በአሜሪካ በህወሃት የሚደገፉ ሚዲያዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጥያቄ ቀረበ፤ “አምባሳደሩ ይገደሉ” ከሚሉት ጀምሮ የተደራጀ መረጃ እየቀረበ ነው

Date:

ተቀማጭነታቸውን አሜሪካ ያደረጉ በህወሃት የሚደገፍፉ ሚዲያዎች ላይ ጥብቅ ምርመራ እንዲካሄድ ጥያቄ መቀረቡ ተሰማ። ቀደም ሲል የህወሃት ደጋፊ የነበሩና አሁን ላይ የድርጅቱን አካሄድ የሚነቅፉ “በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ማሲንጋ ሳይቀር ይገደሉ” ከሚልው ጀምሮ ከሽብር ቡድኖች ጋር በመሆን መረጃ የሚያሰራጩ ሚዲያዎች ከነሙሉ መረጃው ለአዲስ አበባ ኤምባሲ እና አሜሪካ ለሚመለከታቸው ተቋማት መቅረቡን በይፋ አስታውቀዋል።

ሰላም ወዳድ የትግራይ ወጣቶች የተባሉ የሲቪክ ማህበረሰብ አካላት በአሜሪካ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የተወሰኑ የትግራይ ሚዲያ ተቋማት ላይ ጥልቅ ምርመራ እንዲደረግና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለክቡር ማርኮ ሩቢዮ ይፋዊ የቅሬታ ደብዳቤ አቅርበዋል። ቅሬታቸውን ያቀረቡት አሜሪካ በህወሃት ከፍተኛ አመራሮችና ተባባሪዎቻቸው ባለቻቸው ላይ የቪዛ ዕገዳ ማድረጓን ተከትሎ ነው።

በደብዳቤው ላይ እንደተመለከተው፣ ሰኔ 18 ቀን 2026 ዓ.ም በወጣው መግለጫ መሠረት፣ ወጣቶቹ የአሜሪካ መንግስት በህወሃት (TPLF) መሪዎች ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ ውሳኔ በበጎ ጎኑ የሚመለከቱት ቢሆንም፣ ይህ እርምጃ ብቻውን ግን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል። በመሆኑም አሜሪካ እርምጃዋን እንድታጠናክር ጠይቀዋል።

በተለይም በአሜሪካ ሀገር መቀመጫቸውን አድርገው የሚንቀሳቀሱት እንደ ዛራ ሚዲያ ኔትወርክ (Zara Media Network)፣ ኮራይዘን (Horizon)እና ትግራይ ፕሬስ (Tigray Press) የተባሉ የሜዲያ ተቋማት ለፅንፈኛ የህወሃት አመራሮች ልሳን በመሆን እያገለገሉ መሆናቸውን ወጣቶቹ በክሳቸው ስማቸውን ጠቅሰው፣ የሚያሰራጩትን የጦርነት ቅስቀሳ ዘርዝረው አቅርበዋል።

“እነዚህ ተቋማት ህዝብን ለሁከትና ለብጥብጥ በመቀስቀስ እንዲሁም የትግራይ ወጣቶች በድጋሚ ወደ ጦርነት እንዲገቡ ግፊት እያደረጉ ነው” በማለት በጽኑ ተቃውመዋል። ሚዲያዎቹ በተለያዩ ወቅቶች አቋማቸውን ቢቀያይሩም ዋና ዓላማቸው አሁን ትግራይን ወደ ዳግም ጦርነት እየመራ ያለውን የህወሃት ክፍል ማንገስ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል።

በመሆኑም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በእነዚህ ተቋማትና ከጀርባቸው ባሉ ግለሰቦች ላይ አፋጣኝና ሁሉን አቀፍ ምርመራ በማካሄድ፣ በሀገሪቱ ህግ መሠረት አስተማሪ የሆነ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድባቸው ወጣቶቹ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የአሜሪካ የወንጀል ሕግ (18 U.S. Code § 2339B) በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር “የውጭ የሽብር ድርጅት” (FTO) ተብለው በተፈረጁ ቡድኖች ላይ በጣም ጥብቅ አቋም እንዳለው የሚናገሩ ወጣቶቹ የጠቀሷቸው ሚዲያዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ተባባሪ የሆኑበት የጽምዶ ህብረት ከሽብር ወንጀል ጋር በተያያዙ ቅስቀሳዎች ላይ ተሳታፊ ለመሆናቸው በርካታ ማስረጃዎች አሉ።

ራሳቸውን ከአልሸባብ የየመን ሁቲ ጋር እና በተለምዶ ሽብርተኞችን ከሚያደራጁና ከሚደግፉ አገራት ጋር በግልጽ ግንኙነት እንዳላቸው ከሚናገሩ ቡድኖች ጋር በቀጥታ ተገናኝተው ቅስቀሳ ሲሰሩ የነበሩ ሚዲያዎ በአሜሪካ ህግ መሰረት ሊመረመሩ እንደሚችሉ ህጉ ሊፈቅድ እንደሚችል የሚናገሩ “ህወሃትና ከህወሃት ጋር ግንባር የፈጠሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች በገሃድ በአሜሪካ መንግስት በሽብር ተፈረጀው የሱዳን መንግስት ጋር ጦር ከመስጠት ጀምሮ አብረው እየሰሩ ነው። ሚዲያዎቹም ይህንን እንደ አንድ ትልቅ ስኬት አድርገው በየቀኑ ሲቀሰቅሱ ነበር። ይህ አካሄድ ሽብርን መደገፍ ነው” ባይ ናቸው።

አንድ በአሜሪካ የሚገኝ ሚዲያ ወይም የሚዲያ ባለቤት የሽብር ቡድን ተብሎ ለተፈረጀ ቡድን ወይም ድርጅት ወይም አገር የአየር ሰዓት በመስጠት፣ የእነሱን የፕሮፓጋንዳ ስራዎች በንቃት በማሰራጨት፣ ስልታዊ የኮሙኒኬሽን ድጋፍ (Expert advice or assistance) በመስጠት ከተሳተፈ ይህ እንደ “ቁሳዊ ድጋፍ” (Material Support) ስለሚቆጠርበት ያስጠይቀዋል። ይህ የወንጀል ክስ ሲረጋገጥ እስከ 20 ዓመት ጽኑ እስራት፣ በጥቃቱ ምክንያት የሰው ሕይወት ከጠፋ ደግሞ እስከ ዕድሜ ልክ እስራት ሊያሰቅጣ የሚችል ከባድ ወንጀል መሆኑንም ስለ ህጉ የሚያውቁ ጥቅል መረጃ ሰጥተዋል።

ቀደም ሲል “የትግራይ ህዝብ ጦርነት ባህሉ ነው” በማለት ወደ ጦርነት ሲነዱት የነበሩት የትግራይ አክቲቪስቶች አሁን ላይ አቋማችውን ቀይረው ለጊዜው ስማቸውን ያልጠቀሷቸውን ሚዲያዎች ሲያሰራጯቸው የነበረውን መረጃ በማሰባሰብ ለአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲና አሜሪካ ባሉበት አገር ለሚመለካታቸው አደረጃጀቶች መረጃ ማቅረባቸውን እያመለከቱ ነው። አሉላ በአውራምባ ሚዲያ ላይ ይህንኑ ሲያስታውቅ እንዳለው በርካታ ወነጀሎችን የፈጸሙ “አምባሳደር ማሲንጋ ይገደል” ያሉት ሳይቀሩ መረጃ ቀርቦባቸዋል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related