ከእስራኤል ትልቁ የስለላ መረብ የተስወረው 911 ቀናት የሆኑት ዕግታ፤ ሃይማኖት ካሳን ማን ሰወራት?

Date:

አዲስ ሪፖርተር፣ አዲስ አበባ — የአንድ ህፃን ልጅ በድንገት መሰወር የአንድ ቤተሰብ የግል ህመም ብቻ ሳይሆን፣ የጠቅላላው ማህበረሰብ የሕሊና ቁስል እና የአንድ አገር የደህንነትና የመፍትሔ አሰጣጥ ስርዓት ትልቅ ፈተና መሆኑን ኢየሩሳሌም ፖስት ይናገራል። ለዚህ ማሳሰቢያ አዘል ማብራሪያው መነሻዋ ደግሞ ሃይማኖት ካሳ ናት። ስለላውና ጥበቃው በበረታባት እስራኤል ሃይማኖትን የሰወራት ማን ነው?

በእስራኤል ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ሰፌድ ከተማ በሚገኘው የጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በድንገት የተሰወረችው የዘጠኝ ዓመቷ ህፃን ሃይማኖት ካሳው ጉዳይ፣ ከቀናት ወደ ወራት፣ ከወራትም ወደ ዓመታት ተሻግሮ ዛሬ ላይ 911 ቀናትን አስቆጥሯል።

ይህ ረጅም የጭንቀት፣ የዕለት ተዕለት ሰቆቃ እና የተስፋ መቁረጥ ጊዜ የህፃኗን ወላጆች ወደ ከባድና ታሪካዊ ውሳኔ ያደገረሳቸው ሲሆን፣ የምርመራውን ሂደት ከአካባቢው ፖሊስ ቁጥጥር አውጥቶ የአገሪቱ ከፍተኛ የውስጥ ደህንነትና የስለላ ተቋም የሆነው ሺን ቤት  እንዲረከበው የሚጠይቅ አዲስና አጣዳፊ አቅጣጫ ይዟል።

የሃይማኖት ካሳው አሳዛኝ ታሪክ የጀመረው እ.ኤ.አ. የካቲት 25 ቀን 2024 ምሽት ላይ ነበር። ህፃን ሃይማኖት ከቤተሰቦቿ ጋር ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ከተጓዘች ጥቂት ዓመታት ብቻ የተቆጠሩ ሲሆን፣ በወቅቱ በሰፌድ ከተማ በሚገኘው ከአይሁድ ኤጀንሲ ጊዜያዊ የመቀበያ ጣቢያ ውስጥ ይኖሩ ነበር።

በዚያች ምሽት ከጓደኞቿ ጋር ሆና ለአካባቢው ማዘጋጃ ቤት ምርጫ የምረጡኝ ወረቀቶችን ስታደል እንደነበር የደህንነት ካሜራዎች ያሳያሉ። ነገር ግን ከዚያች ሰዓት በኋላ ህፃኗ በድንገት ደብዛዋ ጠፋ።

የመሰወሯ ዜና ከተሰማበት ቅጽበት ጀምሮ የእስራኤል ፖሊስ፣ የአየር ኃይል ሄሊኮፕተሮች፣ አነፍናፊ ውሻዎች እና ከ1,800 በላይ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን የተሳተፉበት ሰፊ የፍለጋ ዘመቻ ተካሂዶ ነበር።

ይሁን እንጂ እስከ ዛሬ ድረስ ሃይማኖት ያለችበትን ፍንጭ ሊሰጥ የሚችል አንዳችም የተጨበጠ መረጃ ወይም የሰው ምስክርነት ሳይገኝ ቀርቷል። ህፃኗ በምን ሁኔታ እንደተሰወረች፣ አስቀድሞ ከተጠነሰሰ እገታ ጋር የተያያዘ ይሁን ወይም ሌላ አደጋ፣ ፖሊስ ግልጽ የሆነ መላምት እንኳን ማጠናከር አልቻለም።

ጊዜው እየገፋ በሄደ ቁጥር የፖሊስ የፍለጋ ውጣ ውረድ ውጤት አልባ መሆኑ እና አዳዲስ መረጃዎች አለመገኘታቸው የቤተሰቡን ስቃይ እያበዛና እያደከም ሄደ። በዚሁ መነሻ በኋላ ላይ ምንም እንኳን ምምርመራው ለፖሊስ የከባድ ወንጀሎች መርማሪ ክፍል ቢተላለፍም ያመጣው አዲስ ለውጥ አልነበረም።

የፖሊስ ምርመራ አቅጣጫው ወደ መዘጋትና ተስፋ መቁረጥ ማዘንበሉን የተረዱት ወላጆቿ፣ ጉዳዩ ተራ የጠፋ ሰው ፍለጋ ሳይሆን የከፍተኛ ደህንነት፣ የመረጃና የስለላ አቅም የሚጠይቅ ህገ-ወጥ እገታ ነው በሚል ጽኑ እምነት የሺን ቤት  ኃላፊ ዳቪድ ዚኒ በቀጥታ ጣልቃ እንዲገቡ በይፋ ጠይቀዋል።

የእስራኤል ፖስት ዘገባ እንደሚያመላክተው፣ የህፃኗ ወላጆች ተስፋይ እና ባንቺ ካሳው ለደህንነት መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ በጻፉት ደብዳቤ ጥሪው አገራዊ፣ ለሕሊና የቀረብ ጥሪ መሆኑን አመልክተዋል። በደብዳቤያቸውም፤”ለ911 ቀናት ያህል ልጃችን ሃይማኖት ትመለሳለች በሚል በተስፋ ስንጠብቅ ቆይተናል። ነገር ግን ዛሬ ላይ የእስራኤል ፖሊስ በልጃችን ላይ ምን እንደደረሰ የሚያውቀው መረጃ የለም። የያዘው አቅጣጫ ወይም መላምት የለውም” በማለት ፖሊስ ያገባበትን መደናገር እና የምርመራ ክፍተት ገልጸዋል።

ወላጆቿ በቅርቡ ሌሎች የጠፉ ሰዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በደህንነት ተቋሙ የተቀናጀ ሥራ ተፈልገው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘታቸውን እንደ ማሳያ በማንሳት፣ የደህንነት መሥሪያ ቤቱ የላቀ የቴክኖሎጂና የስለላ አቅሙን ከተጠቀመ የልጃቸውን የአፈና ሚስጢር ሊያወጡት እንደሚችል ይናገራሉ።

በተመሳሳይ ጊዜ ወላጆቿና ደጋፊዎቻቸው በቴል አቪቭ በሚገኘው የሺን ቤት ዋና መሥሪያ ቤት ደጃፍ ሰላማዊ ሰልፎችን በማካሄድ “ፍትሕ ለሃይማኖት፣ ሃይማኖት ታጋች ናት” የሚሉ መፈክሮችን በማንሳት ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

አባቷ አቶ ተስፋይ በደብዳቤያቸው እና በሰልፉ ላይ ባደረጉት ንግግር “የደህንነት ተቋማቱ ለጉዳዩ የሰጡት ዝቅተኛ ትኩረት ከቆዳ ቀለም ልዩነት ጋር እንዳይያያዝ ያላቸውን ስጋት ገልጸው፣ እንደ አንድ አባት ወደ ዚህ መምጣቴ ስህተት እይድለም እና እስራኤል ለሁሉም አይሁዳውያን አስተማማኝ አገር መሆኗን አስመስክሩልኝ” ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ከዚህ በኋላ ይህ የቤተሰቡ አጣዳፊ አቤቱታ አገራዊ የደህንነት ተቋሙ የጉዳዩን ፋይል ሙሉ በሙሉ ተረክቦ የጠፋችበትን ምስጢር እንዲፈታ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ነው።

የሃይማኖት ካሳው ጉዳይ አሁንም ቢሆን የእስራኤልን ህዝብና የመንግሥት መዋቅር የሚያስጨንቅ ትልቅ ያልተመለሰ ጥያቄ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን፣ የደህንነት ተቋሙ የቀጥታ ጣልቃ ገብነት ለፍለጋው አዲስ ምዕራፍና ህይወት በመስጠት እውነታውን ወደ ብርሃን ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“አዲስ አበባን ኦሮሞ ዘረፋት? እውነቱን ልንገራችሁ” ተሳታፊ አባል The Truth About Addis Ababa: A National Dialogue Panelist’s

የቀረበውን ጽሑፍ ይዘትና መልእክት ሳይለወጥ፣ የፊደልና የሰዋሰው ግድፈቶች (ስፔሊንግ፣...

በውጭ ኃይሎች በመገዛት ምርጫና የብሔራዊ ምክክር ሂደቱን ተስፋ ለማጨናገፍ የተቋቋሙ ጥምረቶች ፈረሱ

የስብሰባ መረጃ በማያያዝ ብሔራዊ አገራዊ የምክክር ሂደቱ እንዳይሳካ ዘመቻ...

የኤርትራ ባንዲራ እያውለበለበች የታገተችው የነዳጅ ጫኝ መርከብ የኢራን ንብረት ናት

አዲስ ሪፖርተር ዜና | አዲስ አበባ - የኤርትራን ባንዲራ...