ቴድሮስ ዝምታ መምረጡ ስትራቴጂ ነው?

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ሰዋሰው መልቲሚዲያ ባሰራጨው መግለጫ በተለያዩ ጉዳዩ በማይመለከታቸው አካላት ሲሰራጭ ለነበረው “የተሳሳተ የተባለ” ዘመቻ ማብራሪያ ሰጥቷል። ቴዎድሮስ ካሳሁን ስለተሰራጨው ሃሰተኛ የተባለ መረጃም ሆነ ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ስለሰጠው ማብራሪያ በይፋ የሰጠው ምላሽ ወይም ማብራሪያ የለም። አንዳንድ ሚዲያዎችና ታዛቢዎች “የማይመከታቸው አካላት በዚህ ደረጃ ሁከት ሲያስነሱ ዝም ማለቱ የማህበራዊ ሚዲያውን ውጥንቅጥ ከገበያ አንጻር እንደሚፈልገው ማሳያ ነው” ብለዋል።

ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ከአቀንቃኝ ቴዎድሮስ ካሳሁን ጋር የነበረው ውል በምን ምክንያት እንደተቋረጠ ይፋ አድርጓል። “ውሉ የፈረሰው ድምጻዊ ቴድሮስ ሊለቀው ካዘጋጀው አልበም ውስጥ ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ እንዳይካተቱ የሚፈልጋቸው ስራዎች አሉ” በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ፍጹም የተሳሳተ መረጃ እንደሆነ ገልጿል። ይህን አስመልክቶ ቴድሮስ ያለው ነገር የለም። ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ለሚሰራጩት ወሬዎች በአዎንታም ይሁን በአሉታዊ ጎኑ ምላሽ አልሰጠም።

ሰዋሰው “ከድምፃዊው ጋር በሙዚቃው ይዘት ላይ ተነጋግሮ እንደማያውቅና ጭራሽ የድምጻዊ ቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም አዳምጬ አላውቅም” በማለት በማህበራዊ ሚዲያ ሲረጭ ለነበረው የፈጠራ መረጃ ባዳ መሆኑን አመልክቷል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሆን ተብሎ የተሳሳቱ መረዎች ሲሰራጩ እንደነበር የጠቆመው ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ፣ ለስምምነቱ መቋረጥ ዋናው ምክንያት የCRBT የድምጽ ማሳመሪያ መብት በማን ይሁን? በሚል የተፈጠረ የሃሳብ ልዩነት እንደሆነ አመልክቷል። ቴድሮስ በዚህ ደረጃ የሃሰት መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ በተደራጀ መልኩ ሲበተን እውነታውን አለመናገሩ ወይም ዘፈኑን እንደሚለቅ ባስታወቀበት በፌስ ቡክ ገጹ እውነቱን አለማስታውቁ ያስገረማቸው “የማህበራዊ ሚዲያውን ጩከት ከገበያ አንጻር ይፈልገዋል። ሁልጊዜ ዘፈን ሲያወጣ እንዲህ መሰሉን ስልት መጠቅም ማዘውተሩ የተለመደ ነው፤ ይህን ልምዱን ቢያቆምና በሚታወቅበት ስራው ዝናውን ቢጠብቅ ጥሩ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። ታዋቂ ዩቲይበሮችም ስራውን አድንቀው የተፈጠረውን ማጯጯህ ሊያስቆም ይገባ እንደነበር አመልክተዋል።

ይህ እስከተሳፈ ድረስ አርቲስቱ ያለው ነገር የለም።

ሰንሰለ (Sewasew) መልቲሚዲያ መግለጫ

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከረጅም ዓመታት በኋላ “ኢቶሪካ” በሚል መጠሪያ ይዘት የመጣው አልበም ሊለቀቅ በተቃረበበት ወቅት በድምፃዊውና በድርጅታችን ሰንሰለ መልቲሚዲያ መካከል የነበረው ውል መቋረጡ የሚታወስ ነው።

በዚህም ሰሞኑን ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከሰንሰለ ጋር የነበረውን ውል ማፍረሱን የተመለከቱ መረጃዎች ሲወጡ ቆይተዋል። በዚህም ምክንያት በብዛት ባሉ የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አድናቂዎችና በድርጅታችን ሰንሰለ መልቲሚዲያ ወዳጆች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል። ይህንን ተከትሎ ድርጅታችን ስለተፈጠረው ነገር ማብራሪያ ለመስጠት ተገዷል።

ድምፃዊ ቴዲ አፍሮና ሰንሰለ መልቲሚዲያ የአብሮ መስራት ውል የተፈራረሙት ከአልበሙ የመልቀቅ ዜና በኋላ ሳይሆን ከዛሬ 3 አመት ከ8 ወር በፊት ሲሆን ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ደግሞ የአልበም ስራውን አጠናቆ ለማስረከብ የአንድ አመት ጊዜ ወስዶ ነበር።

ሆኖም ድምፃዊው በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የአልበም ስራውን ለማጠናቀቅ የወሰደውን ተጨማሪ ጊዜ በመረዳት መልቲሚዲያችን በትዕግስት ሲጠብቀው ቆይቷል።

ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ እና ሰንሰለ የነበራቸው ውል የተቋረጠው በሌላ የውል ማሻሻያ ሃሳብ እንጂ እንደሚባለው በነበረው የቀድሞ ውል ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ አይደለም።

ሰሞኑን ከሚናፈሱት የተሳሳቱ መረጃዎች ውስጥ አንዱ “ውሉ የፈረሰው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ሊለቀው ካዘጋጀው አልበም ውስጥ ሰንሰለ እንዳይካተቱ የሚፈልጋቸው ስራዎች አሉ” የሚለው አንዱ ነው።

ይሁን እንጂ ድርጅታችን ይህ ፈጽሞ የተሳሳተ መረጃ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፤ በተጨማሪም ከድምፃዊው ጋር በሙዚቃዊ ይዘት ላይ ተነጋግረን ካለመታወቃችን በላይ ሰንሰለ የድምፃዊ ቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም እስካሁን አዳምጦ እንደማያውቅ ለማረጋገጥ እንወዳለን።

ለስምምነቱ መቋረጥ በምክንያትነት የተወሰደው ጉዳይ በተለምዶ ሲ አር ቢ ቲ (CRBT) ተብሎ የሚታወቀው የመጥሪያ ድምፅ ማሰማሪያ ጉዳይ “በማን ይሁን?” የሚል ሙግትና የሃሳብ ልዩነት መፍጠሩ አንደኛው ሲሆን፤ በውሉ መሰረት የ ሲ አር ቢ ቲ (CRBT) መብት ለሰንሰለ የተሰጠ ቢሆንም መልቲሚዲያው ከድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ጋር በተፈጠረው የሃሳብ ልዩነት ብቻ ላለመለያየት ሌላ መፍትሄ ይዞ ቀርቦ ነበር። ይህም የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ የቀድሞት ስራዎች በሰንሰለ መተግበሪያ ላይ ተጭነው ተጨማሪ ክፍያ ለድምፃዊው ለመክፈል የሚል ሃሳብ ቢቀርብም የአማራጭ ሃሳቡን ድምፃዊው ሳይቀበለው ቀርቷል።

በአንጻሩ ከድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በኩል የቀረበ ሌላ መፍትሄ ቀርቧል መፍትሄውም ” የአልበሙ ከፊል ሙዚቃዎች በድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ዩቲዩብ ቻናል፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በሰንሰለ መልቲሚዲያ ይለቀቁ ” የሚል ነበር ይህን ደግሞ ሰንሰለ መልቲሚዲያ ሃሳቡን ሳይስማማበት ቀርቷል።

ድምፃዊ ቴዲ አፍሮና የሰንሰለ የስራ ግንኙነት ሂደት እስካዚህ ደረጃ ቢሆንም ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ለሰንሰለ መልቲሚዲያ የ3 አመት ከ8 ወር ወለድን ጨምሮ ክፍያ መልሷል፤ በዚህም ምንም አይነት አለመግባባት እንዳልተፈጠረ ለማረጋገጥ እንወዳለን።

ሰንሰለ መልቲሚዲያ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በነገው እለት ለሚለቀው ‘ኢቶሪካ’ ለተሰኘ አዲስ አልበም መልካም ምኞታችንን እየገለፅን፤ እንዲሁም እስካሁን ስለነበረን መልካም የስራ ግንኙነት ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related