አዲስ ሪፖርተር ዜና | አዲስ አበባ – የኤርትራን ባንዲራ እያውለበለበች የተጠለፈችው «ሲቡ 1» የምትባለዋ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ጠለፋ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ አገዛዝ ጣጣ ይዞ እየመጣ ነው። ይህቺ መርከብ ቀደም ሲል ምመጠሪያ ስሟ፣ «ሲሙል» ነበር። በታህሳስ 2025 የአሜሪካ የፋይናንስ ሚኒስቴር ማዕቀብ የጣለባት ይህቺ መርከብ የኢራንን ስትሆን፣ የነዳጅ ውጤቶች በማጓጓዝ ድብቅ የንግድ መስመር በመዘርጋት የምትከሰስ ናት።
በአራት ታጣቂ የባህር ላይ ዘራፊዎች ከየመን አል- ሙካላ የወደብ ከተማ በስተምስራቅ 136 ማይልስ ርቀት ላይ በኤደን ባሕረ ሰላጤ የተጠለፈችው ይህቺ መረከብ፣ በኤርትራ ባንዲራ የምትንቀሳቀሰውን እና «ሲቡ 1(Sibu 1)” የሚል ስያሜ እንዳላት ጠቅሰው የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት፣ መርከቧ የኢራንን የነዳጅ ማዕቀብ ለመሸሽ በሚደረግ ድብቅ የእንቅስቃሴ መዋቅር «Shadow fleet» ውስጥ የምትንቀሳቀስ መሆኗን ተከትሎ ዜናው አሜሪካንን ጨምሮ በኃያላን ሀገራት ዘንዳ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል።
Iran linked oil tanker falls victim to Somali piracy surge An oil tanker under US sanctions for allegedly transporting Iranian petroleum products has become the latest victim of resurgent Somali piracy when it was boarded off the coast of Yemen and diverted toward Somalia.The Eritrea-flagged Sibu 1 was seized on Thursday by six armed individuals, according to the United Kingdom Maritime Trade Operations (UKMTO). The tanker was sanctioned last December by the US Treasury for allegedly being part of a shadow fleet that helps Iranian petroleum products evade US sanctions
የኤርትራ ሰንደቅ ዓላማ ከፊት እያሳየች በየመን ጠረፍ አቅራቢያ በባህር ወንበዴዎች ታግታ ወደ ሶማሊያ ጠረፍ የተሰሰደችው ይህቺ መርከብ፣ የኤርትራ አገዛዝ በቀይ ባህር ቀጣና ላይ የሚከተለውን ህገ-ወጥ እና አደገኛ አካሄድ በአደባባይ ያጋለጠ እንደሆነም እየተገለጸ ነው።
ሞሳድ ኮመንታሪ የኤርትራ መንግስት አክራሪ የእስልምና ኃይሎችን በማሰልጠንና በማስታጠቅ እንደተሰማራ፣ የሱዳንን የርስ በርስ ጦርነት በማቀጣጠልና በምስራቅ አቅጣጫ የተለያዩ ብሄሮችን በማደራጀት መጠመዱን ጠቅሶ ሪፖርት ካወጣ በኋላ የተሰማው የመርከቧ ሚስጢር ለኤርትራ መንግስት መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ የተለያዩ ምንጮች እያስታወቁ ነው።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ህዝብ በግሽበትና በኑሮ ውድነት ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ጠቅሰው ኢራንን በኢኮኖሚ ይበልጥ ለማሽመድመድ ሌላ የከረረ ማዕቀድ ለመጣል መዘጋጀታቸውን ይፋ ባደረጉ ማግስት፣ ኤርትራ ለኢራን በስውር የነዳጅ ንግድ እንደምታሳልጥ ይፋ መሆኑ ሌላው ለዜናው መጦዝ ምክንያት ነው።
በመርከቧ ላይ 20 የሰራተኞች ቡድን የነበሩ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል 16 ህንዳውያን፣ እንዲሁም የሶሪያ፣ ሱዳን እና ኢራቅ ዜጎች ይገኙበታል ተብሏል። መርከቧ ንብረትነቷ የኢራን ሆኖ አሜሪካና ምዕራባውያን አጋሮቿ በኢራን ላይ የጣሉትን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ለማምለጥ ከሚጠቀሙባቸው ድብቅ መርከቦች አንዷ እንደሆነች ተገልጿል።
የነዳጅ መርከቧ ከተለመደው የባህር ላይ የደህንነት እና ኢንሹራንስ ሽፋን ውጭ በመንቀሳቀሷ ለዘራፊዎች ቀላል ኢላማ እንድትሆን አድርጓታል። ይህ ክስተት በኤደን ባሕረ ሰላጤ እና በቀይ ባሕር አካባቢ እየተባባሰ የመጣው አለመረጋጋት የሶማሊያ ባህር ላይ ዘራፊዎች ዳግም እንዲያንሰራሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን እንደሚያሳይ ዘገባዎች አመልክተዋል። መርከቧ የተለመደውን መደበኛ የደህንነት እና ኢንሹራንስ ሽፋን የማትጠቀመው ሚስጢራዊነቷን ለመጠበቅ ይሁን ለሌላ የተገለጸ ነገር የለም።
የኤርትራ መንግስት ለእንደዚህ ዓይነቶቹ ማዕቀብ የተጣለባቸው የኢራን መርከቦች የራሱን ባንዲራ እና ከለላ መስጠቱ፣ የአስመራው አገዛዝ ከበስተጀርባ ከኢራን መንግስትና ከየመን ሁቲ ታጣቂዎች ጋር የዘረጋውን ሚስጥራዊ ግንኙነትና ሽርክና ቁልጭ አድርጎ እንደሚያሳይ ዜናውን ተከትሎ አስተያየት እይተሰጠ ነው። መርከቧ በየመን ሁቲ አማፂያን ቁጥጥር ስር ወደሚገኘው የራስ ኢሳ (Ras Isa) የነዳጅ ተርሚናል ተደጋጋሚ ጉዞዎችን ታደርግ እንደነበር የባህር ላይ የደህንነት መረጃዎች ማመልከታቸው ቀደም ሲል የተሰጠውን አስተያየት የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል።
የደህንነት ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት፤ ምንም እንኳን መርከቧ ከኢራን እና ከሁቲዎች ጋር ጥብቅ ግንኙነት ቢኖራትም፣ መረከቧ ያጋጠማት የሶማሊያ የባህር ዘራፊዎች ጥቃት የካሳ ገንዘብ ለመጠየቅ የተፈጸመ በመሆኑ፣ አጋጣሚው የታቀደ፣ የፖለቲካ ወይም የሁቲዎች የተቀናጀ ኦፕሬሽን አለመሆኑ ዜናውን ይበልጥ ታማኝ አድርጎታል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትና አገራትም የኤርትራ መንግስት ላይ ዓይናቸውን እንዲጥሉ አድርጓቸዋል።
የዓለም አቀፍ ህጎችን የሚያጣቅሱ እንዳሉት የኤርትራ መንግስት ማዕቀብ የተጣለባትን ኢራንን ህጋዊ ሽፋን መስጠት የፈጸመው ተግባር፣ የኢሳያስ አገዛዝ ለዓለም አቀፍ ደንቦችና ለቀጣናው ሰላም ደንታ እንደሌለው በግልጽ ለዓለም ያሳሳየበት እንደሆነ አመልክተዋል።
የኤርትራ መንግስትም ሆነ የኤርትራ ባህር ኃይል እገታውን ተከትሎ መግለጫ ወይም ማብራሪያ አለመስጣታቸው፣ አገዛዙ ተጠያቂነትን ለማምለጥና ጉዳዩን በዝምታ ለማለፍ የሚያደርገውን ጥረት ያሳያል እየተባለ ነው።
ይህ ሁኔታ የቀይ ባህር የደህንነት ስጋት ምን ያህል አስጊ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለስ ለዓለም አቀፉ የባህር ንግድ መስመር እና ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም አስተማማኝ የደህንነት ዋስትና መሆኑን በተግባር የሚያረጋግጥ እንደሆነም ተመልክቷል።
ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ይህ የመንገስትነት ወግ እና ቅርጽ የሌለውን የሻዕቢያ መንግስት “መንግስት ሁኑ” በማለት በየስርቻው የሚያካሂዱትን የትርምስና የሽብር ተግባር እንዲያቆሙ እየተማጸነች መቆየቷ ይታወቃል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






