ህወሃት ከመንግስት ጋር የግንኙነት ገመዱ መበጠሱን አስታወቀ፤ “በሱዳንና በኤርትራ ገንዘብ እንጠቀማለን” – የትግራይ የለውጥ ኋይሎችና ወታደራዊ ክንፉ በይፋ ሊዋሃድ ነው

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና – በትግራይ ያለው የፖለቲካ አውድ ጡዘቱ አይሏል። ከኤርትራ ጋር ጽምዶ ከፈጠረ በኋላ የፕሪቶሪያው ስምምነት መፍረሱን ደጋግሞ ሲያስታውቅ የነበረው ህወሃት የትግራይን ጊዜያዊ አስተዳደር ለማፍርስ ቀጠሮ ከያዘ በኋላ እንዳለው፣ ዛሬ “ከፌደራል መንግሥት ጋር ያለው የግንኙነት ገመድ ተበጥሷል” ማለቱ ተሰምቷል። በሌላ ወገን ደግሞ የትግራይ የለውጥ ኃይሎች ስብስብ እና የትግራይ ሰላም ኃይሎች በሚል የሚታወቀው ወታደራዊ ክንፍ በይፋ ህብረታቸውን ለማወጅ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።

የፌደራል መንግስቱ አንድ ዓመት ሥልጣን ያራዘሙላቸውን የጄነራል ታደሰን ወረደን ጊዜያዊ አስተዳደር እየፈረሰ መሆኑን ህወሃት ይፋ ማድረግ ከጀመረ ቢሰነብትም ዛሬ በይፋ ለቢቢሲ ይህን አስታውቋል፡፡ የህወሓት ቃል አቀባይ ሚካኤል አስገዶም እንዳሉት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርም እየፈረሰ በመሆኑ ህወሓት ከፌደራል መንግሥት ጋር ያለው “የግንኙነት ገመድ ተበጥሷል በመበጠሱ ከአራት ኪሎ የሚሰጥ መመሪያ አይቀበልም።

ለዚሁም ውሳኔ ማስደገፊያ ያደረጉት የፕሪቶሪያ ስምምነት ነው። ቃል አቀባዩ “የፕሪቶሪያው ስምምነት ስለፈረሰ ጊዜያዊ አስተዳደሩም ፈርሷል” በማለት በግልጽ ከፌደራል መንግሥት ጋር ያለው የግንኙነት መበጠሱን አስታውቀዋል። አክለውም ሌተናል ጀነራል ታደሰ ሥልጣናቸውን በሰላም ማስረከብ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል። ይህን ካላደረጉ ስህተት እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል።

ምንም እንኳን የሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደን አቋም ወጥነት የሚጠራጠሩ ቢኖሩም በኃይል ስልጣን ለመውሰድ የሚደረግ ሙከራ ጦርነት እንደሚያስነሳ አመልክተዋል። “እናዳታደርጉት” ሲሉም ጥሪ አስተላልፈዋል።

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሚያዝያ 11/2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ከስድስት ዓመት በፊት ክልሉ ውስጥ በተደረገ ምርጫ የተመረጠው የትግራይ መንግሥት ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ መወሰኑን ይፋ አድርጎ ነበር።

ዛሬ ይፋ በሆነው የህወሃት አቋም መሰረት “ከፌደራል መንግስት ጋር ያለው ግንኙነት ተበጥሷል ሲባል ምን ማለት ነው” በሚል ቢቢሲ ላቀርበው ጥያቄ፣ ቃል አቀባዩ፤ “ከፌደራል መንግሥት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት እንዴት ይሆናል የሚለው በቀጣይ የምናየው ይሆናል። እስካሁን ባለው ግንኙነት ግን ጊዜያዊ አስተደዳር እየፈረሰ ስለሆን የነበረን ገመድ ተበጥሷል የሚል ሀሳብ ነው የምንወስደው” ሲሉ ጥቅል መልስ ሰጥተዋል።

ህወሃት ይህን ይፋ ከማድረጉ በፊት የኦንላይን የገንዘብ ክፍያዎችን መከለከሉ የሚታወስ ነው። አቶ ፍናን አብርሃ የተባሉት የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ከህዝብ ጋር በተደረገ የወይይት መድረክ፣ “እጃችን ላይ ያለውንና የተገኘውን ሁሉ  ይዘን ለሉዓላዊነታችን ለመታገል ወስነናል።የመጨረሻው ግባችንስ ምንድነው? ለሚለው ህወሓት አክሱም ውስጥ ባደረገው ስብሰባ ላይ ባሳለፈው ውሳኔ የቀደመ አቋሙን ቀይሯል።አቋሙንም ግልፅ አድርጓል።የህወሓት የአሁኑ አቋም የራስን እድል በራስ የመወሰን መብታችንን ማረጋገጥ የሚል ሆኗል” ሲሉ ተድምጠዋል።

ፎቶ የትግራይ ሰላ ኃይሎች በከፊል

“በፊት በመከባበር ላይ የተመሠረተ አንድነት ብለን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበርን ይታወቃል።አሁን ያ አቋም  ተቀይሯል።የራሳችንን እድል በራሳችን የመወሰን መብታችንን ማረጋገጥ አለብን ብለናል። በዴፋክቶ ነው ? ወይስ የነፃ አገርነት ጥያቄ  ነው ? ወይስ በሌላ? [ኮንፌዴሬሽን] የሚለው ነገር ቆይቶ የሚታይ ይሆናል” ሲሉም አክለው ተናግረዋል። አቶ ፍናን አብርሃ በዚሁ መድረክ “የኤርትራ ናቅፋና የሱዳን ፓውንድ የትግራይ የመገበያያ ገንዘቦች ይሆናሉ” ማለታቸውን ከድምጸ ወያኔ ባልደረቦች ለመስማት ትችሏል።

አቶ ፍናን አብርሃ ከድምፅ ወያኔ ጋዜጠኞች ጋር በህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ ዙሪያ ውይይት ማብቂያ ላይ የህወሓት  ከተወያዮቹ ለተሰነዘሩ ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህ ጊዜ  “የፕሪቶሪያው የስምምነት ውል ፈርሷል።በቅርቡ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል።ብልፅግናን ሳንደመስስ አንተኛም።የኤርትራን ናቅፋና የሱዳኑን ፖውንድ ለግብይት የምንጠቀምባቸው ገንዘቦች ይሆናሉ” በማለት በድጋሚ ማረጋገጫ ሰጠዋል።

የባይቶና ምክትል ሊቀመንበርና የትግራይ ለውጥ ኃይሎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ በርኸ ለአዲስ ሪፖርተር ከቀናት በፊት ብሌላ ጉዳይ ለተጠየቁት ሲመልሱ፣ በ2012 የመረጠ የተባለው ምክርቤት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ውድቅ ሆኗል። ህወሃት በአደባባይ ዓለም እየሰማ ምርጫው ስህተት እንደነበር አምኖ ተቀብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ከ2012 በኋላ ስድስት ዓመት በመቆጠሩ የምክር ቤቱ የህይወት ዘመን አብቅቷል። አቶ ዮሴፍ እንደሚሉት በወቅቱ ተመርጦ የነበረው ምክር ቤት በሞት፣ በስደትና በፖለቲካ አመለካከት ተመናምኖ ማናቸውንም ውሳኔ ለመወሰን የሚያስችል የድምጽ መጠን የለውም።

“በበርካታ መመዘኛዎች ዳግም ወደ ስራ ሊመለስ የማይችል ምክር ቤት ይመለስ ማለት የተለመደው ትግራይን በጦርነት የማቃጠል አባዜ ነው” ሲሉ አቶ ዮሴፍ ገልጸዋል። በሁኔታውም እጅግ ማዘናቸውን፣ በተለይም የትግራይ ሕዝብ በዚህ ደረጃ እንዲሰቃይ የሚፈርዱበት የህወሃት አመራሮች አስተሳሰብ ሊገባቸው እንደማይችል አመልክተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባይቶና፣ ስምረት፣አረና፣ትንሳዔ ሰብአእንደርታ፣ ቃንጪ ሃቂ፣ ታዋቂ ሰዎችና ድርጅቶች ከውጭና አገር ቤት የተካተቱበት የትግራይ ለውጥ ፈላጊ ኃይሎች ሃራ መሬት ካሉት የሰማ ኃይሎች ጋር በይፋ ጥምረታቸውን ይፋ ሊያደርጉ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተስምቷል።

ለሰላም ኃይሎች ስብስብ ቅርበት ያላቸው ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት የጥምረቱ ስራ አልቋል። በርካታ የአርሚ ሰራዊት አባላት ከቀድሞው በበለጠ እየተቀላቀሉት ያለው የትግራይ ሰላም ኃይሎች ወታደራዊ ክንፍ ከለውጥ ፈላጊዎች ንቅናቄ ጋር መዋሃድ ትልቅ መልዕክት እንዳለው የዜናው ምንጮች አስታውቀዋል።

ትግራይን የተቆጣጠራት የህወሃት ኃይል የአንድ ቤተሰብና የደም ሃረግ የተመዘዘ በመሆኑ በትግራይ ህዝብ ጀርባውን እንደሰጠው ያስታወቁት የመረጃው ባለቤቶች “በትግራ ለውጥ በድጅ ነው” ብለዋል።

ከትግራይ ኃይሎች በመለየት ከአፋር ክልል ጋር በሚዋሰን አካባቢ የራሳቸውን ሠራዊት እየገነቡ መሆናቸውን የሚናገሩት ብርጋዴር ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ) “ከፓርቲ [ህወሓት] ነጻ የሆነ ኃይል” ለመፍጠር ወደ ነጻ መሬት መውረዳቸውን መናገራቸው ይታወሳል። በተለያዩ ጊዜያት በሰጡት መግለጫ በያዝነው ዓመት ህወሃትን እንደሚያስወግዱ አመልክተዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአሜሪካ ዲፕሎማት እና ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ህውሃትን ማዕቀብን እንደሚጣል አስጠነቀቁ

ወደ መቀለ የመጣው የአሜሪካ ልኡክ ከፍተኛ ወታደራዊ ኃላፊዎች የተገኙበትና፣...

“ከመብረቃዊ ጥቃት” መግለጫ በኋላ የሴኮ ቱሬ የመጨረሻ ሳምንታት፤ “አማራ ስለሆንክ አጋለጥከን” የድምጸ ወያኔ ምስክርነት

አዲስ ሪፖርተር - በአብዮታዊ ዴሞክራሲ መጽሄትና ጋዜጣ ዝግጅት መሪነት...

“ሻዕቢያ ገድሎናል፣ አርዶናል፣ወግቶናል ዓለም ዓቀፍ ፍትህ እንፈልጋለን፣ አሁን ግን ጊዜው አይደለም”

“እርግጥ አርደውናል፣ ገለውናል፣ ወግተውናል፣እውነት ነው፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ፣ ከዓለም...