ገዱ እንዳርጋቸው ጠ.ሚ ጃዋር ምክትል ሆነው ተመደቡ፤ መከላከያ እንዲፈርስና በዝግ ተወስኗል

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በስደት አሜሪካን አገር የሚኖሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አዲስ ለሚቋቋመው መንግስት ጠ.ሚኒስትር፣ አቶ ጃዋር መሐመድ ምክትላቸው እንዲሆኑ ምደባ መካሄዱ ተሰማ። በስምምነቱ ውስጥ ዳግም የተገነባው የአገር መከላከያ እንዲፈርስ ይደረጋል። የክልሎች አወቃቀርና ወሰን ወደ ቀድሞው መልኩ እንዲመለስ ይደረጋል።

ይህ የሚሆነው ቅዳሜ በአየር ላይ፣ ከአምንት በኋል በሎንዶንና አሜሪካ መሬት አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ስለፍ ከተደረገ በኋላ አገር ቤት ባለው መዋቅር ምርጫ እንዳይደረግ ተደርጎ ያለው መንግስት ሲፈርስ እንደሆነ ታውቋል። ዕቅዱና የሽግግር ሰነዱ ከተዘጋጀ መቆየቱን ያመለከተው የዋሽንግቶን ተባባሪያችን እንዳለው ምደባው አሁን ይፋ የሆነው በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሲወድቅ ወዲያውኑ ስልጣን የሚረከብ ለማዘጋጀት ታስቦ ነው። ይህ በሚስጢር የተያዘ ምደባ ከወዲሁ ልዩነት ማስነሳቱም ተሰምቷል።

የአመጽ አመቻች ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ “ይህ መንግስት ሲወድቅ ምን እንደሚደረግ የተዘጋጀ ዕቅድ አለ ወይ? አካሄዱ ሸፍጥ ይመስላል። የድርጅት ቅርጽ አይታይም። ዝም ብሎ የመግበስበስ ዓይነት ነው” በማለት ከኢትዮጵያን አድን ዶክተር ሚኒሊክ ላቀረቡት ጥያቄ አቶ ነዓምን ዘለቀ “እመነኝ ምንም ሸፍጥ የለም። ይስህ ጥምረት፣ ህብረት ወይም ድርጅት ሳይሆን ፕሮጀክ ያገናኛቸው ሰዎች የተገናኙበት ነው። ወደፊት ስንተዋወቅ ወደ ሌላ ደረጃ እናድጋለን” በማለት መልሰው እንደነበር የስብሰባውን ቅጂ በማያያዝ መዘገባችን አይዘነጋም። ዶክተር ሚኒሊክ ይህን በመጠየቃቸው አሁን እየተካሄደ ባለው የአመጽ ቅሰቀሳ ላይ ሳይመደቡ ቀርተዋል።

ስብሰቡን ከጀርባ የሚነዳው ሻዕቢያ የሚቆታጠረው የሽግግር ሰነድ ያተዘጋጀ መሆኑን አዲስ ሪፖርተር ከወራት በፊት መዘገቧ አይዘነጋም። የሽግግር ሰነዱ ቀደም ተብሎ እነ አቶ ስብሃት ነጋ እና ጃዋር መሐመድ መክረው ያዘጋጁት እንደነበር የዝግጅቱ ተባባሪ የሆኑትን በማነጋገር የዘገብነው ዘገባ ላይ ጃዋር በጻፈው አልጸጸትም መጽሐፍ ላይ እንዳጣጣለው እንዳልሆነም ተመልክቶ ነበር።

በሰነዱ መሰረት በተደረገ ምደባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሽግግሩ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አቶ ጃዋር መሐመድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር መደረጋቸውን የዲሲ ተባባሪያችን በዜናው አኩርፈዋል የተባሉትን ጠቅሶ ዘግቧል። በአብሮነትና በአመጽ አመቻች የቴክኒክ ኮሚቴ ውስጥ ያሉ ዕውቀቱ ሳይኖራቸው በተሰራው የሽግግር ምደባ አቶ ልደቱ አያሌው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነትን ሲይዙ አቶ ነዓምን ዘለቀ የአገር መከላከያን ለማፍረስ በተደራጀው ኃይል ውስጥ ከፍተኛ ኃላፊነት እንደተሰጣቸው ታውቋል። አቶ ነዓምን በይፋ የሻዕቢያ ወኪል ሆነው እንደሚሰሩ በቴክኒክ ኮሚቴው ስብሰባ ላይ እሳቸው ባሉበት የትህነግ ተወካይ የሆኑት መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በሽግግር ሰነዱ እነ አቶ ገዱና ጃዋር ከሚመደቡላቸው ጋር ሆነው የሚያስቀጥሉት የመጀመሪያውን ህገ መንግስትና የክልል ወሰኖችን ባለመሸራረፍ ነው። ሰነዱ ክህገ መንግስቱ የተቀዳ በመሆኑ ወልቃይትና ራያን ወደ ትግራይ ክልል ይመልሳል። ይህን የሚያስፈጽሙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቀደም ሲል የአማራ ክልል ናቸው የሚባሉትን አወዛጋቢ አካባቢዎች አሳልፈው በመስጠት በአማራ ክልል ፖለቲካ ታሪክ የሚከሰሱ መሆናቸው ይታወቃል።

ሌላው በሽግግሩ ሰነድ ውስጥ ግዙፍ ስፍራ ያለው የአግወር መከላከያን የመበተን መርሃ ግብር ነው። የአገር መከላከያ ሲበተን ወዲያውኑ የሚተካው የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀ ሲሆን በዚህ የቴክኒክ ኮሚቴ ውስጥ ሻዕቢያ፣ ወያኔ፣ እንዲሁንም ትጥቅ ያነሱ ተካተዋል። በሰነዱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና ባህር ኃይልም እንደሚፈርሱ በግልጽ ተቀምጧል። በቴክኒክ ኮሚቴ ውስጥ ጃል መሮ አሉበት።

ሰነዱን ቀደም ብለው ያዩት ለዲሲ ተባባሪያችን እንዳሉት፣ ምርጫ እንዳይደረግ የተጀመረው ዘመቻ መንግስትን አፍርሶ ይህን ኃይል ለማምጣት ያሰበ ነው። ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተሰማ ያለው የአመጽ ጥሪ ሲሳካ አዲስ አበባ ያሉ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ፕሬዚዳንት እንደሚደረጉም ታውቋል። ዘጋቢያችን ስማቸውን ሳይገልጽ እንዳለው እኚህ ሰው የኦሮሞን ሕዝብ ቀልብ ለመሳብ ተብለው የተመረጡ ናቸው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related