የሞሳድ ክንፍ ኤርትራ ከእስልምና አክራሪዎች ጋር ትስስር ያላቸውን፣ የሱዳንን የተለያዩ የብሄር ታጣቂዎችን በማሰልጠንና በማስታጠቅ መጠመዷን ይፋ አደረገ

Date:

ከኢራን፣ ከየመን ሁቲዎች እንዲሁም ከእስላማዊ አክራሪዎች ጋር ስሟ የሚነሳው ኤርትራ፣ በቀይ ባህር ያላትን ሰፊ ክልል በመጠቀም ለቀይ ባህር ደህንነት ስጋት ነች ለምትባለው ኢራን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ክስ ሲሰነዘርባት ይህ የመጀመሪያ አይደለም

አዲስ ሪፖርተር — በስልታዊው የቀይ ባህር ዳርቻ ላይ የምትገኘው ኤርትራ፣ በሱዳን መደበኛ ጦር (SAF) እና በፈጣን ደጋፊ ኃይሎች (RSF) መካከል እየተካሄደ ያለውን አስከፊ ወታደራዊ ግጭት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በምስራቅ ሱዳን አቅጣጫ ያለውን ተፅዕኖዋን በከፍተኛ ደረጃ ለማስፋፋት እየሰራች መሆኑ ተገለጸ።

ሞሳድ ኮሜንታሪ በኦፊሴላዊ የኤክስ ገጹ እንዳመለከተው፣ ኤርትራ በምስራቅ ሱዳን አቅጣጫ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎችን ከማቋቋም አልፋ ከጽንፈኛ ኃይሎች ጋር የቀጥታ ግንኙነት በመፍጠር ቀጠናውን የማወክ ስትራቴጂዋን እየተገበረች መሆኑ ተመልክቷል።

ሞሳድ ኮሜንታሪ ይህን ከማለቱ በፊት ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ኤርትራ የሱዳንን ቀውስ በማባባስ፣ አጋጣሚውን በመጠቀም ተዋጊዎችን በማሰልጠንና በማስታጠቅ ዓይነተኛ ሚና እንደምትጫወት “ዓለም ይወቅልኝ” ስትል ደጋግማ አሁን ድረስ እያስገነዘበች መሆኑ ይታወቃል። ኤርትራ አሁን ላይ ብረት ያነሱ የኢትዮጵያ አማጺያንን በማሰልጠን፣ ከለላ በመስጠት፣ መሳሪያ በማጓጓዝና በማስታጠቅ የምታደርገውን ተሳትፎ አሳድጋ፣ በገሃድ “ጥምር ጦር” ማደራጀቷ ይታወቃል።

እንደ ተለያዩ ዘገባዎችና የጂኦ-ፖለቲካ ተንታኞች ገለጻ፣ የኤርትራ መንግስት በጋሽ-ባርካ የድንበር ቀጠናዎች ወታደራዊ የስልጠና ካምፖችን በመክፈት በምስራቅ ሱዳን የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ብሄረሰብ ተኮር ታጣቂዎችን፣ የቢጃ እና የራሻይዳ ቡድኖችን እንዲሁም ከእስልምና አማፅያን ጋር ትስስር ያላቸውን ኃይሎች በማሰልጠን እና በማስታጠቅ ላይ እንደምትገኝ ተረጋግጧል።

የአስመራ መንግስት ዋና ዓላማ ከራሱ ድንበር ውጪ ታማኝ የሆኑ የደህንነት መዋቅሮችን ማደራጀት ነው። ይህም ኤርትራ ሊቃጣባት የሚችልን ማንኛውንም ቀጣናዊ ስጋት አስቀድማ እንድትከላከል እና በድንበር አካባቢዋ ያለውን አለመረጋጋት ወደ ራሷ ግዛት እንዳይዛመት ለማድረግ እንደ “ደህንነት ከለላ” (Buffer Zone) ትገለገልበታለች።

በሱዳን ውስጥ አሁን ያለው የርስ በእርስ ጦርነት ቢቆም ወይም መፍትሔ ቢያገኝ እንኳ ኤርትራ በምስራቅ ሱዳን ማለትም በካሳላ፣ ገዳሪፍ እና ቀይ ባህር ግዛቶች የገነባቻቸው የታጣቂዎች እና የፖለቲካ መረቦች ከጦርነቱ በኋላም ቢሆን የሚዘልቁ ናቸው። ይህም ኤርትራ በቆዳ ስፋቷም ሆነ በህዝብ ቁጥሯ እጅግ በምትበልጣት ጎረቤቷ ሱዳን የውስጥ ጉዳይ ላይ የረጅም ጊዜ የበላይነት እና የፖለቲካ ተፅዕኖ እንዲኖራት አስችሏታል።

በአንድ ወቅት ኤርትራ በሱዳን ግዛት ውስጥ ያደራጀቻቸው ኃይሎች “ስትፈልግ ጃስ” የምትላቸው የትርምስ አቅሞቿ እንደሆኑና ግብጽ ይህንኑ የትርምስ ምንጭ በዋናነት በሎጅስቲክስና በገንዘብ እንደምትረዳ የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎች መግለጻቸው ይታወቃል።

የእስራኤል የስለላ ድርጅት አካል የሆነው Mossad Commentary በኤክስ ገጹ ይህንን ከማሰራጨቱ ቀደም ሲል፣ የእስራኤል የፖለቲካና የደህንነት ተንታኞች፣ የዜና ማዕከላት Haaretz እና Jewish News Syndicate – JNS እንዲሁም የጂኦ-ፖለቲካ ምርምር ተቋማት የኤርትራን መንግስት ወቅታዊ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ከእስራኤል ስትራቴጂካዊ ጥቅም አንጻር በስፋት ተችተው ማስጠንቀቂያ አውጥተው ነበር።

ኤርትራ ቀደም ሲል ከእስራኤል ጋር የጠበቀ የደህንነት እና የኢንቴልጀንስ ትስስር የነበራት ቢሆንም፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ግንኙነቷን ሙሉ በሙሉ በማቀዝቀዝ እና የእስራኤልን አምባሳደር ሳይቀበሉ በማስተጎል ወደ ኢራን፣ ቻይና እና ሩሲያ ጎራ መቀላቀሏ ይታወቃል። በተለይም ወደ ኢራን አክሲስ (Axis) ማዘንበሏ ጥያቄ ውስጥ ከከተታት ቆይቷል።

ይህ የኤርትራና መሰሎቿ እጥፋት እስራኤል በቀይ ባህር ላይ የነበራትን የደህንነት የበላይነት እንድታጣ እና በምትኩ የኢራን ተፅዕኖ በምስራቅ አፍሪካ ዳርቻ እንዲጠናከር መንገድ መክፈቱን Haaretz የእስራኤል ዕለታዊ ጋዜጣ እና The Cradle Caliber.Az Analysis በስፋት ከማስጠንቀቂያ ጋር አትመው ነበር።

የኤርትራ መንግስት የየመን ሁቲዎች በቀይ ባህር እና በባብ ኤል-ማንደብ የባህር ወለል ላይ በዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች እና በእስራኤል ኢላማዎች ላይ ሚሳይልና ድሮን ሲተኩሱ፣ ኤርትራ ጥቃቱን ለማውገዝ ፈቃደኛ አለመሆኗ፣ ቀደም ሲል ደግሞ ንክኪ እንደነበራቸው በተለያዩ ሪፖርቶች ተመልክቶ ነበር።

“የኤርትራ የባህር ክልል ለሁቲዎች መሸሸጊያ ወይም ድጋፍ ሰጪ ቀጠና ሆኖ እንዲያገለግል በዝምታ ፈቅዳለች” የሚል ስጋት በእስራኤል ዘንድ የተፈጠረውም በዚሁ መነሻ ነበር። በተጨማሪም በቅርቡ በቴህራን በተካሄደው የኢራን ፕሬዝዳንት በዓለ-ሲመት ላይ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተገኝተው የሃማስ መሪ እስማኤል ሀኒዬህ መገደልን ማውገዛቸው የአስመራን አቋም ግልጽ አድርጎታል በሚል የእስራኤልን ስጋት የሚጨምሩ ሪፖርቶች በ WaryaTV / Middle East Security Reports እና JNS (Jewish News Syndicate) በስፋት ወጥተዋል።

ኢራን ለኤርትራ የድሮንና የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ድጋፍ ለመስጠት መስማማቷን እና በምላሹ ደግሞ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ guard (IRGC) በኤርትራ የባህር ዳርቻዎች (በተለይም በአሰብ ወደብ አቅራቢያ) ወታደራዊና የክትትል እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርጉ ዕድል ማግኘታቸው እንዲሁ በተለያዩ ሪፖርቶች ተመልክቷል። ይህንኑ በዚሁ መረብ ኢራን በኤርትራ በኩል ለሁቲዎች እና ለፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖች የጦር መሳሪያ ማስተላለፊያ ኮሪደር (Smuggling Route) ልትጠቀምበት ትችላለች በሚል እስራኤል በከፍተኛ ስጋት እንድታየው ማድረጉን እንደ Stratfor Intelligence & Israeli Defense Policy Papers የመሳሰሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል። በተለይም ስትራትፎር ኢንተለጀንስ ያቀረበው ትንተና ጥልቅ ነበር።

እ.ኤ.አ. በኖቬምበር 2024 የኤርትራ የባህር ኃይል ከአየር ሁኔታ መበላሸት ጋር ተያይዞ ወደ ክልሏ የገቡ ሶስት የአዘርባጃን መርከቦችን እና 24 የሰራተኞች አባላትን በቁጥጥር ስር አውላ ለወራት አግታ መቆየቷ ይታወሳል። አዘርባጃን ከእስራኤል ጋር እጅግ የጠበቀ ስትራቴጂካዊ እና የወታደራዊ ደህንነት ወዳጅነት ያላት ሀገር በመሆኗ፣ ይህ የኤርትራ እርምጃ በኢራን ቀጥተኛ ግፊት የእስራኤልን ወዳጆች ለማስፈራራት የተደረገ ተልዕኮ ተደርጎ በእስራኤል ተንታኞች መወሰዱን Israel Regional Threat Analysis Reports የዘገበው ሌላው የኤርትራን እና የኢራንን ቁርኝት ለማሳየት ነበር።

የእስራኤል የደህንነት ተንታኞች ኤርትራን ከኢራን እና ከሁቲዎች ጋር በመደመር “የጥፋት አክሲስ” (Axis of Chaos) አካል እንደሆነች ይገልጧታል። በሱዳን ጦርነት ውስጥ የምስራቅ ሱዳን ታጣቂዎችን በማሰልጠን የምታደርገው እንቅስቃሴም ቀጠናውን በመበጥበጥ ለኢራን መስፋፋት አመች ሁኔታ ይፈጥራል ሲል Jewish News Syndicate Analysis አመልክቷል። በዓለም አቀፍ የንግድ መስመር (ባብ ኤል-ማንደብ) ላይ የሚፈጠር ማንኛውም አለመረጋጋት የእስራኤልን የኤላት ወደብ እንቅስቃሴ እና የንግድ ደህንነት በቀጥታ ይጎዳዋል።

እነዚህ ከላይ የተጠቃቀሱት እውነታዎች እያሉ ነው የሞሳድ አንድ ምዕራፍ ኤርትራ የሱዳንን ግጭት ተንተርሳ በድንበር አቅራቢያ የምታደርገውን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ተፅዕኖ እያሰፋች መሆኑን ከእስራኤል ጥቅምና ስጋት አንጻር ያመላከተው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የወደፊቱን ትውልድ የማዳን ጥሪ ለትግራይ – “13ኛ አሃድ የለም፤ 500 በላይ ቁስለኞች መከላከያ እጅ ናቸው”

አዲስ ሪፖርተር - አጥፊው ቡድን በከፈተው አላስፈላጊ ውጊያ ምክንያት...

እነ ክርስቲያስን ላይ ዘመቻ ሊከፈት ነው፤ ሰነዱ ላይ በመፈረም ይቅርታ መጠየቃቸው ተሰማ፤

አዲስ ሪፖርተር — ከአማራ ክልል ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ...

ግብጽ በኤርትራ በኩል በጀት ለቀቀች፤ አዲስ የትግል ስልት ተጀመረ፤ ኦሮሚያን ለማበጣበጥ ሰነድ ተዘጋጀ፤

ኦሮሚያ እስካልተረበሸ ድረስ የዲፕሎማሲ ጫና መፍጠር አንችልም። ስለዚህ ኦሮሚያ...