በፈረንሳይ፣ በሎንዶን፣ ስቶክሆልም፣ ኦስሎ፣ ቢልጂየም፣ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ቀጠሮ በተያዘበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ሕዝብረት ያወጣው ጠንካራ ዓለም ዓቀፍ ቅጣትን የሚያስከትል ማስጠንቀቂያ ብዙ ትርጉም አለው። አሜሪካና አውሮፓ “ይህንን ጦርነት በፍጹም አንደግፍም፣ የሰላም ስምምነቱ እንዲፈርስ ሊፈቀድ አይገባም” እያሉ ይህን የሰላም ሂደት ከሚያፈርሱ ማናቸውም ወገኖች ጋር የሚደረግ ህብረትም ሆን ድጋፍ ዋጋ ያስከፍላል” ይላሉ የህግ ባለሙያው
አዲስ ሪፖርተር ዜና – የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያለውን ድጋፍ እስታውቆ፣ ያቀረበው ማስጠንቀቂያ ጥብቅ ነው፤ “የሰላም ሂደቱን የሚያደናቅፉ አካላት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተጠያቂ ይሆናሉ” ብሏል እንደሚችሉ አመልክቷል። ይህ መግለጫ የወጣው አሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖቿን መቀለ ልካ ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ መስጠቷን ተከትሎ መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ለጉዳዩ ትኩረት እንደተሰጠው የሚያሳይ እንደሆነ ተመልክቷል። የአፍሪካ ህብረት በጉዳዩ ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም መያዙን ማስታወቁ የሚታወስ ነው።
ለዋሽንግቶንና አውትራሊያ በተጨማሪ በፈረንሳይ፣ በሎንዶን፣ ስቶክሆልም፣ ኦስሎ፣ ቢልጂየም፣ የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ፋኖና ህወሃት በይፋ መደገፋቸውን፣ ዲያስፖራውም በያለበት ሰልፉን እንዲቀላቀል ጥሪ እያቀረቡ ባሉበት ወቅት የአውሮፓ ህብረት “ዓለም ዓቀፍ ተጠያቂነት ይከተላል” ማለቱ ድንገተኛ ዜና እንዳልሆነ ተመልክቷል። ከምንም በላይ ለህወሃት ቀጥተኛ ድጋፍ ሲሰጡ የነበሩት በአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ እና የደህንነት ፖሊሲ ተወካይ ጆሴፍ ቦሬል ይህን መግለጫ መስጠታቸው ይበልጥ ጉዳዩን አጠንክሮታል።
ከቀናት በፊት አሜሪካ “በቀጠናው ያለኝን ፍላጎት የሚጻረር በመሆኑ ውጊያ እንዲነሳ አንፈቅድም። ከሆነ ግን ሃብትን ማገድና የጉዞ ማዕቀብ እናደርጋለን። ይህ የመጀመሪያው ማስጠንቀቂያ ነው” በማለት መቀለ ድረስ በመሄድ በከፍተኛ የጦር መኮንኖቿ አማካይነት ማስጠንቀቂያ መስጠቷ ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎ ቦሬል ባወጡት መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እና ግጭቶች ከፍተኛ ስጋት እንዳሳደሩ በህብረቱ ስም አስታውቀዋል። ቃል በቃል “ጦርነት እንዲጀመር አንፈቅድም” ብለዋል።
ህብረቱ በፌዴራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል የተፈረመውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ማናቸውም ድርጊቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ አሳስቦ፣ ማናቸውም ችግሮችና ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ አሳስቧል።
ባለፉት ሳምንታት በራያ እና በሰሜን ምዕራብ ፀለምቲ አካባቢዎች የጦርነት እንቅስቃሴዎች መታየታቸውን ያውሳው ህብረቱ፣ ግጭቱ ዳግም ወደ ሰፊ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል አስጠንቅቋል። አክሎም “ከአስከፊው ጦርነት ገና በማገገም ላይ ያለውን ማህበረሰብ ዋጋ የሚያስከፍል ድርጊት ከመፈጸም መቆጠብ አለባቸው” ሲል መግለጫው ሁለቱንም ወገኖች አሳስቧል።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት እና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦሬል ባወጡት በዚህ መግለጫ፣ “የሰላም ስምምነቱ እንዲተገበር እንጂ እንዲዳከም መፈቀድ የለበትም” ብለዋል። ይህንኑ አቋማቸውን እጅግ ከፍተኛ አጽንኦት ሰጥተውታል።
ያልተፈቱ የአስተዳደር እና የወሰን ጥያቄዎች አስመልክቶ ህብረቱ በአገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ማዕቀፍ ብቻ ምላሽ እንዲያገኙ፣ ተፈናቃዮች በሰላም ወደ ቀያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ እንዲመቻች እና
የታጠቁ ኃይሎች ከግጭት ቀጠናዎች እንዲወጡ መደረግ እንዳለበት አሳስቧል። በህገመንግስቱ አወዛጋቢ አካባቢዎች የሚፈቱት በፌዴሬሽን ምክር ቤት አግባብ በህዝብ ውሳኔ እንደሆነ ይታወቃል።
ህብረቱ ማንኛውም የሃይል እርምጃ ዘላቂ ሰላም እንደማያመጣ በመጥቀስ፣ “ልዩነቶች መፈታት ያለባቸው በጠመንጃ ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ የፖለቲካ ውይይት ብቻ ነው” ሲል አቋሙን ገልጿል።
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያለውን ድጋፍ እየገለጸ፣ የሰላም ሂደቱን የሚያደናቅፉ አካላት ግን በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ አመልክቷል።ይህ መግለጫ የወጣው አሜሪካ እና የአፍሪካ ህብረት በጉዳዩ ላይ ተመሳሳይ ስጋት እንዳላቸው በገለጹበት ወቅት መሆኑ፣ ጉዳዩ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ትኩረት ማግኘቱን ያሳያል ተበሏል።
ስለ ማስጠንቀቂያው ያነጋገርናቸው የሕግ ባለሙያ የሰላም ስምምንትን ማፍረስ በምንም መስፈርት ተቀባይነት እንደሌለው አመልክተው፣ የህብረቱ የቅጣት ውሳኔ የሚጀመረው ዓለም የሚከተለው እርምጃ ከዚህ እንደሚቀዳ ተናግረዋል። አክለውም ቅጣቱ የሚሆነው ሃብትን ከማገድ። የጉዞ ማዕቀብ ከመጣልና ሲበዛም ከሌሎች መረጃና ማስረጃዎች ጋር ተዳምሮ በሽብር እስከ መፈረጅ ሊደርስ እንደሚችል አመልክተዋል።
አሁን ላይ በቀይ ባህር ባለው ውጥንቅጥ፣ በመካከለናው ምስራቅ በሚታየው ትርምስ አውሮፓ አፍሪቃ ቀንድ ጦርነትን በዚህ ደረጃ መቃወሟ እንደማያስገርም ያመለከቱት የህግ ባለሙያው፣ ጦርነት ቢነሳ ሰሞኑን የተጀመረው የመርከብ ላይ ሌብነትን ጨምሮ፣ አውሮፓ በስደተኞች እንደምትጥለቀለቅ ስለሚታወቅ ያንን መከላከላቸው የሚጠበቅ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ የባህር ላይ ሌብነቱን የመከላከል አቅም ስላለው የውስጥ ስለሙን ለማስጠበቅ ድጋፍ ማድረጋቸው ጥርጥር የለውም።
አሜሪካና አውሮፓ በጋራ በዚህ ደረጃ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ወደ ጦርነት የሚገባ ከሆነ የቅጣቱ ውሳኔው የኃያላኑ ህልውና ላይ እንደሚመሰረት የህግ ባለሙያው አመልክተዋል። የህግ ባለሙያው አክለውም ህወሃትን ጨምሮ የተለያዩ ታጣቂዎችን በመደገፍም ዋጋ ሊያስከፍል ስለሚችል በተለይ ዲያስፖራው ጥንቃቄ ሊወስድ እንደሚገባው መክረዋል። በዚህ ዙሩሪያ ተጨማሪ ሪፖርት እናቀርባለን።
ብራስልስ #አውሮፓህብረት #TPL #አዲስሪፖርተር #europe #ብልጽግ
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






