“አቶ ነዓምን ከአቶ ጃዋር ጋር ይሠራሉ። ከአቶ ጂሬኛም ጋር በአንድ ግብረኃይል ውስጥ አብረው ናቸው። አቶ ነዓም የሻዕቢያና የቤተክርስቲያን ክንፉ የበጀት አገናኝ ናቸው። ግንኙነታቸው በዚህ ደረጃ ከሆነ፣ የአርሲው ግድያና ግድያው እየተዘገበ ያለበት መንገድ “የሸዋ ኦሮሞዎችን ማነሳሳት” የሚለው የሞዐ ተዋሕዶ የድህረ ምርጫ የአመጽ ዕቅድ አካል ሊሆን የማይችልበት አግባብ የለም”
አዲስ ሪፖርተር (ዋሽንግተን ዲሲ) — ከጥቂት ምርጫ ጣቢያዎች በስተቀር በሰላም መጠናቀቁ በአውሮፓ፣ በአፍሪካ፣ በአገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ታዛቢዎች የተመሰከረለት ምርጫ እንዳይካሄድና ለማሰናከል ቢሞከርም ባለመሳካቱ፣ የድህረ ምርጫ አመጽ ለመቀስቀስ አማራጭ ዕቅድ ተይዞ ነበር።
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከፈጠሩት ጥምረት ውስጥ በከፊል ቅሬታ ያሰሙበት ምርጫ የሚሰናከል ባለመሆኑ፣ በአሜሪካ የኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ የተቀረጸው ሚስጥራዊ ዕቅድ የሸዋ ኦሮሞ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን ማነሳሳት ነበር። የዚህን ሚስጥራዊ ዕቅድ ይፋ መሆን ተከትሎ በአርሲ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ፤ ረብሻውን በሚፈልጉት፣ ረብሻ እንዲፈጠር ብዙ ሀብት ባፈሰሱና ከእነዚሁ ኃይሎች ጋር ተመሳሳይ ዓላማ በሚያራምዱ አካላት ለፖለቲካ ዓላማ እየተጠቀሙበት መሆኑ መነጋገሪያ ሆኗል።
ይህን አሰቃቂ ግድያ ከሰብአዊነት አግባብ የመመልከት ችግር ብቻ ሳይሆን፣ በስም የሚታወቁትን ገዳዮች ለይቶ ማውገዝ ያልተፈለገበት ምክንያት፣ ድርጊቱ ሆነ ተብሎ በቅንጅት የተፈጸመ ለመሆኑ አመላካች እንደሆነ ተወስዷል።
“አክራሪነት በኢትዮጵያ ቦታ የለውም” — የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መግለጫ
ግድያውን አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዘግይቶም ቢሆን ባወጣው መግለጫ “አክራሪነት በኢትዮጵያ ፍጹም ቦታ የለውም” በማለት ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። ገዳዮቹንም “ሽብርተኛው የሸኔ ታጣቂ” ሲል ጠርቷል። በአካባቢው ተደጋጋሚ ግድያ ከመፈጸሙ አንጻር የመንግሥት መግለጫ ከወቀሳ የሚያድነው ባይሆንም፣ የድርጊቱን ፈጻሚዎች ስም ሰላባዎቹ በግልጽ አስታውቀው እያለ ሌሎች ዝም ማለታቸው አነጋጋሪ ብቻ ሳይሆን አስደንጋጭም መሆኑ እየተገለጸ ነው።
ይህንኑ የሃይማኖት ካርድ በመጠቀም አገርን የማበጥበጥ አደገኛ አካሄድ አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፣ ማናቸውም ዓይነት ሃይማኖትን ወይም ብሔርን ሽፋን ያደረጉ የጽንፈኝነትና የአክራሪነት እንቅስቃሴዎች ላይ መንግሥት የማይታገስ መሆኑን በግልጽ አስታውቋል፦
“ኢትዮጵያ የብዝሃነትና የዘመናት አብሮነት መገለጫ እንጂ የአክራሪዎች መናኸሪያ ልትሆን አትችልም። አክራሪነት በኢትዮጵያ ፍጹም ቦታ የለውም። የሕዝቡን የሃይማኖትና የብሔር ስሜት በመጠቀም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘትና አገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን መንግሥት በትዕግሥት አይመለከትም። የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና የዜጎችን ሰላም ለመጠበቅ የማያወላውል ጠንካራ እርምጃ ይወሰዳል።”
የአርሲው ግድያ እውነታ እና የሸኔ ታጣቂዎች ሚና
በግንቦት 23 ቀን በአርሲ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ከአካባቢውና ከደህንነት ምንጮች የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ ድርጊቱን የፈጸሙት ቦታ በመቀያየር ተደብቀው ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጋር የሚተኩሱ የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው። ከተሰነዘረባቸው ጥቃት ያመለጡ ወገኖች ያረጋገጡትም ይህንኑ የሸኔ (ኦነግ ሸኔ) ታጣቂዎች መሆናቸውን ነው። እነዚህ ታጣቂዎች በንጹሃን ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በመፈጸም የሚታወቁ ሲሆን፣ የአርሲውም ጥቃት የዚሁ እኩይ ተግባራቸው ቀጣይ አካል እንደሆነ በስፍራው ያሉ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ተናግረዋል።
ምስክሮቹ ይፋ ያደረጉት እውነታ ይህ ሆኖ ሳለ፣ ሐቁን ወደኋላ በመግፋት ግድያውን አስመልክቶ በስፋትና በብዛት የሚሰራጩት መረጃዎች በአሜሪካ የኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ ከቀረበው “ሃይማኖታዊ ስሜትን ቀስቅሶ አመጽ የመፍጠር” ስትራቴጂ ጋር የሚገጣጠሙ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ማሳያ ሆነው ተወስደዋል።
ከምንም በላይ “እኔ በተወለድኩበት አካባቢ ብቅ ብትል አንገትህን በሜንጫ ነው የምንልህ” በሚለው ጽንፈኛ አነጋገሩ የሚታወቀው ጃዋር መሐመድ ዜናውን ቀድሞ ይፋ ማድረጉና በዜናውም ቀድሞ መንግሥት እንደፈጸመው ማስታወቁ ጥያቄ የፈጠረባቸው ሲሆን፣ ጉዳዩ ተመልሶ ወደ ጃዋር እያመላከተ ነው።
ጃዋር መሐመድ እና የፖለቲካ ኃይሎች ምላሽ
ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት፣ የኦፌኮ አመራር አቶ ጃዋር መሐመድ ጥቃቱ እንደተፈጸመ ቀድሞ በመውጣት መንግሥትን በማውገዝ እና ተጠያቂ ለማድረግ በመሞከር፣ የትክክለኛዎቹን ገዳዮች (የሸኔ ታጣቂዎችን) ማንነት ለመሸፋፈን ጥረት አድርጓል። ይህ የጃዋር ፈጣን ምላሽ የሸዋን ኦሮሞ በማነሳሳት የመንግሥትን የድጋፍ መሠረት ለመናድ በኤምባሲው ከቀረበው ሰነድ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ሆኖ ተገኝቷል።
ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የዋሽንግተን የፖለቲካ ተዋናዮች እንደሚሉት በአሁኑ ሰዓት ጃዋር ከኦነግ ሸኔ ጋር አብሮ ይሠራል። አቶ ነዓምን በሚመሩት የአመጽ አደራጅ ቡድን ውስጥ አቶ ጃዋር ሲወጡ፣ በምትካቸው ያስገቡት የኦነግ ሸኔ ቃል አቀባይና የመሪው ጃል ማሮ አማካሪ የሆኑትን አቶ ጂሬኛን ነው።
አቶ ጃዋር—ከግድያው ያመለጡ ወገኖችና የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ያዩትን መስክረው ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መሆናቸውን ይፋ ያደረጉበት የቢቢሲ ዘገባ ከመውጣቱ በፊት፣ አቶ ጂሬኛም ሳያስተባብሉ፣ የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊም መግለጫ ሳይሰጡ፣ መንግሥትም መግለጫ ሳያወጣ—የሸኔን ስም ለመከላከል ያሳዩት ፍጥነት የአብሮ መሥራታቸው ማሳያ እንደሆነ የዋሽንግተን ተባባሪያችን ያነጋገራቸው አካላት አስታውቀዋል።
ከተጠቀሱት አካላት ጋር አብረው በስብሰባ የሚቀመጡ የዘወትር የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግተን ተባባሪ የመረጃ ምንጭ እንዳሉት፣ አቶ ነዓምን ከአቶ ጃዋር ጋር ይሠራሉ። ከአቶ ጂሬኛም ጋር በአንድ ግብረኃይል ውስጥ አብረው ናቸው። አቶ ነዓም የሻዕቢያና የቤተክርስቲያን ክንፉ የበጀት አገናኝ ናቸው። ግንኙነታቸው በዚህ ደረጃ ከሆነ፣ የአርሲው ግድያና ግድያው እየተዘገበ ያለበት መንገድ “የሸዋ ኦሮሞዎችን ማነሳሳት” የሚለው የሞዐ ተዋሕዶ የድህረ ምርጫ የአመጽ ዕቅድ አካል ሊሆን የማይችልበት አግባብ የለም።
ከዚህም በላይ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው፣ በድርጊቱ ዙሪያ የታየው የጋራ ዝምታ እና ጉዳዩን ለፖለቲካ ትርፍ የማዋል አዝማሚያ ነው፦
- ጥናቱን አቀረበ የተባለው የ“ሞዐ ተዋሕዶ” ክንፍን ጨምሮ፣ የተለያዩ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ በርካታ አክቲቪስቶችና ታዋቂ የሃይማኖት መምህራን ጥቃቱን የፈጸመውን የሸኔ ታጣቂ ቡድን በይፋ ከማውገዝ ተቆጥበዋል።
- “ወገኖቻችን” የሚሏቸው ከስቃዩ ሜዳ ተርፈው የነገሯቸውን እውነት ወደ ጎን ማለታቸው ድርጊቱ አመጽን ለማቀጣጠል የተፈጸመ ስለመሆኑ ማሳያ ነው የሚሉ ጥቂት አይደሉም። በተለይም እየዋለ ሲያድር ይህን ሐሳብ የሚያራምዱት እየበረከቱ ነው።
- እነዚህ ክፍሎች የንጹሃንን ሕይወት ማጣትና የደረሰውን አሰቃቂ መከራ የቡድኑን የሽብር ተግባር በጋራ አውግዞ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ፣ ጉዳዩን ለራሳቸው የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ከማዋል ረገድ ያሳዩት ርብርብ በርግጥም “የድህረ ምርጫው ረብሻ በሃይማኖት ተቋማት ማኅፀን ውስጥ ይፈለፈላል” የተባለለት ዕቅድ ማሳያ አድርገው ተመልክተውታል።
ጉዳዩ እንደ ኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ዛፍ ሥር ተኮኖ እግረ መንገድ የሚገለጽ ሳይሆን፣ ስራውን ሪባን መቁረጥና ሴሚናር ብቻ እንዳደረገው፣ መኖሩና አለመኖሩ ተመሳሳይ ተደርጎ እንደሚገለጽለት የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት የተደናበረ አሠራር ሳይሆን፣ በጥብቅ ክትትልና ጥናት የማያዳግም እርምጃ የሚያሻው ጉዳይ እንደሆነ ከእነዚሁ ወገኖች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።
የ“ሞዐ ተዋሕዶ” እና የአቶ ነዓምን ሚስጥራዊ ግንኙነት
የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግተን ተባባሪ እንደገለጸው፣ የሞዐ ተዋሕዶ ክንፍ አባላት የሸዋ ኦሮሞን የመረጡበት ምክንያት “የአገዛዙ ዋና የድጋፍ ማዕከል በመሆኑና በብልጽግና ወክለው የሚመረጡት አብዛኛዎቹ የፕሮቴስታንት ተከታዮች ስለሆኑ የኦርቶዶክሱን ማኅበረሰብ በቀላሉ ለአመጽ ማነሳሳት ይቻላል” በሚል ስሌት እንደነበር ይታወሳል።
“ኦሮ ማራ ብሎ ነገር የለም። ኦሮ ማራ ሸዋ ነው። እሱም የሸዋ ኦሮሞ ነው” የሚሉት የዚሁ ዕቅድ ባለቤቶች አቶ ነዓምን፣ ይህንን የሃይማኖት ክንፍ በመጠቀም የሚሠራው ሥራ ሚስጥራዊነቱ እንዲጠበቅና በአመጽ አደራጅ ግብረኃይሉ ውስጥ ያሉ እንደ አቶ ልደቱ ያሉ የሕወሃት ክንፍ አመራሮች እንዳያውቁት አድርገው ነበር። ይህ ሚስጥራዊነቱ የጎላው ዕቅድ በአዲስ ሪፖርተር መዘገቡን ተከትሎ በአመጽ አደራጆቹ መካከል ከፍተኛ አለመተማመንና መከፋፈል እየፈጠረ መሆኑን ጠቅሰን መዘገባችንም አይዘነጋም።
ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን አቅንተው የሃይማኖት ግጭት እንዲነሳ በኤርትራ ኤምባሲ ዕቅዱን ያቀረቡት የሞዐ ተዋሕዶ ክንፎች አሁንም እዚያው ዋሽንግተን የሚገኙ ሲሆን፣ መመሪያ የሚቀበሉት ከመምህር ፋንታሁን ዋቄ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
የሞዐ ተዋሕዶ አመራር እንደሆኑ የሚናገሩት አካላት ስለዚህ ዕቅድ በይፋ ያሉት ነገር የለም። በአሜሪካ የኤርትራ ኤምባሲ የቀረበው ይህ አዲሱ የድህረ ምርጫ ዕቅድ በእነ መምህር ፋንታሁን ዋቄ ዕውቅና ስለመካሄዱ እሳቸውን በስልክ ለማግኘት በተደጋጋሚ ቢሞከርም አልተሳካም።
መምህር ፋንታሁን ፋኖን ያቋቋመው ሞዐ ተዋሕዶ መሆኑን፣ ዓላማውም አራት ኪሎ መግባት እንደሆነ፣ ይህንንም በይፋ ከሥነ ምግባርና ከቤተክርስቲያኗ ቀኖና በተወሰዱ አስተምህሮዎች አስደግፈው በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በይፋ ማስተማራቸውና በቃለ ምልልስ ላይ መናገራቸው አይዘነጋም።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






