የአማራ ባንክ “ባንክ ካፕቸር” – አማራ ባንክ በጥቂት ግለሰቦች አንገቱ ታንቋል፣ ሕልውናውም አደጋ ላይ ነው

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው አማራ ባንክ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኝና የጥቂት ግለሰቦች መጠቀሚያ ወይም “ባንክ ካፕቸር” (Bank Capture) ሰለባ እንደሆነ ተምልክቷል። ፊትለፊት ወጥቶ ምላሽ የማይሰጠው ባንኩ በበኩሉ የባንክ ህግና ደንብ ተከትዬ እየሰራሁ ነው ሲል በግል ድረገጹና በፌስ ቡክ አውዱ ላይ አስፍሯል።

መንግስትን ውስጥ ሆነው ራሳቸውን በማደራጀት በሌብነት ሰንሰለት ሌላ ተገዳዳሪ ኃይል እንደሚገነቡ ጡንቸኞች በአማራ ባንክ ውስጥም “የባንክ ካፕቸር” ድራማ መፈጠሩን ያስታወቀው መናኸሪያ ሬዲዮ ነው። ሬዲዮው በዝግጅቱ አሉኝ ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ እንዳለው ባንኩ በጥቂት ሰዎች አንገቱን ታንቋል። ይህንን አካሄድ ነው የ”ባንክ ካፕቸሪንግ” ተፈጥሯል ሲል ዘገባው ይገለጸው። ይህ አካሄድ ባንኩ ያለበትን ደረጃ አደገኛነት ከማመላከቱ በላይ ተዋንያኖቹን መገምገምና እርምት መውሰድ ለነገ የሚባል ጉዳይ እንዳልሆነ የሚያስጠንቀቅ ሪፖርት ነው።

“ይህ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም የደረሰበት መናጋት በባንኩ ቦርድ እና በማኔጅመንቱ መካከል በተፈጠረ ከፍተኛ ፍጥጫ የጀመረ ነው” የሚለው የመናኸሪያ ሪፖርት፣ “የቀድሞው የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በጥር ወር 2018 ዓ.ም ገደማ በድንገት ከሥራ መልቀቃቸውን ተከትሎ ድብቅ የነበሩ የውስጥ ምስቅልቅሎች አደባባይ ወጥተዋል” በማለት ያገኘውን መረጃ ይዘርዝራል።  

የባንኩ የወቅቱ አመራሮችና ኃላፊዎችን ባንካቸው ስሙ በተነሳበት አግባብ ምላሽ እንዲሰጡ ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካለት የገለጸው መናኸሪያ ሬዲዮ፣ የባንኩን የኦዲት ግኝት እንዳገኘ አመልክቷል። ለሚቀርበለት ጥያቄ በግልጽ መስጠት ያልወደደው የአማራ ባንክ መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ባንኩ ያለበትን ወቅታዊ የፋይናንስ ጥንካሬ የሚያሳይና በተለያዩ ሚዲያዎች የቀረበበት ክስ አግባብ እንዳልሆነ የሚከላከል ነው።

ባንኩን አስከፊ አደጋ ላይ ጥሎታል የተባለውና በምስጢር የተያዘው የኦዲት ግኝት እንደሚያሳየው፣ በባንኩ የሂሳብ መዝገብ ላይ ያለው ቁጥርና በተጨባጭ በእጅ ላይ ያለው ገንዘብ ሰማይና ምድር ነው። በተለይም ባንኩ ሪፖርት ከሚያደርገው በላይ ከፍተኛ የሆነ የተበላሹ ብድሮች (NPL) ክምችት እንዳለበት ታውቋል። ለመናኸሪያ ሬዲዮ መረጃ የሰጡ ሠራተኞችና ባለአክሲዮኖች ያጋሩት መረጃዎች ባንኩ የገባበትን ቀውስ የሚያሳዩ ሆነዋል።

ከሚዲያዎች የተነሳበትን ወቀሳ በድፍኑ በመቃወም ያተረፈውንና ያለውን ሃብት በቁጥር አስቀምጦ ስለ ባንኮች አሰራር ህጋዊነት የዘረዘረው መግለጫ ከላይ የተባለውን አያስተባብልም።  

መናኸሪያ ሬዲዮ የደረሱትን መረጃዎች ጨምቆ እንደዘገበው ከሆነ ባንኩ ጥቂት በማይባሉ ትልልቅ ባለሀብቶች አንገቱ ታንቋል። “ጥቂት የማይባሉ ባለሃብቶች የባንኩን አንገት አንቀው መያዛቸው ተሰምቷል” የሚለው ሪፖርት ምሳሌ በማንሳት የድምዳሜውን መነሻ ያብራራል። “ለምሳሌ ያህል ጄር ኃ.የተ.የግ.ማ (Jerr PLC) እና ግሪን ኢትዮ ትሬዲንግ (Green Ethio Trading) የተባሉ ሁለት ኩባንያዎች ብቻ የባንኩን አጠቃላይ የብድር መጠን 28 በመቶ በላይ ያህሉን ተቆጣጥረታል” በማለት የመረጃውን ታማኝነት በማንሳት ይሞግታል።  ይህንኑ ድምዳሜውን ሲያጸና፣ ምሳሌው ባንኩ ለጥቂት ግለሰቦች ጥቅም የቆመ መሆኑን ማሳያ ተደርጎ የሚቀርብ እንደሆነ አመላክቷል።

የቀጥታ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በድረ ገጹ ላይ ሰፊ መከላከያ ያቀረበው ባንኩ “ለአንድ ተበዳሪ የሚሰጥ ብድር ከባንኩ ካፒታል ሃያ አምስት በመቶ በታች እንዲሆን የሚለውን መመሪያ እያከበረ መሆኑ ተረጋግጧል” ሲል ከባንኩን አጠቃላይ የብድር መጠን ሃያ ስምንት በመቶ የሚሆነውን ለሁለት ገለሰቦች ወይም ድርጅቶች ብቻ መስጠቱን ሊያስተባብል ይሞክራል።

የጥሬ ገንዘብ እጥረት ችግርን ከፈታ ከአንድ ዓመት በላይ እንደሆነውና በሞባይል ባንኪንግ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ማስተላለፍ እንደሚቻል ጠቅሶ ባንኩ በምቾት ዞን ውስጥ እንደሚገኝ ቢገልጽም፣ አማራ ባንክ የብድር ክምችትና የሂሳብ አያያዝ ጉድለት ቀስፎ እንደያዘው የመናኸሪያ ሬዲዮ መረጃ ላይ የተመረኮዘ ሪፖርት ያጋልጠዋል።

ባንኩን ለከፋ የእጅ በእጅ ገንዘብ ዝውውርና የአቅም ማነስ ችግር መጋለጡን የሚዘርዝረው ሪፖርቱ፣ “አማራ ባንክ በአሁኑ ወቅት ያለበትን የገንዘብ እጥረት ለመሸፈን ሲል ብቻ ከሌሎች አቻ ባንኮች ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለመበደር መገደዱን ምንጮቹ አረጋግጠዋል” ሲል በድረገጹ ያሰፈረውን የመከላከያ ሪፖርት ገበና ገልጦበታል።  

የኢንዱስትሪ ባለሙያዎችና ለባንኩ አሰራር ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ከሆነ፣ አምራ ባንክ ላጋጠመው ምስቅልቅል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተገቢውን ቁጥጥር አለማድረጉ ሚና አለው። መናኸሪያ ሬዲዮ ስም ሳይጠቅስ “አንዳንድ ባለሥልጣናት” ሲል የጠራቸው አካላት ከግል ባንኮች ጋር ያላቸው ግንኙነት ለብልሽቱ አስተዋጽዖ አለው፤ ሪፖርቱ “ጥላሸት ያረፈበት” ሲል ያመለከተው የባንኮችና የባለስልጣናት ግንኙነት፣ለዘርፉ መበላሸት ትልቁን ድርሻ እንዳለው ተመልክቷል። ከምንም በላይ ባንኮች ሙያው ከሚፈቅደው አሰራር ይልቅ ለፖለቲካ ታማኝነትና ለብሔር ስብስብ ቅድሚያ መስጠታቸው ለወደፊት ደህንነታቸው አደጋ መሆኑ በባለሙያዎች በተደጋጋሚ የሚሰጥ ማስተንቀቂያ እንደሆነ ይታመናል።

ከአማራ ባንክ ሠራተኞችና ከባለአክሲዮኖች የተገኘው መረጃ እንደሚያስጠነቅቀው፣ ባንኩ በጥቂት ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እጅ መውደቁ ለከፍተኛ ቀውስ ዳርጎታል።  ያለው የአመራር መከፋፈል ተቀማጭ ገንዘብ ላላቸው ደንበኞችና ለብዙኃኑ ጥቃቅን ባለ አክሲዮኖች ትልቅ የህልውና ስጋት እንደሆነባቸውም ተመልክቷል።

ይፋ አይውጣ እንጂ ልክ እንደ አማራ ባንክ በርካታ የግል ባንኮች በብድር አሰጣጥ አሰራር ግድፈት እየዋለ ሲያድር የገቡበት የሳራና የውድቀት ማጥ እንደሚገለጥ በስፋት እየተደመጠ ነው። በተለይም አሁን ላይ ብሄራዊ ባንክ የቁጥጥር ሰንሰለቱን ጠበቅ ማድረጉ ነገሮችን እየገለጣቸው እንደሆነ በግል ባንክ ውስጥ በመካከለኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ ይናገራሉ።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

አዲስ ሪፖርተር - ኢራን በእስራኤልና በአሜሪካ የተከፈተባትን  ጦርነት ለመመከት...

በፊንቴክ ኢንቨስትመንት የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ ታዋቂ አርቲስቶች እና ድርጅቶች ንብረት በፍርድ ቤት ታገደ

አዲስ ሪፖርተር - በፊንቴክ ኢንቨስትመንት አማካኝነት "መኪና እናስመጣላችኋለን" በሚል...

የመሬት ይርጋና የታሪካዊው ሰበር ውሳኔ

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ የንብረት ሕግ ታሪክ ውስጥ ለዘመናት...

NBE Mandates Strategic Consolidation to Stabilize Ethiopia’s Banking Sector

Addis Reporter - The National Bank of Ethiopia (NBE)...