ህወሃት አሜሪካን “ባለወላታችን” ብሎ የቪዛ ዕገዳውን “ወገንተኛ” ሲል ተቃወመ

Date:


አዲስ ሪፖርተር ዜና – ‎”ወገንተኛ እገዳ ሰላም ማምጣት ኣይችልም” ሲል ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የቪዛ እግዱን ተቃውሞ ደብዳቤ አሰራጨ። በደብዳቤው የፕሪቶሪያውን ውል አፍርሶ ለምን ስልጣን በኃይል እንደያዘ፣ ታጣቂዎችን ለምን እንደሚያደራጅ፣ ከኤርትራና ሱዳን ጋር ህገምንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ ለምን የጋራ ወታደራዊ ጥምረት “ጽምዶ” እንደመሰረተ፣ ለምን አሜሪካ በሽብር ከፈረጀችው የሱዳን መንግስት ጋር አብሮ እንደሚሰራና የትግራይ ወጣቶችን ለሱዳን እንዲዋጉ እንደሚልክ፣ ከወራት በፊት ለምን የፕሪቶሪያው ስምምነት መፍረሱን በገሃድ እንዳወጀ፣ የግዳጅ አፈሳና አፋኝ ህግ ያወጣበትንና አሜሪካ ዕግዱን ለመጣል በዋናነት ያነሳቸውን ምክንያት አንድ በአንድ ጠቅሶ በደብዳቤው አላሰፈረም። ድርጅቱ በይፋዊ ገጹ ያሰራጨውን ደብዳቤ ትርጉም ከስር ያንብቡ።

‎አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ያላት የሰላም አቋም እና የፕሪቶርያ ዘላቂ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲፈረም የነበራት መሪ ተዋናይነት እና ለትግራይ ህዝብ ሰላም እንዲያገኝ ያሳየቺው ተነሳሽነት እንደሚያደንቅ ያመለከተው የህወሓት መግለጫ፤ በፌደራል መንግስት ተደጋጋሚ የተጣሰው የፕሪቶርያው ስምምነት ሳይታይ ህወሓት ላይ የጉዞ እገዳ ማኖሩ ፍትሓዊነት የጎደለውና ኣሳሳቢ መሆኑን ባወጣው በአቋም መግለጫው አመላክቷል፡፡
ጥፋተኛው አካል ሳይጠየቅ በህወሓት ላይ ብቻ ያነጣጠረ እገዳ ፍትሓዊነት የጎደለው መሆኑን ያመለከተው መግለጫው ፤በእንደዚህ ዓይነት አድላዊነት አቋም ሰላም ማስፈን እንደማይቻል አመልክቷል፡፡

‎እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ህዳር 2 ቀን 2022 የተፈረመው የፕሪቶርያው ዘላቂ የተኩስ ማቆም ስምምነት፤ በሁለቱም ተፈራራሚ አካላት እንዲፈፀሙ በግልፅ ከተቀመጡ ነጥቦች መካከል፤ ህገመንግስታዊ ስርዓት ወደ ነበረበት መመለስ፣ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ወገኖች ወደቦታቸው መመለስ፣ ከመከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ታጣቂዎች ከትግራይ ግዛቶች ማስወጣት፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱና የህወሓት ህጋዊ እውቅና እንዲሁም ፖለቲካዊ ቁመና መመለስ መሆኑ ያስታወሰው መግለጫው፤ እነዚህ ስምምነቶች በፌደራል መንግስት ምክንያት ያልተተገበሩ መሆናቸውን ህወሓት በመግለጫው ያስረዳል፡፡

‎የትግራይ ህዝብ ሰላም ወዳድና በአስቸኳይ ወደ ቄዬው እንዲመለስ እዲሁም የመልሶ ግንባታ ስራዎች ተሰርቶለት ወደ መደበኛ ህይወቱ እንዲመለስ ያለው ፍላጎት ተግባራዊ እንዲሆን የፕሪቶርያ ስምምነት ተግባራዊነት በጉጉት ሲጠባበቅ መቆየቱን ያመላከተው መግለጫው፤ ስምምነቱ ከመተግበር ይልቅ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ፍትሃዊነት የጎደለው እና አለመተማመን እንዲሰፍን ምክንያት ሆኖ መቆየቱ በፁሑፉ ተመላክቷል፡፡

‎ስምምነቱ ሶስት ዓመታት ያሳለፈ ቢሆንም፤ ወሳኝ የስምምነት ነጥቦቹ ሳይተገበሩ መቆየታቸውን ያመለከተው መግለጫው፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተጋሩ ወደ ቂያቸው መመለስ እንዳልቻሉ፣ የተጠያቂነት ሂደት እንዳልተቋቋመና የኢትዮጵያ መንግስት በቅርብ ከተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ውጪ እንድትሆን መደረጉን ህወሓት በመግለጫው ኣመላክቷል፡፡

‎የሰራተኞች ደመወዝ፣ ነዳጅ፣ የባንክ አገልግሎት እና ሰብአዊ እርዳታዎችን የመሳሰሉ መሰረታዊ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ መንግስተ በኩል እገዳ ተደርጎባቸው እንደሚገኝ እንዲሁም በመጠሊያዎች የሚገኙ ወገኖች በከፋ የኖሮ ሁኔታ ይገኛሉ ያለው መግለጫው፤ በረሃብ እየሞቱና መከላከል በሚቻሉ በታዎች እየተጠቁ መሆኑ ያስረዳል፡፡

‎የትግራይን ህዝብ አስርቦ ለማጥፋት በፖሊሲ ደረጃ እየሰራ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት አረሜናዊ ተግባር ሆኖ እየቀጠለ እንደሚገኝ ያስረዳው የህወሓት መግለጫ፣ የትግራይ ህዝብ ስቃይ ከህወሓት ጋር አያይዞ መግለፅ ተገቢነት የጎደለው መሆኑን አስረድቷል፡፡
‎በየመጠልያው የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ተፈናዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ ዋነኛ ተጠያቂ ለማወቅ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶች፣ እንደሁም በፕሪቶርያ ስምምነቶች የተቀመጡ የሰብኣዊ አገልግሎት ጉዳዮች እንዳይፈፀሙ በፖሊሲ ደረጃ ከልክሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት ማወቅ በቂ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ዳሰሳ በማከናወን እውነታው መረዳት እንደሚቻል ያስረዳል፡፡

‎የፌደራል መንግስት ወሳኝ የሚባሉ የፕሪቶርያው ዘላቂ ተኩስ ማቆም ስምምነቶች እንዳይፈፀሙ አንቆ መያዙን ለመረዳት የሚያወጣቸው የተለያዩ ደብዳቤዎችና በመሬት ላይ የሚታዩ ተግባሮቹ መመልከት በቂ ማስረጃዎች መሆናቸው ያመለከተው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መግለጫ፤ በትግራይ ህዝብ ላይ የተጣሉ ክልከላዎች አጠቃላይ ህዝቡ ከመጉዳታቸው በተጨማሪ በወታደራዊ ማስፈራራትና በተደጋጋሚ በፈፀማቸው የድሮን ድብደባዎች እንዲሁም ትግራይን ለማድቀቅ በተከተለው የፖለቲካ ተፅኖ የትግራይ ህዝብ በፌደራል ስርዓቱ ያለ ውክልና እንዲቀር ማድረጉን አስረድቷል፡፡

‎ስምምነቱ እንዳይተገበር ሙሉ በሙሉ የዘጋ አከል አቅልሎ በማየት፤ ችግሩ ባልፈጠረ ተደራዳሪ ላይ ተጠያቂ በማድረግ የሰላም ሂደት ለመተግበር ያለው ዕድል አናሳ መሆኑ ያመለከተው መግለጫው፤ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሚችለው ገለልተኛ፣ መርህን በመጠበቀና የጋራ ተጠያቂነት ሲኖር መሆኑን አስረድቷል፡፡

‎የትግራይ ህዝብ ሰላም ወዳድ በመሆኑ፤ ህወሓት በሰላም ጉዳይ ያለው አቋም የፀና በመሆኑ ያብራራው መግለጨው፤ የፕሪቶርያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር የፌደራል መንግስት ለስምምነቱ ተገዥ በመሆን የሰራተኞች ደመወዝ፣ የባንክ አገልግሎት፣ የነዳጅ አቅርቦት እና የሰብኣዊ ጉዳይ ተደራሽነት ማረጋገጥ ኣለበት ብሏል፡፡

‎በትግራይ ህገመንግስታዊ ግዛት የሚገኙ ወራሪዎች ሙሉ በሙሉ በማስወጣት፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደቀያቸው ለመመለስ የሚያስችል የጊዜ ሰሌዳ በማኖር እንዲሁም የህወሓት ህጋዊነት ለመመለስ የፕሪቶርያው ስምምነት መተግበር ይኖርበታል ያለው የህወሓት በመግለጫ፤ በትግራይ ህዝብ ስቃይና መከራ የተሳተፉ አካላት ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የፌደራል መንግስት ቁርጠኝነት ማሳየት ይኖርበታል ብሏል፡፡

‎የትግራይ ህዝብ ሰላም፣ ፍትሕ፣ እንድሁም በሁሉም አካላት እንደየጥፋታቸው የሚዳኙበት ሁለንተናዊ ዘላቂ የሰላም ሂደት እንዲሰፍን የትግራይ ህዝብ ፍላጎት መሆኑን ህወሓት በመግለጫው ላይ ኣረጋግጧል፡፡

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related