ሻዕቢያ “የጦርነት ፊሽካ ጠብቁ” ሲል የስጋት መመሪያ ሰጠ፤ “እናመስግናለ ሽሬ ቻዎ፣ ሳምንት ምዕራብ እንገናኝ” የሽሬ ተፈናቃዮች የስንብት ፌስቲቫል፤

Date:

አንድ እናት መነጋገሪያ ይዘው “አይዟችሁ” ሲሉ ይሰማሉ። እኚህ እናት በሽሬ የተፈናቃዮች መንደር የሚገኙ ናቸው። በልዩ ስሜት ጉዞ ወደ ሁመራ የሚል መፈክር ያሰማሉ። ጭብጨባና ዕልልታ ይሰማል። ከዚህ ቀደም በተደረጉ ጦርነቶች በሙሉ እናቶች በዚህ መልኩ ልጆቻቸውን እየመረቁ ሲሰጡ ታይቷል። ይህ እየሆነ ሻዕቢያ “ፊሽካ ጠብቁ” ማለቱ ተደምጧል። በፋኖ በኩል “በቅርቡ ይጠብቁን” ማስታወቂያ እየተሰራ ነው። ከሁሉም ወገን የጦርነትና የድል ዜና እየተሰማ ነው። ውጭ አገር ያሉ “ግፋ በለው” በማለት ዜናውን እያጦዙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ በየዋህነት ጦርነት እንደማያራዝም፣ ባጭር ጊዜ በቴክኖሎጂ ይሆናል ያለውነርምጃ እንደሚወስድ እያስታወቀ ነው። ሰፊ ቁጥር ያለው የፋኖ ኃይልም ከነአመራሩ ወደ ሰላማዊው ጎዳና እየጎረፈ ነው።

አዲስ ሪፖርተር – ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ወልቃይትን አስመልክቶ የተለያዩ መረጃዎች አብረው በሚሰሩና በተለያዩ ውላቸውን በቀደዱ አካላት እየተሰራጨ ነው። ጎን ለጎን ደግሞ የግብጽ፣ሱዳን፣ ሻዕቢያ፣ ፋኖና ትህነግ ጥምረትም በግልጽ ሚናውን የለየበት እንደሆነ እየታየ ነው።

ሻዕቢያ “የመጨረሻውን ፊሽካ ጠብቁ” ሲል ትዕዛዝ መስጠቱ ተሰማ። በሽሬ ተፈናቃዮች “ደህና ሁኚ ሽሬ፣ እናመስግናለን” በሚል እየጨፈሩ ናቸው። የሻዕቢያ ልሳን የሆኑ ሚዲያዎች ሱዳን በቤኒሻንጉል ጥቃት መሰንዘሯን እየዘገቡ ነው። ከመንግስት በኩል ከተለመደው የማስጠንቀቂያ መልዕክት ውጪ የተሰማ የተለየ ነገር የለም።

ከጥር 8 ጀምሮ እስከ ጥር 14 ለአንድ ሳምንት የግብጽ የድሮን ኦፕሬሽን ባለሙያዎች ስልተና ከሰጡ በሁዋላ ማጠቃለያው ላይ ብ/ጄኔራል ተክላይ ሃብተስሉስ የተባሉት የኤርትራ አየር ኃይል አዛዥ ባደረጉት ንግግር ነው፣ “የፊሽካውን ድምጽ ጠብቁ” ሲሉ ያስታወቁት።

አዲስ አበባ የሚገኙ የመረጃ ምንጮች እንዳሉት፣ በሰሜናዊ ቀይ ባህር አቅጣጫ፣ ጋህታላይ በሚባል ስፍራ ከግብጽ የመጡ የድሮን ኦፕሬሽን ባለሙያዎች ስልጠና ሲተናቀቅ “ሃያ አራት ሰዓት የኤርትራን የአየር ክልል እንድትጠብቁ ታዟል” የሚል መረጃ አስተላለፈዋል።

የዚሁ የጦርነት ዜና አካል የሆነ ፌስቲቫል በሽሬ እየተካሄደ ነው። “ሁመራ” የሚል ህትመት የሚታይበት ተፈናቃዮች “ቻው ሽሬ እናመሰግናለን ሰሞኑን ምዕራብ ያገናኘን/ ቻው ሽሬ ይቀንየልን፤ሰሙን ምዕራብ ይራከብና…” በማለት በፊስቲቫል መልክ በተዘጋጀ የቅስቀሳ በዓል ላይ ሲጨፍሩ ታይተዋል።

ከዛው “ምዕራብ ትግራይን ነጻ ለማውጣት የተዘጋጀ ኃይል” የተባለ ሚሊሻ በሰልፍ የምረቃ ስርዓት ሲደረግለት የሚያሳይ ቪዲዮ ከተፈናቃይ እናቶች ጭፈራና የሽሬ ስንብት ጋር ተያያዞ የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ከስፍራው ተላልፏል።

ሰሞኑን በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ የትሕነግ ቡድን ከኤርትራው የሻዕቢያ መንግስትና ከሌሎች የክልሉ ጠላቶች ጋር “ህገ-ወጥ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ፅምዶ” በመፍጠር የትግራይን ህልውና ለአደጋ አጋልጧል ሲሉ ከሰው ነበር።

በወልቃይት ግንባር ትህነግ ያሰማራውን ሰራዊት የሚመሩት ጄኔራል ምግበይ ባለፈው ዓርብ “ከኤርትራ አስፈላጊ ተተኳሽ መሳሪያ በበቂ ሁኔታ አግኝተናል። የፈለግነውን መሳሪያ በድንበር ለማሰገባት ተስማምተናል። በሚቀጥለው ሳምንት ምዕራብ ትግራይን እናስመልሳለን፤የከፋና ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ካለ ኤርትራ በጦርነቱ ተሳታፊ ትሆናለች” በማለት መናገራቸውን በማነቃቂያ ንግግሩ ላይ የተገኙ ምስክሮችን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

ባለፈው ቅዳሜ የሰይበር አድማ ለማድረግና በኢትዮጵያ አመጽ ለማቀጣጠል ከተለያዩ ድርጅቶች የተውጣጣ ኮሚቴ ሲመረጥ “መንግስትን ለመቃወም ብለን ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ሆነን እንዴት አገራችንን እንወጋለን” በማለት ጥያቄ ላቀረቡ “ይህን መንግስት ለመጣል ከሴይጣን ጋርም እንሰራለን” በሚል ምላሽ መሰጠቱና አቶ ነዓምን “እነዲህ ያለ ጥያቄ ሊቀርብ አይገባም” በማለት በሻዕቢያ ወኪልነት ማዕረግ ተግሳጽ መስተጣቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ከዚህም በተጨማሪ አቶ ነዓምን ከሁለት ቀን በፊት “ሾልኮ የወጣው የአገዛዙ ሚስጥር! አጋልጥ” የሚል ከአስመራ በZangi የተላከ መልዕክት አሰራጭተው ነበር።  የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችንና ሚዲያዎችን ከሻዕቢያ በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት የሚመሩ የሳይበር ታጋይ አቶ ነዓምን፣ ሻዕቢያና ትህነግ የመሰረቱትን “ጽምዶ” ይፋ ማድረጋቸውንና በወልቃይት በኩል አብረው በሱዳን አቅጣጫ ውጊያ ለመክፈት መስማማታቸውን ሱዳን ላይ ይፋ ባደረጉ ማግስት ያሰራጩት መረጃ በርካቶችን ያዝናና መሆኑን አንዳንድ የትህነግ ደጋፊዎች ሳይቀር ተችተዋል። “አብረን እየሰራን ነው እያልን እንደገና ወልቃይትና ራያ ለትግራይ ሊሰጥ ነው አማራ ንቃ” የሚል መረጃ ማሰራጨት ምግበይ እንዳሉት የሻዕቢያን አለመታመን የሚያሳይ እንደሆነ አመልክተዋል።

ከሁሉም በላይ ሚዛን የደፋው ግን “እንኳን” ያሉት የወልቃይት አካባቢ አክቲቪስቶችና “ነገሩ ገብቶናል” በማለት ምላሽ የሰጡት የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው።

በከፍተኛ ቁጥር ወደ ሰላማዊ መንገድ የመጡትና እየመጡ ያሉት የፋኖ ታጣቂዎችና ከፍተኛ አመራሮች፣ ብዛት “ጽምዶ” በፈጠሩት ወገኖች ዘንዳ ድንጋጤ ስለፈጥረና፣ ወደ ሰላም መንገድ የመጡት የፋኖ አደረጃጀቶች “ከሻዕቢያ፣ ግብጽና ትህንግ ጋር ሆነን አገራችንን አንወጋም። ወልቃይትን ለመሸጥ አንስማማ” በሚል መሰረታዊ ልዩነት በመሆኑ አቶ ነዓምን ይህን መረጃ እንዲያትሙ መታዘዛቸውን የሚገልጹ አሉ።

እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት “መንግስት ወልቃይትን ለትህነግ ሊሰጥ ነው” በማለት በሚስጥር ሰነድና በሚታወቁ ሚዲያዎች ዜና ማሰራጨት የተፈለገው በወላቃይት አካባቢ ህዝብ፣ አስተዳደርና ወደ ሰላም እየገቡ ባሉት የፋኖ አደረጃጀቶች መካከል ልዩነትና አለመተማመን ለመፍጠር ነው። ይህ ዘመቻ ደግሞ በቅንጅት በአማራ ክልል በኩል ጦርነት ለመክፈት ለተጀመረው ቅስቀሳ ግብአት እንዲሁን ታስቦ እንደሆነም አመልክተዋል።

በዚህ ጉዳይ ያነጋገርናቸው የሁመራ ዞን አስተዳደር አባል ቀጥጠኛ መልስ መስጠት እንደምያፈልጉ አመልክተው “ኃስይል ከተመረጠ የትከዜ ዘብም፣ ህዝቡም፣ መከላከያም ንቁ ናቸው። ኃይል ባይመረጥ የተሻለ ነው” ብለዋል።

በሚቀጥለው ሳምንት ወልቃይትን የመቆጣጠር ዕቅድ እንዳላቸው ጄ/ል ምግበይ ካስታወቁ በሁዋላ በሱዳን የሚገኙት የሻዕቢያና የትህነግ ኃይል በይፋ መቀላቀላቸው ተመልክቷል። ይህንኑ ተከትሎ ሻዕቢያ ፊሽካ ጠብቁ ብሏል።

ዘጠነኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው የኢትዮጵያ አየር ኃይል እያሳየ ባለው ወቅታዊ ብቃቱ ላይ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት የኢትዮጵያ አየር ኃይልን አቅም በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በእጥፍ እንደሚያሳድግ አስታውቀዋል። በተጠና  እቅድ፣ በዘርፉ የላቀ ደረጃ ከደረሱ አገራትና ከዋና ዋና አምራቾች ጋር በትብብር እንደሚሰራም አመልክተዋል።

አየር ኃይል ባሁኑ ወቅት የላቀ ብቃት ላይ እንደሚገኝ አመልክተው፣  መንግሥት በአየር ኃይሉ አማካኝነት የጠላት ዒላማን በትክክል በመምታትና ምሽጎችን በማፍረስ ውጊያን የማሳጠር አቅጣጫ እንደሚከተል ግልጽ አድርገዋል። ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟን “በአጭር ጊዜ ድል” እና “በየዋህነት” አሳልፋ እንደማትሠጥ ጭምር ዐቢይ የተናገሩ ሲኾን፣ የተወደውንም እናወራርዳለን  ብለዋል። አክለውም የመንግሥት ቀጣይ ዋና ተግባር የአገሪቱን ስትራቴጂካዊ ፍላጎት እና ብሔራዊ ጥቅም ማረጋገጥ መኾኑን ግልጽ አድርገዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በቅርቡ የተሳሳተ መረጃ ኢትዮጵያ ላይ ያሰራጩት የሮይተርስ የአዲስ አበባ ሰራተኞች ታገዱ፤ የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ፈቃዳቸው ተነጠቀ

ሮይተርስ በአዲስ አበባ ያሰማራቸው ሶስት ጋዜጠኞቹ የስራ ፈቃዳቸው እንዳልታደሰና...

“በመናበብ አመጽና ረብሻ ለመቀስቀስ ከፓርቲዎች ጋር ተስማምተናል” ጃዋር “በትርምስና በዓመጽ አናምንም” ፓርቲዎች

አዲስ ሪፖርተር - “እኛና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ሁለት ድርጅት...

ትህነግ የአፍሪካ ህብረት ጫና ፈጥሮ እንዲያደራድረው ነጥቦችን አስቀምጦ ደብዳቤ ጻፈ

አዲስ ሪፖርተር - የፕሪቶሪያው ስምምነት በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረገ የአፍሪካ...