወሰደውን እርምጃ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ መጠናቀቁን ለመግለጽ “መብረቃዊ” በሚለውን ቃል አሞካሽተውና አወድሰው ያስታወቁት አቶ ሴኮ፣ ይህን ባሉ በሰዓታት ውስጥ የገጠማቸው መከራ ነበር።

“ለጊዜው ስሜን ተወው” ያለው የድምጽ ወያኔ ባልደረባ፣ “ወረዱበት” ሲል ይጀምራል። “አጋለጥከን። አንተ ይህን ያደረከው አማራ ስለሆንክ ነው’ በማለት ሙሉ ቀን ግምገማ ዋሉበት።

የሰሜን ዕዝ ይዞት የነበረውን ዘመናዊ ትጥቅና ከባድ መሣሪያዎች ሙሉ በሙሉ ለመረከብ፣ በሚል የተፈጸመውን ጥቃት አቶ ሴኮ “በመብረቃዊ ጥቃት በአጭር ሰዓት አከናወነው” ባለታቸው የስሜት ንግግር ሆኖ ሳለ “አማራ ስለሆንክ አሳልፈህ ሰጠኸን። ከዳኸን” በሚል አስተቻቸው። ህወሃትን አምነው ወደ ትግራይ አብረው የተግጓዙት አቶ ሴኮ “ተገለሉ” የሚለው ይኸው የድምጸ ወኔ ባልደረባ “ከዛን ቀን ጀምሮ ሴኮ ጥሩ አይሰማውም ነበር። አሟሟቱን ሳስበው ሁለቴ የሞተ ያህል ይሰማኛል” ሲል ስሜቱን ያስረዳል።

የሰሚነ ዕዝ ከተመታ በኋላ ጦርነቱ ሳያይል የድምጽ ወያኔ ባልደረቦች ለድሮን ጥቃት እንዳይጋለጡ በሚል ወደ ተንቤን እንዲሄዱ ተወሰነ። ውሳኔውን የተወሰኑት ያውቃሉ የማያውቁም ነበሩ። ፡መቀለ ዙሪያ የተዘጋጀ ስቱዲኦ እንዳለ ተነገሯቸው። ከዛም በመኪና በለሊት ከያሉበት ተሰባስበው አቅመራ ጊዜያዊ መጠለያ አረፉ።

ጋዜጠኞቹ ፍራሽ ላይ ላፕቶፓቸውን ከፍተው አንዳንድ ነገር እየሰሩ ሳለ፣ ሴኮ ከኃላፊው አበበ ጋር እንደመጡ የሚያስታውሰው የድምጸ ወያኔ ባልደረባ፣ ሴኮ በሙሉ አይኑ ይመለከታቸው እንዳልነበር ይገልጻል። እጅግ ሃዘን በተሰማው ስሜት ወደ ሴቶቹ ጠጋ ብሎ “አዝናለሁ።እኛ ልንጨርሰው የሚገባ ነገር ነበር” በማለት በጸጸት ስሜት መጪው ጊዜ የከበደው መስሎ ይቅርታ ጠየቀ።

“አንተ አማራ ስለሆንክ አጋለጥከን፣ አሳልፈህ ሰጠኸን” በማለት ከተረባረቡበት በኋላ ብዙም ደስተኛ ያልነበረው ሴኮ የዛች ለሌት ወደ ተንቤን አቀና። “መቀለ ዙሪያ ስቱዲዮ ተዘጋጅቶላችኋል” የተባሉት ጋዜተኞችና የተለያዩ ባለሙያዎች በዘጠኝ አውቶቡስ ጉዞ ጀመሩ። መንገዱ አላልቅ ሲላቸው “ወዴት ነው የምንሄደው” ሲሉ ጠየቁ። በስጋትና በጭንቀት ከሰዓታት ጉዞ በኋላ ተንቤን ገቡ። ተንቤን ሲደርሱ በአንድ ሆቴል ውስጥ ጠቅላላ የህወሃት አመራሮችን አገኟቸው። ያለነበሩት ዶክተር ደብርጽዮንና አቶ ጌታቸው ረዳ ብቻ ናቸው።

“ሴኮ ያሳዝነኛል። ልረሳውም አልችልም” የሚለው የድምጸ ወያኔ ባልደረባ፣ አቅመራ ጊዜያዊ መጠለያ ለቀው ሊወጡ አካባቢ በርካታ ሕጻናት በግምት ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 16 የሚሆን የተለያይ ጉዳይ ደርሶባቸው ነበርና በአውቶቡስ ሞልተው መጡ ይላል። “ቆስለዋል። አንዱን ጠጋ ብዬ ምን ሆንክ ስለው እጄ ተቃጠለ አለኝ፤ ከዛ በኋላ ምስማት ስላልቻልኩ ጥዬው ሄድኩ። እነሱን እያሰብኩ ስለነበር ብዙም የመንገዱ መራቅ ትዝ አላለኝም ነበር”

በሆቴሉ ምግብ አዘው እየጠበቁ ሳለ አንድ ቅጥነቱንና ጉዳቱን በቃላት ለማስረዳት የሚያስቸግር፣ የተጎሳቆለ ወጣት ወደ ሆቴሉ ገባ። ምግብ ሲያዝ አልቋል ተባለ። እጅግ ያሳዝን ነበርና “ና ቁጭ በል አሉት” ከጋዜጠኞቹ ጋር ሊመገብ ቁጭ አለ። እጅግ እርቦት ስለነበር ትሪውን አጸዳው። ሁለት ሊትር ውሃ ጠጣ። ሲበላ ምግቡ፣ ሲጠጣ ውሃው በጉሮሮው ሲወርድ የሚታይ ይመስላል። እጡት፣ “ውጊያ አለ፤ ምግብ፣ ውሃ፣ ስንቅ የለም። የነበረውን ግማሹን ሻዕቢያ ወሰደው። ግማሹም ተደፋ፤ አራት ቀኔ እህል ከቀመስኩ” ብሎ አጫወታቸው።

በበነጋታ የድምጽ ወያኔ ኃላፊ ወደ አንድ ጥግ ወስዶ መሬት ላይ ተቀምጦ ሰብሰባቸው። “ከአሁን በኋላ ታጋይ ናቹህ” አላቸው። የስራ መመሪያ ሰጠና ተለያዩ። ከጋዜጠኛነት ወደ ታጋይነት ሽግግር ተደረገ።

ተምቤን እንደሚሄዱ አውቀው አስቀድመው ቤት የተከራዩ፣ ለመጥፋት የትምህርት ማስረጃና ትንሽ ገንዘብ የያዙ፣ ሁሉንም ዓይነት ዝግጅት ያደረጉ እንዳሉ ሁሉ፣ ምንም ሳያቁ ከመቀለ ተጭነው ተንቤይን የተራገፉ በድምሩ አንድ መቶ ሃምሳ የሚዲያው ሰራተኞች ተተራመሱ። የተንቤን ከተማ ነዋሪዎች ሆነው ጦርነት እንዳለ እንኳን የማያውቁ ነበሩ። እዛ ለመቀጠል ያልቻሉ አራት አምስት የሚሆኑ ወደ መቀለ እንዲመለሱ ተፈቀደላቸው። አንዷ የዛሬ የወዲ ወረዳ ባለቤት ናቸው። የተቀሩት እዚያው ሆኑ። በወቅቱ መከላከያ በአየርና በምድር እያጠቃ መቀለ ሊገባ ተቃርቦ ነበር።

የድምጸ ወያኔ ባልደረባ ወደ መቀለ ለሄዱት “መከላከያ ከገባ ይገላችኋላና ራሳችሁን ሸሽጉ” የሚል መልዕክት መተላለፉን በግርምት ያነሳል። የተፈራው አልቀረምና መከላከያ መቀለ ገባ። የተደበቁት መቀለ ያሉት ጋዜጠኞች ቢያዩ ቢያዩ የሚፈልጋቸው አጡ። በሳምንቱ መከላከያ ጥሪ አቀረበ። ከተደበቁበት ወጥተው ሲሄዱ “ቤቱን ልናጸዳው ነውና ዕቃ እንዳይበላሽባችሁ ሰብሰቡ፤ ደሞዝም ውሰዱ” ተባሉ።

ተንቤን የገባው ኃይል አልቻለም። አንድ ማለዳ ላይ ሊያ የምትባለው የወቅቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ ጋዜጠኞችን ሰበሰበችና “ ሴኮና አበበ አብረው ተሰውተዋል። ከዚህ በኋላ የሚያስተባብራችሁ የለም። እግራቹህ ወዳመራችሁ ሂዱ” ብላ አሰናበተች።

“አማራ ስለሆነ ፖለቲካ ሰራብን። አጋለጠን በሚል ከተገመገመበት ቀን ጀምሮ ሰላም የሸሸው ሴኮ መጨረሻው ይህ ሆነ፣ በድሮን ጥቃት ሽሽት ላይ እያሉ ከባልደረባው ጋር አለፈ” የሚለው የድምጸ ወያኔ ባልደረባ፣ ሴኮ ያን ጊዜ ቢያልፍ ኖሮ ብዙ የሚለው ነገር ይኖረው ነበር። በበረሃ ቆይታው ብዙ ማየቱን የሚናገረው ይህ ጋዜጠኛ “ሴኮን መርሳት አልችልም። ምክንያቱም እንሱን አምኖ መጥቶ አማራ ነህ ብለው አገለሉት” ይላል።

በሁለተኛ ደረጃ የሚገርመውና ሊረሳው የማይችለው ጉዳይ፣ በርሃ ሄደው ውስኪ ይጋዝላቸው ስለነበሩት የህውሃት አለቆች ጉዳይ ነው። ተንቤን ድረስ ውሲክ እያስመጡ ይጠጡ ነበር። ሌላም ሌላም ቺርስ!!

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related